ፅጌሬዳ
ክፍል 26
አረ አቶ ሳሙኤል ከሴት ልጅ በላይ ወንድ ልጅ ነው ጠቃሚው እሱ ነው መከታ ሚሆነው እኔ እሻሎታለሁ አልኳቸው።
ማሂ እየሳቀች ከኋላ የመጣ አይን አወጣ አሉ ጭራሽ ሴት ልጅ ያን ያህል አስፈላጊ አደለም እያልክ ነው ለነገሩ አባቴ ከኔና ካንተ ማንኛችን እንደምንጠቅመው ያቃል አደል እንዴ አባቴ አለች እየተፍለቀለቀች።
አረ እኔ ስቀልድ ነው ልጆቼ
ሁሉም ሰው የየራሱ የሆነ ቦታ አለው የሚፈለግበት ልክ አለው አንዱን በአንዱ ቦታ መለካት ጥሩ አደለም አሉንና እኔ እንቅልፍ ሰአቴ እየደረሰ ስለሆነ ልተኛ በቃ እናንተ ተጫወቱ ብለው ተነሱ
እንዴ በዚህ ሰአት መተኛት የጀመርከው ከመቼ ጀምሮ ነው ትንሽ ቆይ እንጂ አለች ማሂ !!
አይ ልጄ ዛሬ ደከምከም ብሎኛል ልተኛ ብለው ወደመኝታ ቤታቸው ገቡ።
ማሂ አይን አይኔን እያየች አባቴኮ በውስጡ ስለሚይዝ ነው እንጂ በጣም አስከፍቼዋለሁ አውቆኮ ነው ሚስቀው
ወይኔ በናትህ እሱ እንደዚህ ከሚከፋብኝ ከሚያዝንብኝ ባልነግረው ይሻለኝ ነበር አለች።
አረ ማሂ ተረጋጊ እኔና አንቺ እንድናወራ ብለውኮ ነው ምናልባት ከፍቶሽ ደብሮሽ አዝነሽ ከሆነ ከኔጋ እንደጓደኛ እንድታወሪም አስበው ይሆናልኮ በቃ ተረጋጊ እራስሽን አታስጨንቂ አልኳት።
ምሽቱን ዝም ብለን ስናወራ ስንሳሳቅ አመሸንና እሷም ካባቷጋ እኔም ከትራሴጋ ተቃቅፈን ተኛን።
በነጋታው በጠዋቱ ያባቴ ስልክ ነበር ከመኝታዬ ያነቃኝ
ሄሎ አባቴ !
እንዴት አደርክ ልጄ ከእንቅልፍህ ቀሰቀስኩህ መሰለኝ እንዲሁ ስብሰለሰል አድሬኮ ካንተጋ ባወራ ቀለል ይለኛል ብዬ ነው ልጄ ሀሳብህንም ብትነግረኝ መልካም ነው አይመስልህም አለኝ።
አረ ልክ ነህ አባቴ ግን ስለምንድነው ምናወራው ማለቴ ያስጨነቀህ ነገር አለ እንዴ አልኩት።
ምን መሰለህ ልጄ መቼስ አሁን እዚህ ያለንን መሬት ሸጠን ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ተስማምተናል ግን ምን መሰለህ እዚህ ያለው ግቢያችን በጣም ሰፊና ንፁህ እንደሆነ ታቃለህ
ይሄንን ግቢያችንን ብንሸጠው እና እዛ ለመግዛት ብንሞክር እዛ የተሻለ ቦታ እንኳን አይገዛልንም እዚህና እዛ መሬት ሰማይና ምድር ነው ።
በዛ ላይ አሁን ልጄን ከዳርኳት የሰፈሩ ሰው እንደቀድሞው ሲያከብረኝ ጎንበስ ቀና ሲልልኝ ሳይ ደሞ ድጋሜ ሰፈሩን ትቼ መሄዴ ልቤን እርብሽ እርብሽ አደረገኝ።
ተወልደን ተድረን ወልደን ከብደን ከኖርንበት ቤት መውጣት ለናትህም ቢሆን ሊከብዳት ይችላል ልጄ አንተ እንደሀሳብ ምን ትለኛለህ አለኝ ።
ዝም አልኩኝ እኔጃ አባቴ ከናቴና ከእህቴጋ አውሩበትና አብራችሁ ሆናችሁ ደውልልኝ እኔም እስከዛ ትንሽ ላስብበት አልኩትና ስልኩን ዘጋሁት።
ከመኝታዬ ተነሳሁና ተጣጠብኩኝ ማሂም አባቷም ተነሱ ቁርስ ቀረበና እየበላን ለሁለቱም ያለውን ነገር ነገርኳቸው በነሱ በኩል ምን እንደሚያስቡ ጠየኳቸው።
ማሂ ድንግጥ ብላ እንዴ ማለት እነሱ ቤታቸውን ሸጠው ካልመጡ አንተ ልትሄድ ነው አለችኝ??
