ፅጌሬዳ
ክፍል 24
ሲመሻሽ በጋራ ተሰብስበን እራታችንን በላንና ሰንጨርስ አቶ ሳሙኤል ዛሬ ግን እንዴት እዚህ አመሸሽ መቼም እነሱ መተዋል የሚል ምክንያት ፈጥረሽ ነግረሽው ነው አደል አሏት ማሂን።
ማሂ የውሸት ፈገግ አለችና አባቴ ጠረንህ ሁላ ናፍቆኛልኮ ዛሬማ ካንተጋ ነው ማድረው አለች።
እኔ መች አጣኋት ይቺን ይቺንማ በይ ነይ ተነሽ አረፍ እንበል አሉና አቅፈዋት ወደመኝታ ቤታቸው ገቡ።
እኔና አባቴ ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን አባቴ ከድሮ ጀምሮ ምን ትጠላለህ ቢባል ከሰው ገንዘብ መበደር ነበር ሚለው አሁን ለእህቴ ሰርግ እንዴት ገንዘብ ለመበደር እንደተስማማ ጠየኩት ???
አባቴ ትኩር ብሎ አየኝና ልጄ ችግር ባለጌ ነው የማትፈልገውን ሰው እንድትሆን ያደርግሀል ጠብቀህ ያቆየኸውን ህግም እንድትሽር ሰው ፊት አንገትህን እንድትደፋ በቃ ሌላ ማንነት ይሰጥሀል ማጣት መጥፎ ነው ልጄ።
እኔ አሁን ላይ ልጄን አንቀባሮ ከመዳር በላይ ክብር የለም በዛ ላይ ቤቴን ሼጬ ሳይውል ሳያድር እመልሰዋለሁ አደል እንዴ ደሞኮ ሳሙኤል እንዴት አይነት ደግ ልብ ያለው ሰው መሰለህ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ተዋውቀንኮ አብሮ አደግ ጓደኛዬ የሆነ ያህል ነው የተቀራረብነው አለኝ።
በጣም ደስ ይላል አባቴ አሁን የድግሱን ሀላፊነት እናቴ ናታ ምትወስደው እኛ መች ነው ምንሄደው አልኩት።
አዎ እናትህ እንኳን ይሄን ብዙም ታቀላጥፋለች የሴት ወንድኮ ናት በዛ ላይ እሷ ሰው ይወዳታል በስራ ብዙ አትቸገረም እኛ 15 ቀን ሲቀረው ነው ምንሄደው አለኝ።
እሺ በቃ አሁን ደክሞሀል ተኛ ብዬ ወደመኝታው አስገባሁትና በረንዳው ላይ ወጥቼ ቆምኩኝና ትንሽ እራሴን ለመሰብሰብ ሞክሬ ተመልሼ ገብቼ ተኛሁ።
የዛን ሰሞን ስራ በሁለቱም በኩል ተጧጡፎልን ነበር ማሂም ባሏ ለስራ ከሀገር እንደወጣና ቤት ውስጥ ብቻዋን ስለሚደብራት እኛጋ እንደምትሆን ለአባቷ ነግራቸው እኛውጋ መኖር ጀምራለች ።
ሰርቼ ከስር ከስር ለእህቴ እንዲያስገቡላት ለሰዎች እሰጣለሁ ብሩን ምክንያቱም እኔ መታወቂያም ሆነ ቡክ የለኝም።
እህቴ በየቀኑ እየደወለች አልፈልግም አትላክልኝ ትለኛለች እኔ ምንም ያህል ገንዘብ ሳገኝ ወደሷ አካውንት አስገባለሁ እንደዛ እንደዛ እያልን ሰርጉ 15 ቀን ሲቀረው አባቴ ወደክፍለ ሀገር እንድንሄድ ጠየቀኝ እኔ ቢያንስ 10 ቀን ብሰራ ብዙ ብር እንደሆነና 5 ቀን ሲቀረው እመጣለሁ ብዬ እሱን ወደሀዋሳ ሸኝቼ እኔ ወደስራዬ ተመለስኩ።
