Postlar filtri




አደራ 3ዱዓወችን ሁሌም እንዳትረሳ✋
1.ጌታየ ሆይ ! መጨረሻየን አሳምርልኝ
2.ጌታየ ሆይ ! ከመሞቴ በፊት ንፁህ ተውባ ወፍቀኝ
3.ልቦችን ገለባባጭ የሆንክ አምላክ ሆይ ! አደራ ልቤን በዲንህ ላይ አፅናልኝ


ይከታተሉን | Follow us፡
ቴሌግራም | @Africatvch1
Tik Tok | https://vm.tiktok.com/JJ4u7hN/
ዩቲዩብ | https://youtu.be/XCeDFKDS2sY

┄┄┉┉✽̶»̶̥





"ኢብን ዐባስ (ረ.ዐ) እንዳሉት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹የገሃነምን እሳት እንዳየው ተደርጓል፡፡ ከሐዲ ሴቶች በብዛት (የእሳት) ጓደኛ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፡፡ ‹‹በአላህ ይክዳሉን?›› የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፡፡ ‹‹ባሎቻቸውን ነው የሚክዱት፡፡ ለነርሱ የተዋለላቸውን መልካም ነገር ያስተባብላሉ፡፡ (ምስጋና ቢስ ይሆናሉ፡፡) ለብዙ ጊዜ ፀጋ የዋልክላትን አንዲት ሴት ከዚያ ካንተ (የማትፈልገውን) አንድ ነገር ካየች፡- ‹‹ምን አድርገህልኝ ታውቃለህ፡፡›› ትላለች፡፡




የግሩባችንን አድራሻ
ለመቀላቀል 👇👇👇
https://t.me/joinchat/P6mUxRu_O_Kwa-zNfXoaig


#ለኸይር ካልሆነ በቀር ዝምታ ማብዛትን አደራችሁን፡፡
ታማኙና እዉነተኛዉ ነቢይ❣ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ስለ ዝምታ ታላቅነት ሲናገሩ
عليك بطول الصمت إلا من خير
#አደራህን_ኸይር_ነገር_ሲቀር_ዝምታ_አብዛ ይላሉ፡፡
አዎ! አንሸወድ! ዝም እንበል! ወደ አሏህ የሚያቃርብ ዝምታ ሰዎች ዘንድ ከሚያስቅ ንግግር ይሻላል። #ምክንያቱም_ዛሬ_ብዙ_ልናስቅ_አንችላለን ነገ ግን ... ብዙ ታስለቅሳለች፡፡ ሰይዱና ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንድህ ይላሉ፦
من كثر كلامه كثر سقطه ومن كثر سقطه قل حياؤه،ومن قل حياؤه قلورعه،ومن قل ورعه مات قلبه.سبحان الله!!
#ንግግሩ_የበዛ_ሰዉ ስህተቱ ይበዛል፤ስህተቱ የበዛ ሐያኡ ያንሳል፣ሐያኡ ያነሰ ጥንቁቅነቱ(አሏህን መፍራቱ)ያንሳል፤ጥንቅቁነቱ ያነሰ #ልቡ_ይሞታል!!! ያ አሏህ! ዝምታና እርጋታ ምን አይነት ወርቅና የማይጠገብ ነዉ!!



የግሩባችንን አድራሻ
ለመቀላቀል 👇👇👇
https://t.me/joinchat/P6mUxRu_O_Kwa-zNfXoaig


🌾የጁምዓ እለት ትሩፋት
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌾 فضلُ يوم الجمعةِ

⚂የጁምዓ እለት የሳምንቱ ምርጥ ቀን ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አላህ ዘንድ ከቀናቶች ሁሉ በላጩ የጁምዓ እለት ነው።» ብለዋልና በዚህ እለት ስራዎቻችንን ይበልጥ ማሳመር ይገባናል።
📚صححه الألباني في
السلسلة الصحيحة - رقم: (1502)
صحيح الجامع - رقم: (1098)

⚂የጁምዓ እለት በጀማዓ (በህብረት) የተሰገደ የፈጅር ሰላት ከየትኛውም ወቅት ሰላት በላጭ ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አላህ ዘንድ በላጩ ሰላት በጁምዓ እለት በጀማዓ የተሰገደ የሱብህ ሰላት ነው።» ብለዋልና ከየትኛውም እለት በበለጠ ቀድሞ ለመገኘት መጣር ይበልጥ ያስመነዳል።
📚السلسلة الصحيحة -
الألباني صحيح - رقم: 1566