አይ ማሂ እሱን ፈጣሪ ያውቃል አልኳት
ፈጠን ብላ አይ በቃ ይሽጡት አለች።
አቶ ሳሙኤል ገልመጥ አደረጓትና ተይ ልጄ እንደዚህ አይባልም ።
እሱ የነሱ ውሳኔ ነው
እኔ ያለውን ነገር ካባትህጋ አወራለሁ አንተም አስቲ በደንብ አስብበትና ማታ ቁጭ ብለን ደውለን እናወራቸዋለን አሉኝ።
እሺ ብዬ ከቁርስ ቡሀላ እንደተለመደው ማሂ ወደ ጋራዥ አድርሳኝ ብዙ ዴሊቬሪ እቃዎች ስላሉ ከሰአት ሱቅ እንድመጣ ነገራኝ ተለያየን።
ባጋጣሚ ጋራዥም ብዙ ሚያስፈልጉ እቃዎች ስለነበሩ ካንዱጋ ሌላውጋ ስሽከረከር ሳላቀው 8 ሰአት ሆነ
የቀረኝን አንድ እቃ ለሞተረኛ ላኩና እኔ ወደማሂጋ ሄድኩ:: እስከዛ ሰአት ድረስ ምሳ ሳትበላ እየጠበቀችኝ ነበር።
አብረን ምሳ በላንና እቃዎቼን ይዤ እንደተለመደው አሪፍ ብር ሰርቼ ተመለስኩ ብሩን ለማሂ ሰጠኋትና አስቀምጭው አንችጋ አልኳት ።
ወደቤት አብረን እየተመለስን ስልኬ ጠራ
delivery ያደርስኩላት አንድ ልጅ 200 ብር ቲፕ ሰታኝ ነበር ።
እሷ ናት የደወለችው መጀመሪያ አላወኳትም ነበር ከዛ ግን ስሟን ስትነግረኝ ትዝ አለኝ ፈታ ያለች ልጅ ናት እያወራን በመሀል እኔ መሳቅ ጀመርኩ ደንበኛ እንደምትሆን ምናምን እየነገረችኝ በዛውም ጓደኛሞች መሆን እንደምንችልም ነገረችኝ።
ማሂ ፊቷ እየተቀየረ መኪናውን በፍጥነት መንዳት ጀመረች ቆይ መልሼ እደውልልሻለሁ ብዬ ስልኩን ዘጋሁትና ቀስ በይ እንጂ ማሂ ምን ሆነሻል አልኳት።
ለማውራት አልተመቸህ ሆኖ ነው መቼ ነው መልሰህ ምትደውልላት ደሞስ ስራህን አደል እንዴ የሰራኸው ከደንበኛጋ እንደዚህ መገልፈጥ ምን ይሉታል አለችኝ እየተኮሳተረች።
አይ እንግዲ ማሂ ደሞ ችግር አለብሽ ማንን ማውራት እንዳለብኝና እንደሌለብኝ አንቺ ነሽ እንዴ ምትነግሪኝ እንዴ ደሞስ ደንበኛ ሰው አደለም ያለው ማነው ጓደኛሞች እንሁን አለችኝ እሺ አልኳት አለቀ አንቺ ምን ያናድድሻል ስላት መኪናውን አቆመችና ውረድ አለችኝ።
የምርሽን ነው ልውረድ??