ማታ ቤት ስገባ አቶ ሳሙኤልና አባቴ ተገናኝቶ እንደማያቅ ሰው በስልክ እረጅም ሰአት ያወራሉ።
እኔና ማሂ እዛው አንድ ሳሎን ቁጭ ብለን text እየተፃፃፍን እየተደበቅን እንሳሳቃለን።
በነገራችን ላይ ማሂ የእህት ሶስተኛ ሚዜ ነች።
ለሙሽሪት የሚያስፈልጋትን ሙሉ ወጪ የሸፈነችውም እራሷ ማሂ ነበረች ።
10 ቀኗን ከሚገባው በላይ ተሯሩጬ ሰራሁና 5 ቀን ሲቀረው እኔ አቶ ሳሙኤልና ማሂ ሆነን ወደ ሀዋሳ ሄድን።
ሰፈሩ እንዳለ የድግስ ድባብ ላይ ነው የኛ ግቢ ውስጥ ገቢ ወጪው የሰው ብዛት ድግሱ የዛን ቀን ነበር የሚመስለው እህቴ ታድለው ግን ቤተሰቦችህ ይሄ ሁላ ሰው ልክ እንደራሱ ድግስ ሲሯሯጥ ማየት ደስ ይላል አለች።
አዎ ደስ ይላል እዚህኮ አንዱ ሲደግስ ሁሉም እንደራሱ ድግስ ቀን ከሌሊት ነው ሚሰራው አልኳት።
የሰርጉ ቀን ደረሰ አባቴና እናቴ ምድር ላይ በነሱ ልክ ሰው ያለ አልመስል አላቸው ደስታቸው ወደር አልነበረውም ማሂም መቼም የሰው ደስታ ከራሷ በላይ ነው ሚያስደስታት ሽር ጉድ ስትል ነበር።
ድግሱ አደለም የተጠራውን ሰው ሌላም ህዝቦ ቢጨመር ያበላ ነበር ከመጠን በላይ ነው የተደገሰው ማለት እችላለሁ በዛው ልክ ደሞ ያልተጠራ ህዝብ አልነበረም።
የኔን መመለስ ያላወቁ አንዳንድ ሰዎች ደሞ ከድግሱ በላይ በኔ ሲገረሙም እያየሁ ነበር ።
አባቴ ወደቀድሞ ክብሩ ሲመለስ የመጣው ሰው ሁሉ እንኳን ደስ አለህ እያለ ከፍ ዝቅ ሲልለት እናቴ የቀድሞ ሳቋ ፈገግታውን ፊቷ ላይ ሳገኘው በጣም ደስ አለኝ። የሰው ሁላ አይን ከኔ ላይ አልነቀል ብሎ ነበር።
የሙሽራው መምጫ ሰአት ደረሰና ሙሽራው ሙሽሪትን በክብር ሊወስድ መጣ እኔ ማታ ከማሂጋ ሚጨፍረው ሶስተኛው ሚዜ ምን አይነት ይሆን የሚለውን ነበር በጉጉት ስጠብቅ የነበረው ።
የፈራሁት አልቀረም ሶስተኛው ሚዜ በጣም ቆንጆ ፂማም ልጅ ነበር ።
ሳየው ደሜ ፈላ አሁንኮ ከማሂጋ ማታ እንደሚዜ ተቃቅፈው ይጨፍሩ ይሆናል አብረውም ፎቶ ይነሳሉ ቆይ ቢወዳትስ እሷስ እንዳየችው ቢመቻት እያልኩ በውስጤ ሳብሰለስል ቆየሁና
ለራሴ ምን አይነት ቀሽም እንደሆንኩ ነገሬ ወደፕሮግራሙ ተመለስኩ
መመለስ አይበሉት ልቤ ብትንትን ብሎ ነበር ለምን እንደዛ እንደሆንኩ ግን ፈጣሪ ይወቀው ።
ሰአቱ ሲደርስ ሙሽራው ሙሽሪትን ይዞ ወደሱ ቤት ሄደ ማሂም አብራ ሄደች።
አንቺ እዚሁ ጠብቂያቸው አይባል ነገር ሆኖብኝ እንጂ ምንም ደስ አላለኝም ነበር።
