ፅጌሬዳ
ክፍል 29
ለሌሊት 11 ሰአት የሞላሁት አላርም ቀሰቀሰኝና ተነሳሁ ልብሴን ለባብሼ ማንም ሳያየኝ ከግቢ ለመውጣት ሹክክ እያልኩ ስራመድ አቶ ሳሙኤል እታችኛው ሳሎን ሱፋቸውን ዝንጥ ብለው እንደለበሱ ቁጭ ብለዋል።
ሳያቸው ልክ መልአከ ሞት ከፊት ለፊቴ የተቀመጠ እንጂ እነዚያ ደጉ ሰውዬ አቶ ሳሙኤል የተቀመጡ አይመስልም ነበር።
እእእእእ አቶ እእ ሳሙኤል ምነው በሰላም ነው ምነው አልኳቸው።
ተው እንጂ ልጄ ቢያንስ ሳልሸኝህ ሰላም ግባ ሳልልህ ዝም ብለህ ብትሄድ ላንተስ ህሊናህ ያርፍልሀል አሉኝ ።
አይ እኔኮ እንዳልረብሾት ብዬ ነው እንጂ ሌላ አደለም ደሞ እመለስ የለ እንዴ አልኳቸው ጥሩ ለማንኛውም እኔ ነኝ ቤተሰቦችህጋ ማደርስህ አሉኝ።
አኔ አይሆንም ሞቼ እገኛለሁ ብቻዬን እሄዳለሁ አልኩኝ እሳቸው እየተቆጡ አይ እንግዲህ አንዴ ተናገርኩ ተከተለኝ ብለው ወደመኪናቸው ገባንና ጉዞ ጀመርን።
ግን ድንገት እንድትወስን ያደረገህ ምንድነው አሉኝ።
አረ ድንገትኮ አደለም ያው ቤተሰቦቼም ትንሽ ሰሞኑን ተጨንቀዋል ከስልክ በላይ ደግሞ በአካል ሄጄ ብንወያይ መልካም ነው ብዬ አስቤ ነው አልኳቸው
ጥሩ ከቤተሰቦችህጋ ለማውራት ብለህ እንጂ ከማሂጋ ተጣልታችሁ ምናምን አደለም ማለት ነው አሉኝ።
አፌ ተሳስሮ ዝም አልኩኝ።
ልጄ እኔ አባት ነኝ ከአባትነቴም በላይ ህይወት ብዙ ነገሮችን አስተምራኛለች ከዛ ውስጥ ሰዎችን በዝምታ መረዳት ነው።
ሳላወራ ሳለፈልፍ ቀደም ቀደም ሳልል ዝም ብዬ ሰዎችን መረዳት በዝምታዬ ውስጥም ለሰዎች መዳኒት መሆንን እፈልጋለሁ።
አንተና ማሂ እንደተጣላችሁ ማወቅ ለኔ ያን ያህል ከባድ አደለም ያንተም ሀዋሳ መሄድ ጥሩ ነው ምናልባት ትንሽ ስትራራቁ የልጅነት ፀባያችሁ ይለቃችሁና እንደትለቅ ማሰብ ትጀምሩ ይሆናል።
እኔ ማሂን አቃታለሁ በጣም ጎበዝ ጠንካራ ትግስተኛ ሁሉንም ሰው መረዳት ምትችል ልበ ሩህሩህ ሁሌም ቢሆን ከራሷ ጥቅም ሰዎችን ምታስቀድም ሴት ናት ።
ግን ትልቁ የማሂ ድክመት በጣም የቀረበችው የራሴ ነው ብላ ያሰበችው ሰው ከሆነ እዛ ሰው ላይ ነፃነቷን ማወጅ ትፈልጋለች እንደህፃን መቅበት መሞላቀቅ ያምራታል ያንን ደሞ ሰው አይረዳትም
አንተንም ጨምሮ እንዳልተረዳሀት ነው የገባኝ አሉኝ።
አረ እንደዛ አደለም እኔኮ በጣም ተረድቻታለሀ ብታኮርፈኝም እችላታለሁ ድንገት ተነስታ ቅይር ትልብኛለች ትናደድብኛለች እኔ ግን እንደምንም ዋጥ እያደረኩት ለመቻል እሞክራለሀ አሁን ግን ጭራሽ የምር አኮረፈችኝ ሃናግራት ብሞክርም አልሰማ አለችኝ ቆይ የኔ ጥፋት ምኑ ላይ ነው።
እኔኮ ምንም ብታደርገኝ ብትገለኝ ሁላ አልቀየማትም ውስጧን አቀዋለሁ ክፋት የለባትም በሰዎች ላይ ተንኮል ምቀኝነት ሚለውን ነገር አታስብምኮ ግን በቃ ብቻ እኔ አሁንም እንደተጣላን አይሰማኝም ለጊዜው ከአይኗ ሰወር ልበል ብዬ የው እንጂ አልኳቸው።
ጥሩ አደርግ ነገሮችን ለማብረድ መሞከርህን ሳላደንቅልህ አላልፍም ግን አደራ እንዳትቀየማት እሺ እኔም ዛሬ እንደምትሄድ አልነገርኳትም እራሳችሁ ጨርሱ እኔ ጣልቃ ከምገባባችሁ አሉኝ።