አዎ ውረድ አሁን ደውልላትና እዚሁ ጨርሰህ ና ወደቤት አለችኝ እንደለመደችው እንባ እየተናነቃት ነበር ስታወራ ።
ሁኔታዋ ግራ ስላጋባኝ ዝም ብዬ ቁጭ አልኩኝ።
አትወርድም እኔ ልውረድ አለችኝ በድጋሜሜ
የዛኔ በአንዴ ቅይርር አልኩኝ
ለምንድነው ከገዛ መኪናሽ ምትወርጅው እኔ ወርድልሻለሁ እንጂ ኤጭ አሁንስ በጣም ነው የሰለችኝ ማሂ አሁን ይሄ ምኑ አናዶሽ ነው እንደዚህ ምትቀየሪው ካንቺጋ እንደልጅ መጣላት መታረቅ እየሰለቸኝ ነው በቃ እንደውም እራሴን ማዳመጥ እፈልጋለሁ በእግሬ እመጣለሁ ሂጅ ብያት ልወርድ ስል መኪናውን አስነስታ ነዳችው።
አንቺ ግን ጤነኛ ነሽ ማሂ ቆይ ልክ ነው ማደርገው ብለሽ ታስቢያለሽ ማሂ ለኔኮ ብዙ ነገር አድርገሽልኛል አሁን ሰው ሆኜ ብዬድ ብለብስ ቢያምርብኝ ከሰዎችጋ ብግባባ ለሁሉም ነገር ምክንያቷኮ አንቺ ነሽ ንፁህ ልብ እንዳለሽ አቃለሁ ግን ማሂ እኔ ይሄ ምታኮርፊው ነገር የሆነ ቀን እንዳይሰለቸኝ እፈራለሁ በናትሽ በቃ እንደልጅ ቶሎ ቅይር ቅይር አትበይ እሺ እኔ ብዙ ሚያስጨንቀኝ ና ውስጤን ባዶነት እንዲሰማኝ የሚያደርገኝ ብዙ ነገር እንዳለ ታቂያለሽ በዛ ላይ አንቺ በየደቂቃው ስትቀያየሪቢኝ ደሞ በጣም ይከፋኛል ያበሳጨኛል
ማሂ አብረሽው ምትውይው ሰው ሁሌ ደስተኛ ሲያደርግሽ አብረሽ ስትስቂ ስትደሰቺ ስትከፊም አብረሽ ሲሆን ነው ደስ የሚለው እንጂ አሁን እየሳቅሽ ነው ሳልጨርስ ምታኮርፊ ከሆነ ከባድ ነው።
ብታምኝም ባታምኚም ያን ያህል ጊዜ ከፊደልጋ ስንቆይ አንድም ቀን አኩርፋኝ አታውቅም ምንም ነገር ሲፈጠር በግልፅ ነው ምንነጋገረው እንጂ አንኮራረፍም አልኳት።
ዝም አለችኝ
ዝምታዋ ደሞ መልሶ አስፈራኝ ሰው ዝም ሲል በውስጡ ትልቅ ነገር እያብሰለሰለ ነው ዝምታ ሲበዛ ያስፈራኛል ።
ግቢ ውስጥ ከደረስን ቡሀላ መኪናዋን አቆመችና ወረድን ወደቤት ልትገባ ስትል ነይ የሆነ ቦታ ደርሰን እንምጣ ብዬ ወደውጪ ይዣት ወጣሁ።
እንደዛ ከሆነ ሁለተኛ አጠገቤ ሴት እንዳታወራ ያሁኗንም ልጅ ብሎክ አድርጋትና አሳየኝ አለችኝ።
✎ክፍል 27 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️ ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333