ብቻ ግን ድግሱ በጣም አስደሳች ነበር ሰው ሁሉ ሲጨፍር ሲደሰት አባቴ በደስታ ብዛት መሳቅ እስኪከብደው ድረስ በደስታ ሲፈነድቅ አየሁት ።
አቶ ሳሙኤል ሁሉንም ሰው ልክ እንደሚያቃቸው ነበር ሲያስተናግዱ የነበረው በጣም ደስ ብሎኝ የማደርገው እስኪጠፋ ከሁሉም ሰውጋ እየተሳሳኩ እያሳለፍኩ በመሀል ማሂ ትዝ ትዝ ትለኛለች።
መቼስ በባህላችን መሰረት የሴት ቤተሰብ በሰርግ ቀን ወንዱጋ መሄድ ነውር ስለሆነ እንጂ ሄጄ የማሂን አይን አይን ባየው ደስ ይለኝ ነበር።
ሰርጉ አዳሩንም ጭምር ነበር ማለት እችላለሁ የሰፈሩ ሰው ሲቀውጠው አደረ ሳንተኛ በዛው ነጋ ማሂ ወደ 5 አካባቢ መጥታ ተኛች።
እኔ እንደዛው እንደፈጠጥኩ ነጋልኝ በነጋታው ከድግሱ ያልተናነሰ ሰው መጥቶ ነበር ።
እህቴ ደወለችና እንዴት እየሆንን እንደሆነ ጠየቀችኝ ነገርኳት የሷን አዳርም ጠየኳት አረ ወንድሜ እንዴት ደስ እንደሚል በጣም ደክሞኝ ነበር ግን ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነቃ የምትወደው ሰው እቅፍ ውስጥ መሆን በራሱ ሌላ አለም ነው ።
ብታይ በቃ አለምን በመዳፌ ያደረኳት ያህል ነበር ደስ ያለኝ ።
በዛ ላይ ትናት ያባቴና የናቴን ደስታ ሳይ ምነው ቀደም ብዬ ባገባሁ ነው ያሰኘኝ ብላ ሳቀች።
እኔም በጣም ደስ እንዳለኝ ነግሪያት ለመልሱ እንደምንገናኝ ተስማምተን ስልኩ ተዘጋ።
ማሂ በሚቀጥለው ቀን ያ ሁሉ ሰው ሲመጣ ሲጨፍሩ እንኳን እሷ አልተነሳችም ነበር።
አቶ ሳሙኤል አይ ማሂ ድካምኮ አትችልም የኔ ልጅ አሳዝናኝኮ ነው እንቀስቅሳት እንዴ ሲሉ እናቴ አይ እረፍት ታድርግ ችግር የለም ይደክማታል አለች።
ማሂ አረፋፍዳም ቢሆን ተነሳችና ወደመስተንግዶው ገባች ።
በመሀል በመሀል ስለሰርጉ እየጠየኳት ትመልስልኛለች ።
እና ሚዜውስ እንዴት ነበር ካንቺጋ የደረሰው አልኳት ።
አረ በስማም አንተ ምን አይነት ሰው እንደሆነ አሳቀቀኝ አይኑን ከኔ ላይ አልነቅል ብሎኝ ነበር ።
መጨረሻ ላይ ፊቴን ሳጠቁርበት ነው ካጠገቤ ዞር ያለው አለችኝ።
አልገባኝም ምን ማለት ነው ከሱጋ ዝም ብዬ መገልፈጥና መጃጃል ነበረብኝ እንዴ ምን አይነት ጥያቄ ነው ብላ እንደለመደችው አኮረፈችና ተነስታ
ሄደች።
✎ክፍል 25 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️ ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333