⚂የጁምዓ እለት ከሌሎች ቀናት በበለጠ በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋት የማውረጃ ቀን ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«በጁምዓ ቀንና በጁምዓ ሌሊት በኔ ላይ ሰለዋትን አብዙ። በኔ ላይ አንዴ ሰለዋትን ላወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ያወርዳል።» ብለዋልና ትንሽ ሰርተን ከአስር እጥፍ በላይ ለማግኘት ከወዲሁ እድሉን እንጠቀም።
📚صحيح الجامع
الألباني حسن - رقم: 1209

⚂የጁምዓ እለት መኖሩም መሞቱም ለሙስሊሙ ፀጋ ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«ማንኛውም ሙስሊም የጁምዓ ቀን ወይም የጁምዓ ሌሊት የሞተ እንደሆን አላህ ከቀብር ፈተና ሳያድነው አይቀርም።» ብለዋል።
ስለዚህ በመጀመርያ የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን
♂አርካኑል ኢስላምን በስርዓቱ የተገበረ ሙስሊም እንሁን።
♂በማስከተልም አላህ በራህመቱ ከቀብር ፈተና እንዲጠብቀንና ለዚህ ሰበብም እንዲያበቃን ሁሌም እንለምነው።
📚حسنه الألباني في صحيح الترمذي - رقم: (1074) ، تخريج مشكاة المصابيح - رقم: (1316) الألباني :إسناده حسن أو صحيح لغيره

⚂የጁምዓ እለት የሳምንቱ ከኃጢኣት መንፂያ ቀን ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«ከባባድ ኃጢኣቶች ኖረው ካልጋረዱት በስተቀር አምስቱ ሰላቶች እንዲሁም ከጁምዓ እስከ ጁምዓ በመሃከላቸው ያለውን ኃጢኣት ያብሳሉ።»¹ በሌላ ዘገባም «ከባባድ ኃጢኣቶች ኖረው ካልጋረዱ በስተቀር ከጁምዓ እስከ ጁምዓ በመሃከላቸው ላለው ማበሻ ናቸው።»² ብለዋል።

ስለዚህ ከከባባድ ወንጀሎች በመራቅ ወይም ተውበት በማድረግ፣ አምስቱን እለታዊ ሰላቶች ጠብቆ በመስገድና የሳምንቱን ልዩ የስብስብ ቀን የጁምዓን ሰላት በመስገድ ተጨማሪ ግድፈቶቻችንን እናፅዳ።
¹📚صحيح مسلم - رقم: (233)
²📚الألباني - صحيح الجامع رقم: (3110)

⚂ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የመከባበርያ ቀን ነው።

ሁሉም ሙስሊም ክቡር ነው። ሀብታም ከድሃ ታላቅ ከታናሽ፣ ገዢ ከተገዢ የሚለይበት ቦታ አየደለምና መስጂድ ሲደርስ ያገኘበት ክፍት ቦታ ሊቀመጥ ይገባዋል እንጂ ማንንም አስነስቶ ወይም እንዲነሳ አስደርጎ ሊቀመጥ አይገባውም።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አንዳችሁ በጁምዓ ቀን ወንድሙ የተቀመጠበት ቦታ ሊቀመጥ ብሎ እንዳያስነሳው። ነገር ግን ሰፋ ሰፋ አድርጉ ይበል።» ብለዋልና ኢማሙ ኹጥባ ያልጀመሩ እንደሆነ ሰዎችን እንዲጠጋጉለትና እንዲሸጋሸጉለት በስርዓት ማግባትም ይችላል።
📚صحيح مسلم - رقم: (2178)

⚂ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የፅዳት ቀን ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አንዳችሁ ወደ ጁምዓ ሲሄድ ይታጠብ።» ማለታቸው ተዘግቧል።
📚صحيح البخاري - رقم: (882)

⚂ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የቁርኣን ቀን ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ ቀጣዩን ብለዋል☞
«በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መሃል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።»
📚حسنه الألباني في
تخريج مشكاة المصابيح - رقم:(2116)

በሌላም ዘገባ እኛ በተለምዶ ሐሙስ ማታ በምንለው የጁምዓ አጥቢያ ምሽቱን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው አጅሩ እጅግ በጣም ሰፊ ነው።
«ለይለቱል ጁምዓ ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሱ እና በበይተል ዐቲቅ (በካዕባ) መካከል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።» ብለዋል።
📚صححه الألباني في
صحيح الترغيب -رقم: (736)