በጣም አመሰግናለሁ ድሮ ልጅ እያለሁ የሌሎችን አባት አይቼ የኔን አባት ሳይ እዚህ ምድር ላይ ተከብሮ ሚያስከብር ለልጆቹ ሟች ቁም ነገረኛ አባት ያለው የኔ አባት ብቻ ይመስለኝ ነበር እርሶን ካየሁ ቡሀላ ግን ትክክል እንዳልነበርኩ ተረዳሁ ማሂ እናቷን ባታቃትም እርሶን የመሰለ ከናትም ከአባትም ከጓደኛ ከእህትና ከወንድም የበለጠ ሁሉን ያሟላ አባት ስላላት እድለኛ ናት እርሶ እስካሉላት ድረስ የትኛውም ጉድለቷ ክፍተቷ ይታያታል ብዬ አላስብም።
ብቻ የአባትና የልጅ ወግ ይዘን የልብ የልባችንን እያወራን ስለቤቱም እያወጋን አዲስ አበባ ያሉትን የቤቶች ዋጋ እየነገሩኝ መንገዳችንን ቀጠልን።
ወደ ሁለት ሰአት አካባቢ ላይ ማሂ ደወለችና አባቴ የት ሄደህ ነው ሳትነግረኝ አለቻቸው።
ይቅርታ ልጄ ሰላም እንዳልነሳሽ ብዬ ነው ወደ ሀዋሳ ሄጃለሁ አሏት።
ምን ጮኸች ሳትነግረኝ ወደሀዋሳ ሄድክ አባዬ እኔ አላምንም ቆይ ምን ልትሰራ ነው የሄድከው አለች?
ትንሽ ጉዳይ አለችኝ እመለሳለሁኮ የኔ ልጅ አሏት ።
እሺ በቃ መልካም ቀን ዛሬ አብረን እንውላለን ብዬ አስቤ ነበር በቃ ችግር የለውም አለቻቸውና ስልኩ ተቋረጠ።
ሀዋሳ ከደረስን ቡሀላ ማሂ ደግማ ደወለች አባዬ ከማንጋ ነው የሄድከው አለች።
ምነው ልጄ ለምን ጠየቅሽኝ አሏት??
ንገረኝ ከማንጋ ነው አብራችሁ ነው እንዴ የሄዳችሁት አለች ስፒከር ላይ ስለነበር ድምጿን በደንብ እየሰማሁት ነበር።
አዎ የኔ ልጅ አድርሼው ልመለስ ብዬኮ ነው አሏት።
እውነት ይሄን ካንተ አልጠብቅም በፈጣሪ ስም እኔን በመሀል ቤት አገለላችሁኝ ማለት ነው እሱ ወደ ሀዋሳ ሲሄድ እኔ አላውቅም እእእ ቆይ እኔ ለሱ ይሄን ያህል ጨካኝ ነኝ ለነገሩ አንተ አባቴ ያለነገርከኝን እሱ እንዲነግረኝ መጠበቄ ነው የኔ ጥፋት ቻው አንዳችሁም እንዳትደውሉልኝ በጣም ነው ያዘንኩብህ ብላ ስልኩን ዘጋችው።
አየህ አደል ማሂ እንደዚህ ናት ይሄኔ መጣላታችሁንም እረስታው ይሆናልኮ አሉኝ።
እያወራን ወደቤት ገባን ቤት ሁሉም ተሰብስበው እየጠበቁን ነበር የእህቴ ባል ቤተሰቦች ሳይቀሩ መጥተው ነበር።
ሁሉንም በየተራ ሰላም ብዬ ተቀመጥኩኝ ከናቴ አጠገብ እቅፍ አድርጋ እያሻሸሸችኝ አይን አይኔን እያየችኝ ቁጭ አለች ወደራሷ ጥብቅ አድርጋ አስጠጋችኝና እኔኮ በህልሜ በህልሜ እየመሰለኝ ነው።
የሆነ ሰአት ተነሽ ነግቷል የሚሉኝ እየመሰለኝም እሳቀቃለሁ ብላ ግንባሬን ሳም አደረገችኝ ቡናው ተፈላ ቤቱ በእጣን ጭስ ደመቀ ሁሉም ሳቅ ጨዋታውን አደራው።
አባቴ ከነግርማ ሞገሱ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ከአቶ ሳሙኤልጋ የልብ የልባቸውን ያወጋሉ
እኔም ከናቴ አጠገብ ተነሳሁና ወደ እህቴ ባልጋ ሄድኩኝ። አጠገቡ ቁጭ ብዬ እንደወጣት እንደጓደኛ አወራሁት ስለትዳራቸው ጠየኩት በአግባቡ አጫወተኝ ቀለል ያለ ምርጥ ልጅ ነው ብዙ ማውራት እንደማይወድ ከሁኔታው ያስታውቃል ።
ምሳችንን በላልተን ቡናችንን ከጠጣጣን ቡሀላ አቶ ሳሙኤልና አባቴ እስቲ አንዳንድ ነገሮችን አየት አየት አድርገን እንምጣ አሉና ከቤት ወጡ።
✎ክፍል 30 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️ ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333