ፅጌሬዳ
ክፍል 37
እሺ አልናቸው አባቴ እስከውጪ ሸኛቸውና ተመለሰ።
እኔና እህቴ ማሂ ቀኑን ሙሉ ተኝታ ስትውል እንዳይደብራት ምን እንደምናደርግ እያወራን ነበር።
ቀስ ብለን አሰብንና ፊልም መረጥን እሱን አይተን ስንጨርስ ዘፈን በረጅሙ ከፍተን በየተራ እያስመሰሉ መዝፈን ጀመርን።
ማሂ ፍርስ እያለች ትስቃለች እኛ በሷ ሳቅ ውስጥ እራሳችንን እየሳቅን እናገኘዋለን።
ቀኑን ሙሉ ስንበላ ስናዝናናት ዋልን ማታ አቶ ሳሙኤል አመሻለሁ ግን እየመጣሁ ነው ብለው ደወሉልን።
ብዙም ሳይቆይ የህቴ ባል ከስራ እኛጋ መጣ በእጁ ያንጠለጠለውን ፍራፍሬ ለእህቴ ሰጣትና አስተካክይውን አንጭው እየተጫወትን እንበላዋለን አላት።
እሺ ብላ ተቀብላው ሄደች።
እውነት ለመናገር ትዳራቸውን ሳየው ያስቀናኛል። እህቴ ማታ መሽቶ ሲመጣ እንዴት በደስታ ፊቷ ፍክት እንደሚል ቃል የለኝም እሱም ቢሆን መጀመሪያ እንደገባ እሷን አቅፎ ለመሳም ነው ሚቸኩለው።
ዝም ብዬ ሳያቸው መንፈሳዊ ቅናት ያድርብኛል ውይይይይ ግን ታድለው እሷም የመጀመሪያዋ እሱም የመጀመሪያው በቃ ሌላ አታውቅ እሱም ሌላ አያውቅ ፈጣሪ ፈቀደላቸው ተጣመሩ እየተዋደዱ ደሞ አብረው ያረጃሉ እላለሁ::
እየመሸ ሲሄድ እህቴና ባሏ እራታቸውን በልተው ወደቤታቸው ሄዱ እኛ አቶ ሳሙኤልን መጠበቅ ጀመረን።
ወደ ሶስት ሰአት አካባቢ አቶ ሳሙኤል ቤት ደረሱ መኪና ሙሉ እቃ ሰው እንዴት ተሸክሞ ይመጣል።
አባቴ አየና በጣም ተቆጣ እኛ ለአንድ ልጅህ እንዳናንስ ነው ይሄን ሁላ ያመጣኸው ወይስ ደሞ እኛ የለንም ቸገረን አልንህ ብሎ ፊቱ ቅይር አለ እናቴም ብቶን ደስተኛ አልነበረች።
ይሉኝታ አስያዝከን አንተ ለኛ ልጅ ስንት ነገር አድርገህ ከነ ሙሉ ጤንነቱ አስረክበኸን እኛ ለማሂ እንዳናንስ ነው አለች።
አቶ ሳሙኤል ቆጣ ብለው ይልቁን እቃውን በማስገባት አግዙኝ ከተማዋን ስዞራት ነው የዋልኩት ገና ቆማችሁ እኔን እየተቆጣችሁ ነው አሏቸው ና አብረው እቃውን ማስገባት ጀመሩ ።
እኔ እንደቤት እመቤት ከማሂጋ ቁጭ ብዬ እያወራሁ እነሱን ማየት ጀመርኩ።
ሲጨርሱ እራት ቀርቦ በላን ሁላችንም ወደመኝታችን ሄድን።
በነጋታው አቶ ሳሙኤል ቤት ነበር የዋሉት እንደተለመደው እህቴም በጠዋት መጣችና ልብሷን ቀያይራ ፀጉሯን አሲያዘችላት።
ከቁርስ ቡሀላ ማሂን ወክ እንድታደርግ ተራ በተራ ሳሎን ላይ አመላለስናት።
እጇ ከአንገቷጋ እንደታሰረ ከደረቷ ላይ ስለማይንቀሳቀስ በጣም ምቾት ነስቷት ነበር።
እኛ ትንሽ ለወገቧ እንዲጠቅማት ነበር ወክ እንድታደርግ ስናግዛት የነበረው ።
ለሳምንት በዚህ ሁኔታ ቀጠልን።
እህቴ ቀድማ ልብስ ስለምታጥብ እኛጋ ማታ እንደምትመጣ ነግራን ነበር አቶ ሳሙኤልም ቢሆኑ አዲስ አበባ እንደሄዱ እዛው ነበር ያደሩት።
በጠዋት ተነስታ ቁርስ ሰራርታ እናቴ ወደቤተክርስቲያን ሄዳለች ተኝተን ምንቆይ መስሏት እስክንነሳ ነበር የሄደችው።
ማሂ ቀድማኝ ተነሳችና ደወለችልኝ ና እየጠበኩህ ነው አለችኝ ሄድኩ።
በናትህ ልብስ መቀየር ፈልጌ ነበር አግዘኝ ዛሬ ቀኔን በጠዋቱ ደመቅ ማድረግ እፈልጋለሁ አባቴም ሲመጣ ቆንጆ ሆኜ ልጠብቀው አለችኝ።
ግንባሬን ቋጠር እያረኩ ማለት እኔ እንዴት ላግዝሽ አልኳት??