⚅በተጨማሪም የጁምዓ እለት የማንንም ክብርና መብት የማንጥስበት፣ ከውስጥም ከውጭም በወሬም ሆነ በሌላ ጉዳይ ሰውን እንዳንረብሽ የተከለከልንበት ልዩ ቀን ነው። ይህንንም ለዒባዳ ብለን መስጂድ እንኳን መጥተን ክፍት ቦታ ፍለጋ ከሰው ትከሻ ላይ እየተረማመድን እንዳንሄድ ከልክለውናል። ኢማሙ ኹጥባ ላይ ሳሉ ምንም አይነት ቃል ትንፍሽ እንዳንል ተከልክለናል። ጣቶቻችንን ከመሰባበርም ሆነ ልብሶቻችንን ሆነ ሌላ ነገር አየነካካን እንዳንጫወት ተከልክለናል።

ማንኛውም ሰው በጁምዓ እለት ወደ መስጂድ ሲመጣ ክፍት ቦታ ከፊትለፊቱም ሆነ ከጎኑ ክፍተት እንዳይኖር ወደፊት መጠጋትን የመሰለ እንደገባ በማመቻቸት መቀመጥ አለበት። ምክንያቱም ከኋላ የሚመጡት ቦታ ፍለጋ ስህተት እንዳይፈፅሙና ክብሩንም እንዳይነኩ ይረዳልና። በመሰረቱ ቦታ ፍለጋ ከሰው ትከሻ ላይ መረማመድ ተከልክለናል። ኢማሙ ኹጥባ ላይ ሳሉ ምንም አይነት ቃል ትንፍሽ እንዳንልም ተከልክለናል። ጣቶቻችንን ከመሰባበርም ሆነ ልብሶቻችንን ሆነ ሌላ ነገር አየነካካን እንዳንጫወትም ተከልክለናል።
ባጠቃላይ
የሰው ትከሻ አትርገጥ~እንዳትወራገጥ
አርፈህ ተቀመጥ~በፀጥታ አድምጥ
ለጌታህ እጅ ስጥ

اللهم صل وسلم على نبينا محمد وعلى آله وأصحابه أجمعين
~
Abufewzan
© ተንቢሀት

Via = ኡስታዝ አህመዲን ጀበል


*እንዴት ነው ከእሳት መራቅና ጀነትን መግባት የሚቻለው?!*

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– "ከእሳት መራቅንና ጀነትን መግባት የፈለገ፣ እስከ ህይወት ፍጻሚው ድርስ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን በማመን ላይ ይጽና እንዲሁም ሰዎች ለሱ እንዲያደርጉለት የሚፈልገውን ነገር ለሰዎች ያድርግ።"
(ሙስሊም ዘግበውታል)


❥::::::::::::::::የጀነት_ስሞች::::::::::::: ❥
1) ጀነት
2) ዳሩ ሰላም
3) ዳሩል ኹልድ
4) ዳሩ ሙቃማህ
5) ጀነቱል መእዋ
6) ጀናት ዓድን
7) ዳሩል ሐየዋን
8) አል ፊርደውስ
9) ጀናቱ ነዒም
10) መቃሙል አሚን
11) 'መቀዓድ ሲድቅ'
12) 'ቀደመ ሲድቅ'
▒▒▒ ጀነት ▒▒▒
•የጀነት ፀጋዎቿ ያልቁብኛል ብሎ ጭንቀት ፤ እለያታለው ብሎ ስጋት የለም; ፀጋዎቿ
ዘውታሪ ሞትም የለምና!
ዱንያ ላይ የቱን ያክል ገንዘብ ቢኖርህ ገንዘብህ ቢትረፈረፍ ንብረትህ ቀድሞህ
ይጠፋል አልያም ትተኸው ትሄዳለህ ።
•በጀነት ውስጥ ልክ እንደ ዱንያ ጠላት የለም ለወደፊት ማሰብ የሚባል ነገርም የለም
፤ ሁሉ ነገር እንደፈለክ ነው; ጥላቻ የሚባል ነገርም ከልብ ላይ ይወገዳል ።
• በጀነት ውስጥ ልክ እንደ ዱንያ ኑሮ እንድትሞላልኝ ብለህ ሰበብ ለማድረስ ደፋ ቀና
ማለት የለም; ጀነት ውስጥ ሙሰቢቡ (አላህ) ነፍስ የምትፈልገውን ሁሉ አዘጋጅቷልና
•••
------------------------------------------------
ጌታችን ሆይ! ለጀነትህ ብቁ ባንሆንም ጀሐነምን መቋቋም አንችልምና በሰፊው
እዘነትህ ጀነትህን ወፍቀን/


