🔸🔸🔺🔺🔹🔸
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ ማኔ
ክፍል 2️⃣5️⃣
ይዟት ወጣ ቀድም እሱ ዘለለ በዚህ በኩል እኔን እረግጣ ዘለለችና ወደቤቷ ገባች።
በዛ መሀል ልእልት ምን እያሳለፈች እንደሆነ ቤት ምን እንደጠበቃት ከምን አይነት ችግርO እንዳጋፈጥኳት ማሰብ ከብዶኝ እራሴን በጭስ ውስጥ ለመደበቅ ዝም ብዬ ያለማቋረጥ ማጨስ ጀመርኩ።
ከልእልት ችግር በላይ ደሞ የእዮብ ዝምታ ይበልጥ አስፈራኝ።
እስከማታ በጭንቀት ውስጥ ምንም ሳናወራ አሳለፍን ማታ ላይ እዮብ አጠገቤ መጥቶ ቁጭአለና ታቃለህ ፈጣሪ እዚህ ምድር ላይ ብዙ ነገሮችኝ ውብ አድርጎ ፈጥሯል ከዛም ውስጥ በጣም ውቡ ፍቅር ነው ግን ፍቅር ሚዋበው ላደለው ሰው ብቻ ነው።
ፍቅር ላንዳንዱ ህይወትን ይሰጣል ላንዳንዱ ደሞ ህይወትን ይነጥቃል፡፡
ባህራን እኔ በምወደው አባቴ እምልልሀለሁ ልእልትን ከልቤ ነው ማፈቅራት አይቼ አልጠግባትም የዋህነቷ ፍቅሯ የውስጧ ንፅህና እኔጃ ሰው እንደሷ ሚፈጠርእራሱ አይመስለኝም ግን ስላፈቀርኳት ስለወደድኳት ወዳንተ እንድትቀርብ መንገዱን አመቻቸሁ ምክንያቱም እኔ እራስ ወዳድ አደለሁም ይቺን የመሰለች ልጅ ከኔ ከሱስኛና ህይወቱ ካበቃ ቦርኮጋ እንድትሆን ማደርጋት እኔ እራስ ወዳድ አደለሁም
አንተን ስላመንኩህ ከልብህ ሰው ነህ ብዬ ስላሰብኩ ነው ትናት ሁለታችሁ እንድትገናኙ እኔ ወጥቼ የሄድኩት ግን አንተ ይቺን ንፁህ ልጅ ፍቅሯን መቀማትል ሳያንስ ክብሯን ገፈፍካት አሁን ሳትፈልግ በግድህ አብረሀት ትሆናለህ አለኝ አነጋገሩ ይበልጥ አናደደኝ። ደፍሪያት አደለምኮ የሰራሁት ነገር ልክ አደለም ግን ማንም ሰው ሳልፈልግ አብሪያት እንድሆን አያስገድደኝም አልኩት።
እዮብ ተናዶ ትቶኝ ወጣ እኔ ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ በጭንቀት ለመፈንዳት ምንም አልቀረኝም፡፡
የመጨረሻ ደረጃ ላይ ስደረስ ቤቱን ትቼ ወጣሁ እዮብ ሊኖርበት ይችላል ብዬ ያሰብኩት ቦታ ምንም አልቀረኝም ላገኘው አልቻልኩም፡፡
ማታ አምስት ሰአት አካባቢ ምንተኛበት ወደነበረው ቤት ሄድኩ የለም ሁሉንም ጠየኳቸው እንዳላዩት
ዝም ብዬ መጓዝ ጀመርኩ እናቴ ከሞተች ጀምሮ ብቸኝነት በጣም አፈራዋለሁ ጥሩ ስራ ስሰራም ይሁን መጥፎ ስራ ስሰራ ሰው አብሮኝ እንዲኖር እፈልጋለሁ ብቻ ስለመሆን ማሰብ በራሱ ሰላም ይነሳኛል።
ብቻ የዛን ቀን እዮብ ቢያንስ ቤት ከመጣ ብዬ ቤት ገብቼ ጠበኩት የለም። በነጋታው 11 ሰአት አካባቢ ወደናቴ መቃብርጋ ሄድኩኝ ። መቃብሯ ላይ ያለውን ፎቶ ቀና ብሎ ለማየት ድፍረቱን አጣሁ። የተፈጠረወን አንድ ባንድ ነገርኳት።
ለሳምንት ያህል ከእዮብም ከልእልትምጋ ሳልገናኝ ሁለቱም አድራሻቸወን አጥፍተው ጠፉብኝ ሳምንቱ የአመታቶችን ያህል እረዘመብኝ።
መብላት ሁላ አቃተኝ።
ከዚህ በፊት እዮብ ሱሰኛ ስትሆን ሱስህ ነው ጓደኛህ ያለኝን አስታውሼ በየሰአቱ አንዴ አንዱን አንዴ አንዱን በቃ በላይ በላይ እጠቀማለሁ ግን ለኔ ምንም ሱስ ጓደኛ ሊሆነኝ አልቻለም።
ከሳምንት ቡሀላ እኔ ተነስቼ እዮብን ፍለጋ ስወጣ ወደቤት እየመጣ አየሁት፡፡
እንዴት ደስ እንዳለኝ እኔ አቃለሁ ግን የውስጤን እምቅ አድርጌ ይዤ ሳየው ተኮሳትሬ ቆምኩኝ።
አታስመስል ባክህ ውስጥህ እየሳቀ ግንባርህን አትቋጥር ብሎኝ ወደቤት ገባን።
ቁጭ ብለን ማውራት እንዳለብን ነግሮኝ ማውራት ጀመርን፡፡
በተለይ ስለልእልት ብዙ ነገር አወራኝ ሴት ልጅ ጉልበቷ እንባዋ ነው በተለይ ደሞ ለእንደ ልእልት አይነት ሴት ሰውን ተናግሮ ማስቀየም ለማይችል ምስኪን ሴት ከእንባ በላይ ጉልበት የላቸውም። በዚህ ምድር ላይ ለመኖር ተስፋ እንደቆረጥክና ጨካኝ ሰው እንደሆንክ የገባኝ ከልእልትጋ አድረህ ምንም እንዳልተፈጠረ ኖርማል ስትሆን ነው አለኝ ማለት አልኩት?