ልብስ እንድለብስ ነዋ ልብስ ምረጥልኝና አውጣልኝ ከዛ አግዘኝ እንድቀይር አለችኝ።
አንቺ ያምሻል እንዴ እናቴ እስክትመጣ ጠብቂ እንጂ እኔ እንዴት ነው ማግዝሽ ባይሆን እስከዛ ፀጉርሽን ላሲዝልሽ አልኳት ወደሷ እየተጠጋሁ።
ተወው እሺ ልብስ አውጣና ስጠኝ ለራሴ አለችኝ።
ሙሉ ቀሚስ አውጥቼ ሰጠኋት ።
ግዴታ ልብሱን ለመልበስና የለበሰችውን ለማውለቅ እጇ መፈታት አለበት ፈታሁላት ያማታል ብዬ ከመፍራቴ የተነሳ እጄ እየተንቀጠቀጠ ነበር።
እሺ አሁን እንዴት ልቀይርልሽ መቼስ በቢጃማሽ ላይ አልደርበው ወይ ደሞ እራቁትሽን አላደርግሽ አልኳት።
በቃ ተወው አልኩህኮ እጄን ከፈታህልኝ እራሴ ጨርሰዋለሁ ፊትህን አዙር ወይ ውጣ አለችኝ።
ፊቴን አዙሬ ቆምኩ።
ልብሷ እጇን ሲነካባት ምታወጣው የሲቃይ ድምፅ መቋቋም ከምችለው በላይ ነበር።
ከሷ በላይ ህመሙ እኔን ተሰማኝ አስሬ ጨረሽ ልዙር ጨረሽ ልዙር እያልኳት ቆምኩኝ።
በመጨረሻም እሺ እጄን እሰርልኝ በቃ አለችኝ።
እሺ ብዬ እጇን ማሰር ጀመርኩ ህመሙ እየባሰባት ነበር ።
እሺ ምን ላድርግልሽ እንዲሻልሽ አልኳት ልብሶቿን እያስተካከልኩ ።
እኔጃ እኔ ግን ይሄንን ነገር መልመድ ምችል አይመስለኝም እጄን ቶሎ ካልተሻለኝ የማብድ ነው ሚመስለኝ አለች እያለቀሰች።
ወደደረቴ ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳትና ይሄኮ ያልፋል ለትንሽ ጊዜ ነው ማሂ ወላለማቸውንስ እንደዚህ የሚኖሩ አሉ አደል ።
እእ እጅና እግርምኮ ሳይኖራቸው ደስተኛ ህይወት የሚኖሩ ጥቂት አደሉም አንቺ ለቀናቶች እንዴት ይከብድሻል አልኳት።
እሱስ ልክ ነህ አለች በግራ እጇ እንባዋን እየጠረገች።
ድንገት ትኩር ብዬ አየኋት
ምነው ለምንድነው እንዲህ ምታየኝ አለችኝ እንደማፈር እያለች።
ለምን እንደሆነ አላውቅም ግን ሁሌ ሳይሽ ታሳዝኝኛለሽ አልኳት።
ምኔ ነው ሚያሳዝንህ አንተ ማትረባ አለችኝ።
እኔጃ ማሂ አላቅም ግን ፊትሽን ሳየው ድምፅሽን ስሰማው ልቤ ውስጥ የሀዘኔታ ስሜት ይሰማኛል አልኳት።
ፈገግ አለችና ልብህ ውስጥ ያለው ምናልባት ሀዘኔታ ሳይሆን ፍቅር ይሆናል እስቲ የዛኔ ሆስፒታል የገባሁ ጊዜ ምን ተሰማህ አለችኝ???
አረ ማሂ ላብድ ነበር ፈጣሪን ባንቺ ቦታ እኔን እንዲያደርገኝ ስለምነው ነበር ብታይ በቃ ካንቺጋ ህይወቴ ሁላ ያበቃለት ነው የመሰለኝ።
ከፈጣሪጋ ሁሉ ግብ ግብ ፈጥሪያለሁኮ እሱ ይቅር ይበለኝ እንጂ አልኳት።
ታዲያ ይሄንን ስሜት ምን ትለዋለህ አለች ወደኔ ቀረብ አይኔን እያየች።
ምናልባት አንቺ እንዳልሽው ፍቅር ሊሆን ይችላል ብዬ ከንፈሯን እራሴው ግጥም አድርጌ ሳምኳት በተራዋ እሷ ሳመችኝ ተራዬን ጠብቄ ደገምኳት።
የእናቴን ድምፅ ስሰማው እንዴት ተስፈንጥሬ ተነስቼ እንደወጣሁ ሳላውቅ ከክፍሉ ወጣሁ ወደኋላ ዞሬ ለማየት ድፍረቱን እስካጣ ነበር የደነገጥኩት።