ፅጌሬዳ
ክፍል 27
ለምን ይሄን የማደርግበት እኔን ሊያሳምነኝ የሚችል አንድ ምክንያት ብቻ ንገሪኝና አደርገዋለሁ አልኳት ።
በቃ አሳማኝ ይሁን አይሁን አላቅም ግን እኔ ደስ አይለኝም አለቀ።
የራስሽ ጉዳይ ነው አወራለሁ ብለህ ካሰብክ አውራ ግን ለኔ ትኝሽ resepect ካለህ በቃ አታውራ ደስ አይለኝም አለች።
ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ ማሂ ግን ደና ነሽ ማለቴ አሁን የኔ ስልክ ማውራት አለማውራት ላንቺ ክብር ከመስጠትጋ ምን አገናኘው አልኳት ።
በቃ ትርፍ ንግግር አልፈልግም ወደ ቤት ሄጄ እረፍት ማድረግ እፈልጋለሁ አለችና ወደኋላ ተመለሰች አልተከተልኳትም
ለራሴ ጊዜ መስጠትን ፈልጌ ነበር ወደፊት ወክ እያደረኩ መራመድ ጀመርኩ ።
አባቴ ያለኝን ነገር እንደ አዲስ ማሰላሰል ጀመርኩ ።
አሁን ቤቱ ባይሸጥና ወደዚህ ባይመጡኮ የአቶ ሳሙኤልን እዳ ከየት አምጥተን እንከፍላለን።
እኔስ ተመልሼ እዛ ሄጄ ልኖር ነው ወይስ እዚህ እነማሂጋ እስከመቼ ልቆይ ነው ግራ ገባኝ ።
የቤተሰቦቼ ህይወት መስመር ከያዘና ከተስተካከለ እነሱ ሚመቻቸው ቦታ ቢኖሩ ደስታዬ ወደር የለውም ግን ተመልሶ አባቴ በእዳ መያዝና መጨነቁ አይቀርም እኔ ደሞ ምን ሰርቼ ነው እዳቸውን ልከፍልላቸው ምችለው እቃ ለማድረስ ከተማ ለከተማ ዞሬ ነው ወይስ ደሞ ጋራዥ ውስጥ መሬት ለመሬ ተንከባልዬ ነው አላቅም ብቻ ምን ማሰብ እንዳለብኝ እስኪያቅተኝ ድረስ ሆድ ባሰኝ ውስጤን ባዶነት ተሰማኝ።
በመሀል አባቴ ደወለና አሁን እናውራ እንዴ ቤት ነህ?? አለኝ
አይ አባቴ ልገባ ነው ትንሽ ነው የቀረኝ ቆይ መልሼ እደውልልሀለሁ ብዬው ስልኩ ዘጋሁት።
ወደቤት ተመለስኩ
ቤት ስገባ ማሂ ጋቢ ለብሳ ያባቷ ጉልበት ላይ ተደግፋ ተኝታለች ።
አባቷ ፀጉሯን እያሻሹ ይደባብሷታል ሲያዩኝ ኖር ልጄ ተቀመጥ ተቀመጥ አሉኝ።
በእግዜር አይገባም ብያቸው ቁጭ አልኩኝና አባቴጋ ደወልኩ
አነሳው ከሁሉምጋ ሰላምታ ከተቀያየርኩ ቡሀላ ወደጉዳያችን ገባሁ ስፒከር ላይ አድርጌው ነበር ማወራቸው
መጀመሪያ የናቴ ሀሳብ ምን እንደሆነ ጠየኳት እኔ ልጄ ሁለት ልብ ነኝ እዚህ ብንኖርም ብዬ አስባለሁ በሌላ በኩል ደሞ ምናልባት ቢሸጥም ትርፋማ ልንሆን እችላለሁ ብዬ አሰብኩ ግን ከኔ በላይ የውጭውን ነገር እናንተ ታቁታላችሁ
አለች።
እህቴን በተራዋ ጠየኳት እሷ አሁን ከባለቤቷጋ እየኖረች ስለሆነ ዞሮ ዞሮ ከሀዋሳ እንደማትወጣ ነገረችኝ።