ቢያንስ ቢያንስ በጣም መፀፀት ማልቀስ ማንባት ነበረብህ ይቺን ልጅ ሳትወዳት ሳታፈቅራት የውሸት ጋጋታ ደርድረህ አብረሀት ካደርክ ከመድፈር በምንም አይተናነስም ባህራን ውስጥህን ሳየውኮ እንደዚህ አይነት ሰው አትመስለኝም አለኝ። አልነበርኩም እናቴ እስክትሞት እንደዚህ አልነበርኩም የእናቴ ሞት ሰወነቴን ንፁህ ልቤን ሁሉንም ነገሬን ነው ያሳጣኝ አልኩት።
ምናልባት ፈጣሪ አንዷን እናትህን ወስዶ ሌላ እናት ሊሰጥህ አለመሆኑን በምን አወክ???
መመለስ አልፈለኩም ይልቁንም ልእልትን ከእናቴጋ ማወዳደሩ አበሳጨኝ።
ዝም ብዬ ተነስቼ ከቤት ወጣሁ ልእልትና ወንድሟ በኛ በር ላይ እያለፉ ነበር፡፡ ስታየኝ አንገቷን ደፋች እኔም ሳያት ልቤ መታ ፊቷን ተመለከትኩት ጥቁርር ብላለች የለበሰችው ልብስ እዚህ ግባ አይባልም ፀጉሯን ሁለት ቦታ ሰርታው አሲዛዋለች በዛ ላይ እንዳለ ተነጫጭቷል፡፡
አሳዘነችኝ ያ የበፊት ነገሯ ፊቴ ላይ መጣብኝ ቢያንስ ደስተኛ ባላደርጋት እንኳን ለሀዘኗ ምክንያት መሆን አልፈልግም ነበር።
ባጠገቤ ከወንድሟ ደና ግልምጫ ደርሶኝ አልፈው ሄዱ።
ባጠገቤሼ ወደውስጥ ገባሁና ለእዮብ ነገርኩት እዮቤ ልእልትንኮ አየኋት አልኩት።
ከተቀመጠበት እንዴት እንደተነሳ አላቅም የታለች የታለች እያለ ወደ ውጭ ወጣ ከሩቅ እየታጠፉ ከጀርባዋ አይቷት ተመልሶ ገባ።
አየሀት እእ እንዴት ናት ካየኋትኮ ሳምንት ሆነኝ ጠቁራለች ወይስ እንደበፊቱ ናት???? አለኝ::
ፊቷ ተቀይሯል አልኩት። ወዲያው የሱም ፊት ተቀየረ ምናለ ላንዴ እኔን በወደደችኝና በምላሹ ምሰጣትን ክብርና ቦታ ምናለ ልእልት ትንሽ ቀደም ብላ ወደህይወቴ
በመጣች ኖሮ አለኝ። ግቢ ውስጥ ከወዲያ ከወዲህ እየተንጎራደደ ባህራን ግን እንዴት አስቻለህ ምንም አልናፈቀችህም ምንም ትዝ አትልህም በቃ የጥያቄ መአት አከታተለብኝ ሲሰለቸኝ ትቼው ከቤት ወጣሁ።
ሰፈር ውስጥ ሰው እንዳያየኝ ፈጠን ፈጠን እያልኩ ስለምራመድ ከመቼው አስፋልት እንደደረስኩ አላቅም ።
እኔ በዚህኛው አስፋልት ቆሜ ልእልት በዛኛው አስፋልት ቆማ ፊት ለፊት መተያየት ጀመርን ። ሳያት ሳያት ውስጤ ምን እንደሚሰማኝ አላቅም እያዘንኩ ይሁን እየተከፋሁ ለራሴም አይታወቀኝም ሳያት ታሳሳኛለች ብዬ እራሴን ለማሳመን ብሞክርም አልችልም አይ በቃ ህይወቴ ውስጥ ምንም ዋጋ የላትም ተራ ሰው ናት ብዬ ለማሰብም እቸገራለሁ ።
ነገሮች ውዝግብ እንዳረጉኝ ጊዜያቶች ተቆጠሩ ጊዜዎች በሄዱ ቁጥር ደሞ እኔ እዛ ሰፈር መሄድም አቆምኩ እዮብ ደሞ የልእልትን አይን ለማየት ከዛ ሰፈር መውጣት አቆመ ብል ማካበድ አይሆንብኝም ቀስ በቀስ ለሱሱ ሚሰውን ጊዜ እየቀነሰ እሷን ጥበቃ ሰፈር መታጠፊያ ላይ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ስራው አደረገው......
🔻ክፍል 2️⃣6️⃣ ላልተወሰነ ግዜ ተቋርጧል እሱ እስኪቀጥል አንድ ምርጥ ታሪክ የምናደርሳችሁ ይሆናል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️