መለየት ህመም ነው
መለየት ህመም ነው
እጅግ የሰቃያል፣
መገኛው እሩቅ ነው
ለመዳን ይከብዳል።
አንተ የአላህ ባሪያ ትንሽ ቀን የማውቅህ፣
በውርጭ በብርዱ ደጋ የወሰድኩህ፣
ለትንሽ ጊዚያት የአንከራተትኩህ፣
ውድ ወንድሜ ነበርክ ሁሌ የማልሰለችህ።
ዛሬ ላይ በአጭሩ መለያየት መጥቶ፣
ከሀገር ብትወጣ ሁሉ ነገር ሰምሮ፣
የመለየት ህመም ይዞኛል በርትቶ፣
ብቼኝነት ገዝፏል ሁሉም ባንተ ቀርቶ።
ይድረስህ ስላምታ ጋራውን ተሻግሮ፣
ከሳውድ ክልል ውስጥ አንተን አንተን ብሎ፣
ከናፋቂህ ዘንዳ ይድረስህ ከወሎ፣
ላ’ንተ ደስታ ነው ውድ ሀገር ደርሰሃል፣
እኔስ ታምሜያለሁ ሌላውም ይልሀል፣
ለደሴ ዙሪያዎች መሄድህ ኮድቶናል፣
ምንም ማድረግ ሳንችል ዝምታን መርጠናል።
በመለየት ህመም ስቅይት ይዘናል።
አንተ የበራራው የጥቅሳው ጀግና፣
ምን ብዬ ልንገርህ የሆዴን ላውጣና።
እንዴት ልግለፅልህ. በየትኛው ቃና፣
የመለየት ህመም አርጎኝ ደፋቀና፣
በዝምታ ብዛት. ተጭኖኝ ደመና፣
ሁሉ ነገር ቀርቶ እየመሸ ነጋ ።
ወንድም ከተመቸህ ከደላለኝ ከቶ፣
የሄድክበት ሀገር ከተስማማህ ከቶ፣
ለኔ ግደለኝም ብሰቃይም ደግሞ
ግን
ወሎ ይጠይቃል የትጠፋብን ብሎ፣
ተውሒድ የሚነገረው በገጠሩ ገብቶ
ሱናን የሚያሳየው. በግሩ ተንከራቶ፣
ሁሉም የሚጠራው እንደ ልጅ አንስቶ፣
ዲን እንዲያስተምረው መድረክ አዘጋጅቶ
ዛሬ ላይ ሲፈልግ አንተን አንተን አጥቶ።
ከቶ ከየት ትገኝ ተሻግረህ ከማዶ።
ውድ የአላህ ባሪያ በል አላህ ያስመችህ፣
ባለህበት ቦታ ሁሉንም ያግራልህ።
እዚህ ላለኡማ. በደዓህ አሳታውሰህ፣
ለሙስሊሙ ኡማ ጠቃሚ ያድርግህ።
ይድረስ
ለኑረዲን አል አረቢ. ሳውዲከወንድምህ
አወል ተፈራ ጭረቻ አስጎሪ
@AbuTeqiyQaidhttps://t.me/AbuTeqiyPomeChannel