ፅጌሬዳ
ክፍል 41
አባቴ ጠጋ አለና መተቃቀፉን ትደርሱበታላችሁ ለጊዜው እንግዶቻችሁን ብታስተናግዱ ምን ይመስላችኋል አለን።
ተላቀቅንና እጇን ይዤ ፊት ለፊቱ ወንበር ላይ ከጎኔ ቁጭ አደረኳትና እናቴን ሄጄ አቀፍኳት።
የባሰ እንባዋን ለቀቀችው አይ የኔ ልጅ ያ ሁሉ የእንባ ዘመኔ አልፎ ዛሬ አንተን እዚህ ቦታ ቆመህ ማየቴን ሳስበውኮ ህልም እየመሰለኝ ነው አለችኘ ።
እናቴ እኔምኮ እውነት አልመስልህ ብሎኛል ግን በቃ ዛሬ ደስታችን ፈጣሪ ቸር አደል የልባችንን ክፋት ሳያይ ለዚህ ቀን አበቃኝ እሱ የተመሰገነ ይሁን ቁጭ በይ በቃ አልኳትና ወዳባቴ ሄድኩ።
ያ ግርማ ሞገስ በተሞላ ድምፁ የሚያምር የአባትነት ፈገግታን እየለገሰኝ መቼስ አባት በአደባባይ አያለቅስም ብዬ ነው እንባዬን ዋጥጥ ያደረኩት ልጄ አኮራኸኝ ክብሬን ደግመህ ደግመህ መለስክልኝ ፍሬያችሁን ለማየት ያብቃኝ ብሎ ጥብቅ አድርጎ አቀፈኝ።
ሁሉንም በየተራ አቅፌ ደስታዬን ከተጋሩኝ ቡሀላ ቁጭ አልን ።
በቃ አሁን ደሞ ወደ መዝናናቱ እንሂድ ደስታችንን እናክብር አለ አባቴ።
አይይይ ቆይ እሱን አንድ ላይ ነው ምናከብረው ገና የኔን ስጦታ መች አያችሁትና ነው አሉ አቶ ሳሙኤል።
ሁሉም ምን እንደሆነ ለማወቅ እንደጓጓ ግልፅ ነው።
ማሂ ግራ ገብቷት ምንድነው አባቴ እኔ ከዚህ በላይ ደስታን መቋቋም አልችልም በደስታ ብዛት እሞትብሀለሁ ያንተን ለሌላ ቀን አቆይልኝ አለችው።
አይ ኑ እኔን ተከተሉኝ ብለው ወደፊት ሄዱ እጇን ይዣት ተከተልናቸው ሌሎቹም ከኛ እኩል ምን እንደሆነ ለማየት ጓጉተው ተከተሉን።
ማሂ ወዴት እንዳልሄድ ፈርታ እንደሆነ አላቅም አጥንቴ እስኪሰባበር አጠብቃ ያዘችኝ ብል እራሱ ማጋነን አይሆንብኝም
እናንተ ሰዎች ሰው በደስታ ብዛት አይሞትም ብላችሁ ነው አደል ዛሬ በኔ ይጀመርና ጉድ እንዳትሆኑ ብላ ከት ብላ ሳቀች
ወዲያው አቶ ሳሙኤል ፊታቸውን ወደኛ አዞሩና አሁን አይንሽን ጨፍኚ አሏት።
ጨፈነች የመኪና ቁልፍ ከኪሳቸው አወጡ ዙሪያዋን የተሞሸረች እንኳን ለመንዳት ለማየት የምታሳሳ መኪና ከፊት ለፊቷ ቆማለች ሁሉም ልክ መኪናውን ሲያዩ ማሂ አይኗን ከመግለጧ በፊት በጩኸትና ጭብጨባ አንባረቁት ደንግጣ አይኗን ገለጠች ።
ሰው ለካ ደስታ ሲበዛበት ሰውነቱን ማዘዝ ይከብደዋል ማሂ ለመጮኸም ለመደሰትም አቅም አጣች እንዲሁ በቆመችበት እንባዋን ዝርግፍ አደረገችው የአባቷ ደረት ላይ ልጥፍ አለችና አባቴ አመሰግናለሁ የኔ ጀግና በቃ ከዚህ ውጪ ደስታዋን በእንባ ነበር የገለፀችው።
እውነት ለመናገር ጉዳዩ ለኔም እንግዳ ነበር ከሷ እኩል ነው ሰርፕራይዝ የሆንኩት።
ማሂ ቃላት እንዳጠሯት ግልፅ ነበር የመኪና ቁልፉን ተቀበለችና ለመመረቅ ወደ ውስጥ ገባች መንዳት ግን አልቻለችም እጇ እየተንቀጠቀጠ አልታዘዝ አላት ተመልሳ ወረደችና በድጋሜ አባቷን ጥብቅ አድርጋ አቀፈቻቸው ።
ብቻ ምሽቱ የማሂ ነበር ።