አባቴ ደሞ በተራው እኔን ጠየቀኝ ቁርጥ ያለ ነገር መናገር አልቻልኩም በቃ አንተና እማዬ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ላይ ድረሱና አሳውቁኝ እኔ በሁለቱም ሀሳባችሁ እስማማለሁ አልኩት አቶ ሳሙኤልም ጎሽ ልጄ እንደሱ ነው ሚሻለው እነሱ እንዲወስኑ እድሉን ስጣቸው አሉኝ።
አንዳንድ ነገር ካወራን ቡሀላ ውሳኔ ላይ ሲደርሱ ደውለው እንዲያሳውቁኝ ነግሪያቸው ስልኩ ተዘጋ።
አቶ ሳሙኤል ውሎዬ እንዴት እንደነበር ስራ እንዴት እየሄደልኝ እንደሆነ ያለውን ነገር እንደ አባት ከጠየቁኝ ቡሀላ
ገብቼ ተኛሁ ።
አንዳንዴ ጭንቅላታችን ሀሳብ በዝቶበት ይሁን ብቻ እኔጃ ግን የትኛውን ነገር ማሰብ እንዳለባችሁ እራሱ ግራ ገብቷችሁ አያውቅም በቃ ለማሰብ ሞክሬ ግን ማሰብ በራሱ ከበደኝ
በነጋታው ማሂ ሳትቀሰቅሰኝ ቀድማ ወደስራዋ ሄደች አቶ ሳሙኤል ቁርስ እየጠበቁኝ ነበር በሰላም ነው ማሂ በጠዋት የወጣችው አልኳቸው።
አዎ ልጄ ስራ ቦታ ሚጠብቁኝ ሰዎች አሉ ለነሱ ቶሎ እቃ መስጠት አለብኝ ብላ በጠዋት ነው የወጣችው አሉኝ።
ቁርስ በላልተን ስንጨርስ ልብሴን ቀያይሬ ወጣሁ።
ልክ ከቤት እንደወጣሁ ደወልኩላት አታነሳም ደሞ በምን አኩርፋ ይሆን ይቺ ልጅኮ ጤነኛ አደለችም እያልኩ ወደ ስራዬ ሄድኩ ቀኑን ሙሉ በስራ ተወጥሬ ነበር ስራውን እየለመድኩት ስመጣ መኪና እየፈታሁ የውስጡን ነገር ደሞ እነሱ እንዲጨርሱት ለባለሙያ መስጠት ጀመሪያለሁ 3000 የተቀበልኩትን እቃ ለነሱ ከ7እስከ 8 ሺ እሸጥላቸዋለሁ ።
የዛን ቀን እስከ 11 ሰአት ድረስ አንድ መኪና አስቸግሮን እሱን ለመጨረስ ስንለፋ ነበር ።
11 ሰአት ላይ ማሂጋ ልሂድና በዛው ምሳ እንበላለን አብረን ወደቤት እንመለሳለን ብዬ ሱቋ ሄድኩ።
ብታይ እንዴት እንደራበኝ ጠዋት ደሞ ምንድነው ስልክ ማታነሺው ለማንኛውም ነይ በቃ አብረን ምሳ እንብላ አልኳት።
አይ በልቻለሁ አንተ ብላ አለችኝ ፊቷን እንደቋጠረችው።
ማለት ሳትደውይልኝ በላሽ ምን ሆነሽ ነው አልኳት ሁኔታዋ ግራ አጋብቶኝ።
ምንም አልሆንኩም አንተ ወደህይወቴ ሳትመጣ በፊትምኮ ብቻዬን ነበር ምበላው አለችኝ ተኮሳትራ።
ነገሮችን ለማብረድና ለመሳቅ እየሞከርኩ በናትሽ ቀኑን ሙሉ ከመኪናጋ ስታገል ውዬ በጣምም ደክሞኛል አሁን ደሞ ያንቺን ኩርፍታ መቋቋም አልችልም አትጃጃይ በናትሽ አላሳዝንሽም እንዴ አልኳት።
ምንም አልመሰላትም ነበር ንግግሬ
