እንኳን ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) አደረሳችሁ!
ባንካችን 4ኛ ዙር እችላለሁ መርሃ ግብርን በይፋ ጀምሯል!
እ.አ.አ ከማርች 3 - 31 ቀን 2025 ድረስ በሚቆየው የሴቶች የሥራ ፈጠራ፣ የሙዚቃና የቲክቶክ ቪዲዮ ውድድር ላይ ተሳተፉ! ተሸለሙ !
1) የሙዚቃ ተሰጥዖ ውድድር
ባንካችን የሙዚቃ ተሰጥኦ ያላቸውን ሴት ተሳታፊዎችን በማወዳደር በባለሙያና በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰጥ የህዝብ ድምጽ አሸናፊዎችን ይሸልማል፡፡ ሽልማቱ 1ኛ ብር 100,000፣ 2ኛ ብር 75,000 እና 3ኛ ብር 50,000 ይሆናል፡፡
በሙዚቃው ዘርፍ ተሰጥኦ አለን የምትሉት ከ 3ደቂቃ ያልበለጠ የሙዚቃ ሥራ ያለ ሙዚቃ መሣሪያና የድምፅ ማዳመጫ (Earphone) በቪዲዮ ሰርታችሁ በቴሌግራም አድራሻ --- 0919- 85 73 73 ላኩልን፡፡
2) የቲክቶክ ቪዲዮ ተሰጥዖ ውድድር
በተመረጡ ቲክቶከሮች መካከል ለሴት ደንበኞቻችን ያዘጋጀናቸውን የአደይና ዘህራ የቁጠባ ሂሳቦች በተለየ መንገድ የማስተዋወቅ ውድድር ይካሄዳል፡፡በዚህም ውድድር ሽልማቱ 1ኛብር 100,000፣ 2ኛ ብር 75,000 እና 3ኛብር 50,000 ይሆናል፡፡
3) የሥራ ፈጠራ ውድድር
የሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታት ባንኩ ባሉት ዲስትሪክቶች የሥራ ፈጣሪ ሴቶችን በመምረጥ በአነስተኛ የወለድ ምጣኔ ካለመያዣ እስከ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብድር ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ መስፈርቶችን የምታሟሉ አቅራቢያችሁ ባሉ ቅርንጫፎችና የዲስትሪክት ፅ/ቤቶች በመቅረብ ከየካቲት 19 እስከ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት በጽሑፍ ጥያቄያችሁን አቅርቡ፡፡
መሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች አስቀድማችሁ የፌስቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/BoAeth/ ተቀላቀሉ
የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ለማግኘት ሊንኩን ይጠቀሙ፡፡
https://t.me/BoAEth