ቁጭ ብለን አይኗን ከቀለበቱ ላይ ሳትነቅል እጇን አቅፋ እንደተቀመጠች መሸላት
ፕሮግራሙ ሲጠናቀቅ ሁላችንም ወደቤት አመራን ማሂም መኪናዋን እየነዳች ለሁለት መኪና ተከፍለን ወደ ቤት ሄድን።
ቤት ስንደርስ ዛሬማ ከዚህ ሁላ ደስታ በቀላሉ መውጣት አልፈልግም ሌሊት እያወራን እየተዝናናን ነው ማንጋት ያለብን አለ አባቴ።
ሁላችንም ተስማማን ቤቱን ሌላ ድባብ ውስጥ አስገባነው ሁላችንንም ደስታ አስክሮን ነበር ።
በመሀል አቶ ሳሙኤል ጨዋታ አነሱ በቃ ከዛሬ ጀምሮ እናንተ ባልና ሚስት ናችሁ መፈራረም ብቻ በቂ ነው እርግጠኛ ነኝ ልጄ በድጋሜ ሰርግ እንዲደገስ ምትፈልግ አይመስለኝም ባይሆን የመጀመሪያ ልጃችሁን ውለዱና ክርስታናውን እንደሰርግ አድርጋችሁ መደገስ ትችላላችሁ አይመስላችሁም አሉ።
አባቴ ቆጣ ብሎ ኦኦኦ እንደዚህማ አይሆንም እኔ ሀዋሳ ላይ ታይቶ የማይታወቅ ሰርግ ነው ምደግስላቸው የመጀመሪያ ልጄማ እንዲሁ በቀለበት ማሰር ብቻ ጋብቻ አይመሰርትም ወዳጄ ሳሙኤል አንተንም እረዳሀለሁ ግን ሀዋሳ ላይ መሆን ይችላል ሰርጉ ትልቁ ግን የናንተ ውሳኔ ነው ልጆች እናንተ ምን እያሰባችሁ ነው አለን።
እኔ :- ሰርጉ ትንሽ ይቆያል አሁን አይደገስም እንጂ መደገሱን አልጠላም ግን አሁን እኔም አራሴን በስራ ማጠነክርበት አባቴ አንተም ወደቀድሞ ገቢህ ምትመለስበትን እድል ምታመቻችበት ሰአት ነው አልኩት።
ማሂ ቀበል አለችኝና እኔም በሱ ሀሳብ እስማማለሁ ልክ ነው የፎቶ ፕሮግራምና ቀለል ያለ ድግስ ቢኖረን ባይ ነኝ እሱ እንዳለው ትንሽ ቆየት ብሎ መሆን ይችላል አለች።
ሁሉም በሀሳባችን ተስማሙና ምሽቱ ያማረና የደመቀ ሆኖ አለፈ::
ከቀለበቱ ቡሀላ እኔ ከቤተሰቦቼጋ ወደ ሀዋሳ ተመለስኩና ለትምህርት ማስረጃነት የቀረኝን 1 file ይዤ መጣሁ።
ስራዬን አጣጡፌ መስራት ጀመርኩ ከአቶ ሳሙኤልጋ ስራ ቡታ ጅንን ያልኩ የስራ ባልደረባቸው ከስራ ውጪ ጓደኛቸው አማካሪያቸው እቤት ውስጥ ደሞ ልጃቸውና የልጃቸው ባል ሆኜ ህይወታችን ቀጠለ ።
ከማሂጋ እኔና አባቴ እንተኛበት የነበረውን ክፍል ለራሳችን ወስደን የሁለታችን ክፍል አደረግነው።
ማሂም ከስራዋ ጎን ለጎን ስለጎዳና ልጆች የሚያጠነጥነውን መፅሀፏን ፅፋ አጠናቀቀች ።
እኔም ገና ትምህርቱን ተምሬ ሳልጨርስ የድርጅቱን ስራ ጥንቅቅ አድርጌ አወኩት ማለት እችላለሁ ነገሮችን የመያዝ የመረዳት ችግር ስለሌለብኝ ለኔ ከባድ አልነበረም።
እህቴም የራሷን ሽፎን ቤት ከፍታ መስራት ጀምራለች።
አባቴ ወደቀድሞ ስራው ገቢው ተመልሷል እንኳን ለቤተሰቡ ለሰውም መትረፍ ሚችለውን አባቴን መልሼ አግኝቼዋለሁ።
ሰርጋችን ከ2 ወር ቡሀላ ሀዋሳ ላይ ይደገሳል ምክንያቱም ማሂ እርጉዝ ናት።
ምዕራፍ 1
ተ
ፈ
ፀ
መ
በቀጣዩ ምእራፍ እንገናኛለን
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333