እኔ ምን አልኩህ በልቻለሁ አልበላም ነውኮ ያልኩት አለችኝ ጭራሽ እንደመቆጣትም እያደረጋት ነበር።
እሺ ብያት ሱቁን ትቼ ወጣሁና ወደቤት ሄድኩ እውነት ለመናገር taxi ውስጥ እንባ እየተናነቀኝ ከራሴጋ ላለማልቀስ እየታገልኩ ነበር ሰፈር የደረስኩት።
ከtaxi ከወረድኩ ቡሀላ በእግሬ እየተራመድኩ ብዙ ነገር ማሰብ ጀመርኩ ማሂ ከመጠን በላይ አናዳኛለች ለምን እንደዚህ እንደምትሆን ፈጣሪ ይወቀው ግን ይሄ ኩርፍታ ሚባል ነገር በጣም ነው አብሮን ያለን ሰው የሚጎዳው።
ቤት ስገባ አቶ ሳሙኤልም ቤት አልነበሩም ደወልኩላቸው
ወደድርጅታቸው ሄደው እዛው ከስራ ባልደረቦቻቸውጋ እራት ለመብላት እንደወጡና እዛው እንደሚያመሹ ነገሩኝ
ምግቤን በላላሁና ቁጭ አልኩኝ ሲደብረኝ እህቴጋ ደወልኩና እረጅም ሰአት አወራን ከሷጋ ስጨርስ ከናትና አባቴጋ አወራሁ አባቴ በዛውም ግቢውን በባለሙያ እያስገመተው እንደሆነና አሪፍ ገንዘብ እንደሚያወጣ ነገረኝ
በዛውም እኔ እዚህ ያለውን የቦታ ሁኔታ በደንብ አጥንቼ እንድነግረውም ጨምሮ ነገረኝና ስልኩ ተዘጋ።
ብዙም ሳይቆይ ማሂ መጣች ነገ የታዘዙ እቃዎች አሉ እና በሚመችህ ሰአት መጥተህ አድርሳቸው አለችኝ።
ሰራተኛዋ መጥታ እራት ላቅርብልሽ እንዴ ብላ ጠየቀቻት አይ በልቼ ነው የመጣሁት ደክሞኛል ልተኛ ነው ብላ ወደክፍሏ ገባች።
ሁኔታዋ በጣም አናደደኝ በፍጥነት መኝታ ቤት ገብቼ አልጋው ላይ ተዘረርኩ ትራሱን አፌ ላይ አፍኜ ለመጮህ ሞከርኩ ወደውስጥ እንጂ ወደ ውጪ መጮህ አልቻልኩም ነበር።
ምን አስቀይሚያት እንደሆነ ለማሰብ በሞከርኩ ቁጥር እንባዬ ይፈሳል ለቅሶዬን ዋጥጥ ለማድረግ ብሞክርም አቃተኝ
የበታችነት የባዶነት ስሜት ተሰማኝ።
በነጋታውም እኔ ከመነሳቴ በፊት ቀድማኝ ወጥታ ነበር።
በቃ ጥሩ እኔ ማንንም መለመን የለብኝም ስራዬን ልሰራራና ወደ ቤተሰቦቼ እመለሳለሁ
ተቀብያት ከሱቁ ወጣሁ እቃዎቼን አደራርሼ ስመለስ የእቃውን ብር ለሷ ሰጠኋት የራሴን ትርፍ ደሞ እራሴጋ አስቀረሁት ።
ማታ ቤት ስገባ ለአቶ ሳሙኤል በደንብ ሰላምታ ካቀረብኩ ቡሀላ ዛሬ በጣም እንደደከመኝ እራትም በልቼ እንደመጣሁ መተኛት እንደምፈልግ ነግሪያቸው ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ
ይቀጥላል....
✎ክፍል 28 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️ ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333