የ6 ዓመት ህፃን ያገተ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
ህፃን ኢብራሂም ጀማል የሱፍ ዕድሜው 6 ዓመት ሲሆን በደ/ወሎ ዞን ወራኢሉ ወረዳ ቀበሌ 01 ጥር 23 /2017 ዓ/ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት ገደማ የጠፋ መሆኑን ወላጅ አባቱ አቶ ጀማል የሡፍ ገልፀዋል።
የህፃኑ አባት ልጁ መጥፋቱን እንዳረጋገጡ በጠፋ ከ5 ሰዓታት በኋላ ማለትም ጥር 23/2017 ዓ/ም ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ በኮምቦልቻ ከተማ ለአቢሻገር ክ/ከተማ ፖሊስ እንዳሳወቁ ተመላክቷል።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአቢሻገር ክ/ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ም/ኢ/ር ሁሴን መብራቱ እንዳሉት የእግታ ወንጀሉ መረጃ እንደደረሰ ፖሊስ በኬላና በሁሉም አጠራጣሪ ቦታዎች ጥብቅ ክትትል ሲያደረግ እንደነበር ገልፀዋል።
ሀላፊውም እንዳሉት ከተጠናከረ ክትትልና ፍተሻ በኋላ በ2ኛው ቀን ጥር 24/2017 ዓ/ም ከጧቱ 2 ሰዓት በኬላ ፍተኛ ህፃኑን ከአጋች ሰይድ ኡመር ጣሂር ጋር በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ እና ህፃኑን ከነ ሙሉ ጤንነቱ ለወላጅ አባቱ ያስረከቡ መሆኑን አስረድተዋል።
እንደ ኢንስፔክተሩ ገለፃ በአጋቹ ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
ያነጋገርናቸው የታጋች ህፃን አባት አቶ ጀማል የሱፍ ልጃቸውን በማግኘታቸው ደስታቸው እጥፍ መሆኑን ገልፀው ልጃቸውን የታደገላቸውን ፖሊስ ታላቅ የሆነ አክብሮትና ምስጋና ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የአቢሻገር ክ/ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር ሁሴን መብራቱ እንዳሉት ለፖሊስ ሀይሉ የሚሰወር የወንጀል ድርጊት አይኖርም ማህበረሰቡ በአካባቢያቸው ፀጉረ ልውጥ እና አጠራጣሪ ሰዎች ሲያጋጥም ለፖሊስ ጥቆማ መሥጠት፤ ራሥን፣ ቤተሰብን እና ንብረትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በጀግንነት መጠበቅ በሰባዊነት ማገልገል!!
#መረጃው በኮምቦልቻ ከተማ የአቢሻገር ክፍለ ከተማ ፖሊስ ነው።