ይከታተሉን | Follow us፡
ቴሌግራም | @Africatvch1
Tik Tok | https://vm.tiktok.com/JJ4u7hN/
ዩቲዩብ | https://youtu.be/XCeDFKDS2sY

┄┄┉┉✽̶»̶̥


ዛሬ በአንዋር መስጂድ" አንዲትን ነብስ ሕያው ያደረገ የሠዎችን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ።"

በሚለው የቁዱስ ቁርአን ጥቅስ ላይ መሰረት በማድረግ ልዩ የደም ልገሳ አካሂደዋል ።

በቦታው ተቀዳሚ ሙፍቲህ ዶክተር ሃጂ ኡመር ኢድሪስ ተገኝተው መክፈቻ ንግግር አድርገዋል ። በዚህ በኮረና ቫይረስ ምክንያት ሃገራችን እየተጨነቀች ባለችበት ሰአት ይህን መሰል በጎ ተግባሮች መከወናቸው ይበልጥ የሚበረታቱ ናቸው ብለዋል ።

ምንጭ
Bilal tube

ይከታተሉን | Follow us፡
ቴሌግራም | @Africatvch1
Tik Tok | https://vm.tiktok.com/JJ4u7hN/
ዩቲዩብ | https://youtu.be/XCeDFKDS2sY

┄┄┉┉✽̶»̶̥


ዛሬ አባቶች ቀን ነው! አባት ለሆናችሁ እንዲሁም አባቶቻችሁን ለምትወዱ ልጆችም መልካም የአባቶች ቀን ይሁንላችሁ!


https://instagram.com/stories/selullaofficial/2336239233282238085?igshid=f6qynm7btvje


❥:::::::::::::ምርጥ ጓደኛ::::::::::❥

☞ከጓደኛ ምርጡ ማነው? ተብለው ሲጠየቁ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ በማለት መለሱ "

አላህን እንድትፈራ የሚያስታውስህ መልካም ሲሰራ ስታየው ተግባሩን የምትከተል ለችግርህ

ስትጠራው የሚደርስልህ ነው አሉ አላህ ጥሩ ጥሩ ጓደኞችን ያብዛልን።
ይከታተሉን | Follow us፡
ቴሌግራም | @Africatvch1
Tik Tok | https://vm.tiktok.com/JJ4u7hN/
ዩቲዩብ | https://youtu.be/XCeDFKDS2sY

┄┄┉┉✽̶»̶̥
ሊና TUBE on TikTok
#በየቀኑየእንግሊዘኛቃላትከነትርጉማቸው #lina_tube #ethiopia #habesha


‍ 💐የአሏህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦

💐"አምስት ነገሮችን ከአምስት ነገሮች በፊት ያዝ(ሰንቅ)፦

☞ህይወትህን ከሞትህ በፊት ፣
☞ጤንነትህን ከበሽታህ በፊት፣
☞ክፍት ጊዜህን ከመወጠርህ በፊት፣
☞ወጣትነትህን ከእርጅናህ በፊት፣
☞ሀብትህን ከድህነትህ በፊት፡፡"
💐ሶሂህ አልጃሚእ 1077💐

ይከታተሉን | Follow us፡
ቴሌግራም | @Africatvch1
Tik Tok | https://vm.tiktok.com/JJ4u7hN/
ዩቲዩብ | https://youtu.be/XCeDFKDS2sY

┄┄┉┉✽̶»̶̥
ሊና TUBE on TikTok
#በየቀኑየእንግሊዘኛቃላትከነትርጉማቸው #lina_tube #ethiopia #habesha


የጨረቃና የፀሀይ መጋረድ የምን ምልክት ነው? እነዚህ ግርዶች ስናይ እንድንሰግድ የታዘዝነው ስንት ሰላት ነው? አሰጋገዱስ?
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

1/ ከሁለቱ ብርሓናት (ጨረቃና ፀሀይ) የአንዳቸው ብርሐን ሲጠፋ ወይንም በክፊል ብርሀናቸው በመጋረድ ወደ ጥቁርነት ሲቀየር ኢስቲግፋር በማብዛት አላህ ቁጣውን ያነሳልንና በራሕመቱ ያዝንልን ዘንድ የሚሰገድ የሶላት አይነት ‹‹ሶላት አል-ኩስፍ›› ወይም ‹‹ሶላት አል-ኹሱፍ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ከፊል ሊቃውንትም ‹‹አል-ኩሱፍ›› ለፀሀይ ግርዶሽ ሲሆን ‹‹አል-ኹሱፍ›› የሚባለው ደግሞ ለጨረቃ ግርዶሽ ነው ይላሉ፡፡

