የጨረቃና የፀሀይ መጋረድ የምን ምልክት ነው? እነዚህ ግርዶች ስናይ እንድንሰግድ የታዘዝነው ስንት ሰላት ነው? አሰጋገዱስ?
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው
1/ ከሁለቱ ብርሓናት (ጨረቃና ፀሀይ) የአንዳቸው ብርሐን ሲጠፋ ወይንም በክፊል ብርሀናቸው በመጋረድ ወደ ጥቁርነት ሲቀየር ኢስቲግፋር በማብዛት አላህ ቁጣውን ያነሳልንና በራሕመቱ ያዝንልን ዘንድ የሚሰገድ የሶላት አይነት ‹‹ሶላት አል-ኩስፍ›› ወይም ‹‹ሶላት አል-ኹሱፍ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ከፊል ሊቃውንትም ‹‹አል-ኩሱፍ›› ለፀሀይ ግርዶሽ ሲሆን ‹‹አል-ኹሱፍ›› የሚባለው ደግሞ ለጨረቃ ግርዶሽ ነው ይላሉ፡፡
2/ ሶላቱል-ኩሱፍን መስገድ ተወዳጅ የኾነ ጠንካራ ሱንና ነው፡፡ እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደነገረችን፡- ‹‹በረሱል (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘመን ፀሀይ ብርሀኗ ተጋረደ፡፡ የአላህ መልክተኛም ሶሓቦችን ሶላት አሰገዱ…›› [ቡኻሪይ 1044፣ ሙስሊም 901፣ ሙወጠእ ኢማሙ ማሊክ።]
ከአቢ መስዑድ አል-አንሷሪይ በተላለፈው ሌላ ሐዲሥ ላይም የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- ‹‹ፀሀይና ጨረቃ ከአላህ የችሎታው መገለጫ ምልክቶች ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ ባሪያዎቹንም በነሱ ሰበብ (ቅጣቱን) ያስፈራራበታል፡፡ ለማንም ሰው ሞት የሚጋረዱም አይደሉም፡፡ የኾነ ነገር በነሱ ላይ ካያችሁ ቶሎ ብላችሁ ስገዱና አላህም በናንተ ላይ ያለውን እንዲያነሳላችሁ ለምኑት›› [ሙስሊም 911።]
3/ የሶላቱል ኩሱፍ መነሻ ወቅት የፀሀይ ወይንም የጨረቃ ብርሐን በሚጋረድበት ወቅት ነው፡፡ የሚያበቃው ደግሞ ይህ ግርዶሽ ከነሱ ላይ የተነሳላቸው ግዜ ነው፡፡ ግርዶሹ በመነሳት ወይም አንዳቸው በመግቢያ ሰዓታቸው ሲጠልቁ (ሲሰወሩ) ማለት ነው፡፡ የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዳሉት ‹‹ፀሀይና ጨረቃን የተጋረዱ ኾነው ባያችሁ ጊዜ፤ ግርዶሹ እስኪገለጥ አላህን በመለመን ሶላትን ስገዱ..›› [ቡኻሪና ሙስሊም።]
4/ የሶላቱል ኩሱፍ አሰጋገድ ሁኔታ በሁለት ረከዓህ ነው የሚኾነው፡፡ ከተለመደው ሶላት ለየት የሚያደርገው ነገር በመጀመሪያውና በሁለተኛው ረከዓህ ላይ ሩኩዕ የሚደረገውና ከሩኩዕ መነሳት ሁለት ሁለት ጊዜ መሆኑ ነው፡፡ በጥቅሉ አራት አይነት አኳኋን አለው፡፡ እነሱም፡-
ሀ/ ሁለት ረከዓህ ሶላት፡፡ ሩኩዑ እንደ ማንኛውም አይነት ሶላት ባለ አንድ ሩኩዕ የኾነ አሰጋገድ፡፡
ለ/ ሁለት ረከዓህ ሶላት፡፡ ግን ሩኩዑ በየረካአው ሁለት ሁለት ጊዜ የሆነ፡፡ [ቡኻሪይ 1066፣ ሙስሊም 901።]
ሐ/ ሁለት ረከዓህ ሶላት፡፡ ግን ሩኩዑ በየረካአው ሶስት ሶስት ጊዜ የሆነ፡፡ [ነሳኢይ 3/129፣ ሙስሊም 901።]
መ/ ሁለት ረከዓህ ሶላት፡፡ ግን ሩኩዑ በየረካአው አራት አራት ጊዜ የሆነ፡፡ [ሙስሊም 908።]
ፋቲሓና ተጨማሪ ሱራ (አያት) ይቀራል፡፡ ከዛም ሩኩዕ ይወረዳል፡፡ ከዛም ቀና በማለት ይነሳል፡፡ ትንሽ ከቆየ በኋላ ድጋሚ ሩኩዕ ይደረጋል ማለት ነው፡፡
5/ ሶላቱል ኩሱፍን በጀመዓ መስገዱ ተወዳጅ ነው፡፡ ኾኖም ሁሉም ባለበት ላይ ኾኖ በግል መስገድና ኢስቲግፋር ማብዛት ይችላል፡፡ ወላሁ አዕለም)፡፡
© አህመድ ጀበል
———
ይከታተሉን | Follow us፡
ቴሌግራም | @Africatvch1
Tik Tok | https://vm.tiktok.com/JJ4u7hN/
ዩቲዩብ | https://youtu.be/XCeDFKDS2sY
┄┄┉┉✽̶»̶̥