ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ :ጥር 29/2017
"በአክሽን ፎር ዘኒዲ ኢን ኢትዮጵያ"በሚባል ግብረ-ሰናይ ድርጅት ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሣቁስ ተሰጠ።
*************************************************************
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በኩል በተደረገ ጥረትና በተፈጠረ መልካም ግንኙነት ከአክሽን ፎር ዘኒዲ ኢን ኢትዮጵያ /ከ "Action for the needy in Ethiopia" ከሚሠኝ ግብረሰናይ ድርጅት ለሴት ተማሪዎች ድጋፍ ተገኘ።
በመሆኑም በግብረሰናይ ድርጅቱ ትብብርና በዳይሬክቶሬቱ መካከል በተፈጠረ መልካም ግንኙነት 25,000 ፓድ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ የተገኘ ሲሆን ለ2,500 ሴት ተማሪዎች; ለእያንዳንዳቸው 10/አስር-አስር /ፓዶች እንደተሰጣቸው ተገልጿል።
በመሆኑም ተማሪዎች ለንፅህና መጠበቂያ የሚያወጡትን ወጪ ለሌላ ጉዳዮች ማዋል እንደሚችሉ በመግለፅ፣ በቀጣይ ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ት/ቤት ሴት ተማሪዎችም በዚህ መልኩ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው መ/ር ንጉሴ ጎዳና ተናግረዋል። በሌላ በኩል ወደፊትም በተመሳሰይ መልኩ ከዚሁ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር ትስስሩን አጠናክሮ እንደሚሰሩ አብራርተዋል።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