2/ ሶላቱል-ኩሱፍን መስገድ ተወዳጅ የኾነ ጠንካራ ሱንና ነው፡፡ እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደነገረችን፡- ‹‹በረሱል (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘመን ፀሀይ ብርሀኗ ተጋረደ፡፡ የአላህ መልክተኛም ሶሓቦችን ሶላት አሰገዱ…›› [ቡኻሪይ 1044፣ ሙስሊም 901፣ ሙወጠእ ኢማሙ ማሊክ።]

ከአቢ መስዑድ አል-አንሷሪይ በተላለፈው ሌላ ሐዲሥ ላይም የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- ‹‹ፀሀይና ጨረቃ ከአላህ የችሎታው መገለጫ ምልክቶች ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ ባሪያዎቹንም በነሱ ሰበብ (ቅጣቱን) ያስፈራራበታል፡፡ ለማንም ሰው ሞት የሚጋረዱም አይደሉም፡፡ የኾነ ነገር በነሱ ላይ ካያችሁ ቶሎ ብላችሁ ስገዱና አላህም በናንተ ላይ ያለውን እንዲያነሳላችሁ ለምኑት›› [ሙስሊም 911።]

3/ የሶላቱል ኩሱፍ መነሻ ወቅት የፀሀይ ወይንም የጨረቃ ብርሐን በሚጋረድበት ወቅት ነው፡፡ የሚያበቃው ደግሞ ይህ ግርዶሽ ከነሱ ላይ የተነሳላቸው ግዜ ነው፡፡ ግርዶሹ በመነሳት ወይም አንዳቸው በመግቢያ ሰዓታቸው ሲጠልቁ (ሲሰወሩ) ማለት ነው፡፡ የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዳሉት ‹‹ፀሀይና ጨረቃን የተጋረዱ ኾነው ባያችሁ ጊዜ፤ ግርዶሹ እስኪገለጥ አላህን በመለመን ሶላትን ስገዱ..›› [ቡኻሪና ሙስሊም።]

4/ የሶላቱል ኩሱፍ አሰጋገድ ሁኔታ በሁለት ረከዓህ ነው የሚኾነው፡፡ ከተለመደው ሶላት ለየት የሚያደርገው ነገር በመጀመሪያውና በሁለተኛው ረከዓህ ላይ ሩኩዕ የሚደረገውና ከሩኩዕ መነሳት ሁለት ሁለት ጊዜ መሆኑ ነው፡፡ በጥቅሉ አራት አይነት አኳኋን አለው፡፡ እነሱም፡-

ሀ/ ሁለት ረከዓህ ሶላት፡፡ ሩኩዑ እንደ ማንኛውም አይነት ሶላት ባለ አንድ ሩኩዕ የኾነ አሰጋገድ፡፡
ለ/ ሁለት ረከዓህ ሶላት፡፡ ግን ሩኩዑ በየረካአው ሁለት ሁለት ጊዜ የሆነ፡፡ [ቡኻሪይ 1066፣ ሙስሊም 901።]
ሐ/ ሁለት ረከዓህ ሶላት፡፡ ግን ሩኩዑ በየረካአው ሶስት ሶስት ጊዜ የሆነ፡፡ [ነሳኢይ 3/129፣ ሙስሊም 901።]
መ/ ሁለት ረከዓህ ሶላት፡፡ ግን ሩኩዑ በየረካአው አራት አራት ጊዜ የሆነ፡፡ [ሙስሊም 908።]

ፋቲሓና ተጨማሪ ሱራ (አያት) ይቀራል፡፡ ከዛም ሩኩዕ ይወረዳል፡፡ ከዛም ቀና በማለት ይነሳል፡፡ ትንሽ ከቆየ በኋላ ድጋሚ ሩኩዕ ይደረጋል ማለት ነው፡፡

5/ ሶላቱል ኩሱፍን በጀመዓ መስገዱ ተወዳጅ ነው፡፡ ኾኖም ሁሉም ባለበት ላይ ኾኖ በግል መስገድና ኢስቲግፋር ማብዛት ይችላል፡፡ ወላሁ አዕለም)፡፡
© አህመድ ጀበል
———
ይከታተሉን | Follow us፡
ቴሌግራም | @Africatvch1
Tik Tok | https://vm.tiktok.com/JJ4u7hN/
ዩቲዩብ | https://youtu.be/XCeDFKDS2sY

┄┄┉┉✽̶»̶̥
ሊና TUBE on TikTok
#በየቀኑየእንግሊዘኛቃላትከነትርጉማቸው #lina_tube #ethiopia #habesha


ኤም.ዲ.ፍ STORE ® dan repost
የፀሀይ ግርዶሽ፣ አላማጣ!

