እርካታ ሲለካ!
ራበኝ በላሁበት፣
ጠማኝ ጠጣሁበት፣
አማረኝ ለበስኩኝ፣
በረደኝ ደረብኩኝ፣
ሰለቸኝ ቀየርኩኝ፣
ወጣሁ ተናፈስኩኝ፣
ሞላ ፍላጎቴ፣
ሠመረ ምኞቴ፣
ተሟላ ጤናዬ፣
ጨመረ ኪሎዬ፣
ሰከነ ሥጋዬ፣
አረፈ ገላዬ፣
ሥጋዬም ረካ፣
ነፍሴስ በምን ትርካ!
አልኮልና ዝሙት
ዉጤታቸው ፀፀት፣
ጫትና አጉል ሱስ፣
አይጠግኑም መንፈስ፣
ወሬ ሙዚቃ ሣቅ፣
ትርፉ ቀልብ ማድረቅ፣
..
እርቀው ቢሄዱ፣
ቢወጡ ቢወርዱ፣
ቢጓዙ ቢደክሙ፣
ቢለፉ ቢተክኑ፣
ለቀልብ መድኃኒቱ፣
ለነፍስ ጤንነቱ፣
ለሕይወት ስምረቱ፣
ለምላስ ዕረፍቱ፣
ለቋንቋ ዉበቱ፣
ለሩሕ ምሽግ ቤቱ፣
ለወሬ ድምቀቱ፣
ለፊት ኑር ሞገሱ፣
አስተማማኝ መልሱ፣
ጌታን ማስታወሱ፣
እሱን ማወደሱ፣
ስሙን መቀደሱ፣
ማጥራት ማሞገሱ፣
ለመንፈስ ምግቡ፣
ዚክር ነው ቀለቡ፣
በዚክር ነው ለካ
እርካታ ሲለካ!!
ለአህት ወንድሞች ሼር አድርጉት
https://t.me/AbuTeqiyPomeChannel
ራበኝ በላሁበት፣
ጠማኝ ጠጣሁበት፣
አማረኝ ለበስኩኝ፣
በረደኝ ደረብኩኝ፣
ሰለቸኝ ቀየርኩኝ፣
ወጣሁ ተናፈስኩኝ፣
ሞላ ፍላጎቴ፣
ሠመረ ምኞቴ፣
ተሟላ ጤናዬ፣
ጨመረ ኪሎዬ፣
ሰከነ ሥጋዬ፣
አረፈ ገላዬ፣
ሥጋዬም ረካ፣
ነፍሴስ በምን ትርካ!
አልኮልና ዝሙት
ዉጤታቸው ፀፀት፣
ጫትና አጉል ሱስ፣
አይጠግኑም መንፈስ፣
ወሬ ሙዚቃ ሣቅ፣
ትርፉ ቀልብ ማድረቅ፣
..
እርቀው ቢሄዱ፣
ቢወጡ ቢወርዱ፣
ቢጓዙ ቢደክሙ፣
ቢለፉ ቢተክኑ፣
ለቀልብ መድኃኒቱ፣
ለነፍስ ጤንነቱ፣
ለሕይወት ስምረቱ፣
ለምላስ ዕረፍቱ፣
ለቋንቋ ዉበቱ፣
ለሩሕ ምሽግ ቤቱ፣
ለወሬ ድምቀቱ፣
ለፊት ኑር ሞገሱ፣
አስተማማኝ መልሱ፣
ጌታን ማስታወሱ፣
እሱን ማወደሱ፣
ስሙን መቀደሱ፣
ማጥራት ማሞገሱ፣
ለመንፈስ ምግቡ፣
ዚክር ነው ቀለቡ፣
በዚክር ነው ለካ
እርካታ ሲለካ!!
ለአህት ወንድሞች ሼር አድርጉት
https://t.me/AbuTeqiyPomeChannel