ፎቶ: አላማጣ ከተማ ህዝብ ግንኙነት ፅ/ቤት
🔴በፌስቡክ 🔵
https://www.facebook.com/103893371374041/posts/107809020982476/

🔴በዩቲብ ገፅ🔵
https://youtu.be/XCeDFKDS2sY

🔴መረጃዎች ሼር ያድርጉ 🔵
https://t.me/joinchat/AAAAAFBYYkolMpWWI0qkgA


ኤም.ዲ.ፍ STORE ® dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ከፊል ግርዶሹን የሚያሳይ ቪድዮ!

🔴በፌስቡክ 🔵
https://www.facebook.com/103893371374041/posts/107809020982476/

🔴በዩቲብ ገፅ🔵
https://youtu.be/XCeDFKDS2sY

🔴መረጃዎች ሼር ያድርጉ 🔵
https://t.me/joinchat/AAAAAFBYYkolMpWWI0qkgA






Quran < በድምጽ > ለምፈልጉ


ኤም.ዲ.ፍ STORE ® dan repost
​​​_______________________
አጭር ታሪክ

ከወደዱት ሼር ያድርጉ
________________



በአንዲት ትንሽዬ ከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ አይነስውር ሰውዬ
ነበር።ይህ አይነስውር ሰውዬ መሬት ሲጨላልም ወደ ከተማው
መውጫ ያለው ወንዝ አከባቢ እየሄደ ንፁህ አየር መውሰድ
ያዘወትር ነበር።

ታድያ በዛ በጨለማ ሲሄድና ሲመለስ በእጁየመብራት ፋኖስ ይዞ ነው። ሁልጊዜ እንዲህ ያደርጋል።ከእለታት በአንዷ ምሽት 3 ወጣቶች እርስ በርስ እየተቀላለዱ
ሲያልፉ አይነስውሩ ሰውዬ ከነፋኑሱ ያገኙታል።


"አንተ አይነስውር ነህ፤ እንደሚያይ ሰው ፋኖስ ይዘህ ትዞራለህእንዴ" ብለው ተሳለቁበት፣ ሳቁበት።ሰውዬውም በእርጋታ እንዲህ አላቸው፡-"ልክ ናቹ፤ እኔስ አላይምነገርግንፋኑሱ ይጠቅመኛል፤ ምክንያቱም ሰዎች በጨለማው ምክንያት ሳያዩኝ ከገፈተሩኝ
በህዋላ ከምናደድባቸው ፋኑሱ ይዤ ባበራላቸው ለሁለታችን ይጠቅማል" ብሏቸው ሄደ። ወጣቶቹም በሰውዬው ቅን
አስተሳሰብ ተደነቁ።


"ማየት ያለብን በህሊናችን ነው፤ ለሰዎች የምናደርገው በጎ
ነገር ራሱ ተመልሶ በእጥፍ ይከፍለናልና።"


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
•●◉Join us share ••●◉

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌

ቴሌግራም |
@Yefkrtarik @Yefkrtarik2
ፌስቡክ | facebook.com/Yefkrtarik
Tik tok | https://m.tiktok.com/v/6832937192520797445.html?u_code=dcdaal9c13hj22&preview_pb=0&language=en&_d=d9j573m2gche7l&share_item_id=6832937192520797445×tamp=1590949455&user_id=6828268678807995398
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄


በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 6 ደረሰ!

በተጓዳኝ ህመም ምክንያት በፅኑ ህክምና ላይ የነበረች እና በትናንትናው ዕለት የኮሮና ቫይረስ በምርመራ የተገኘባት የ32 ዓመት 'የአዲስ አበባ ነዋሪ' የሆነች ኢትዮጵያዊት ትላንት ለሊት ህይወቷ አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 6 ደርሷል።

Abel birhanu ©

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

1 366

obunachilar
Kanal statistikasi