Postlar filtri


ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጥር 02/2017 ዓ.ም (BHU)

ማስታወቂያ
የመውጫ ፈተና ለሚትጠባበቁ መምህራንና እጩ ተመራቂዎች በሙሉ::

በክረምት መርሓ ግብር በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ድግሪ የትምህርት እርከን ማሻሻያ ስልጠና ስትከታተሉ የቆያችሁና፤እንዲሁም በቅዳሜ እና እሁድ የትምህርት መርሓ ግብር ስትከታተሉ ቆይታችሁ የመውጫ ፈተናውን ያልወሰዳችሁ ሠልጣኞች፤የመውጫ ፈተና የሚሠጠው ከየካቲት 10-12/2017 ዓ.ም ስለሆነ ፈተናው የሚመለከታችሁ አካላት በሙሉ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ አጥብቀን እናሳውቃለን፡፡
የአካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት


Bule Hora University Tuesday, January 7, 2025 (BHU)
To instructors,Students,admin.staffs and to all an interested individuals of our university.
This is to inform you that you are cordially invited to participate on the occasion of the public speech that will be presented by doctor Ayele Kebede on Jaunary 9/2025 at 9 AM that held in Oda Hall.
The detail and related program of the events are as follow.


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 28/2017


ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም (BHU)
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የዕቅድ ዝግጅት፤ክትትል;ግምገማና ሪፖርት አቀራረብን በተመለከተ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ፡፡ Yuunivarsitii Bulee Horaatti Guyyaa 26/2017(BHU)
Yuunivarsitii Bulee Horaatti Leenjiin qophii karoora,hordoffii,madaalii fi gabaasaa irratti hubannoo cimsu kenname.


ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 24/2017
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ በ2017 ዓ.ም ሊተገበሩ የሚገቡ ቁልፍ ዉጤት አመላካች ሥራዎችና ተግባራት ዙሪያ ከየዘርፉ ም/ፕሬዝዳንቶች ጋር የሥራ ዉል ተፈራረሙ፡፡
********************************* ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.bhu.edu.et/
ቴሌግራም -https://t.me/BuleHoraUniversity
ፌስቡክ - https://facebook.com/BuleHoraUniversity
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ


ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 23/2017
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ክረምት ወቅት ላከናወነዉ በጎ አድራጎት ሥራዎች በሰላም ሚኒስቴር በኩል የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል፡፡
****************
በሰላም ሚኒስቴርና በትምህርት ሚኒስቴር የበላይ አስተባባሪነት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃ በክረምቱ ወቅት የተለያዩ በጎ አድራጎት ሥራዎች እንዲሰሩ የተላለፈዉን ጥሪ ተከትሎ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተቋሙን ማህብረሰብ በማሳተፍ ላከናወነዉ በጎ አድራጎት ሥራዎች እና ላስመዘገበዉ ዉጤት በሰላም ሚኒስቴር በኩል የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ


ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም (BHU)
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ‹‹Statistical Package for the Social Sciences (SPSS) and AMOS ›› በሚል ርዕስ ለመምህራን የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ፡፡


ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም (BHU)
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህብረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት YOLK ከተባለው ግብረሰነይ ድርጅት ጋር በመተባበር በምዕራብ ጉጂ ዞን ሀምበላ ዋመና ወረዳ በጮርሶ ሶዱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት በፀሐይ ሃይል የሚሠራ የሶላር ኃይል ማመንጫ አገልግሎት አስጀመረ።
****************
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህብረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት YOLK ከተባለ ከደቡብ ኮሪያ ድርጅት ጋር በመተባበር በምዕራብ ጉጂ ዞን በሀምበላ ዋመና ወረዳ የኤሌክትርክ ኃይል ካልተዳረሰባቸው ት/ቤቶች አንዱ በሆነዉ ጮርሶ ሶዱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፀሐይ ኃይል የሚሠራ ሶላር ዲሽ በመግጠም ትምህርት ቤቱንና ማህብረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት የግብረሰናይ ሥራን ለመሥራት ‹‹SOLAR COW››የሚል መጠሪያ ካለው ሌላ ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት ተፈራርሞ ወደ ስራ እንደገባ ታውቋል።
የሶላር ኃይል ማመንጫው ሊገሳ ዋናው ዓላማ የተማሪዎችን መጠነ ብክነት ለመቀነስ፣የአከባቢው ማህበረሰቡና ቤተሰቦቻቸው በማታ የመብራት ሃይል እንዲያገኙ ለማድረግ ሆኖ በሌላ በኩል የትምህርት ጥራትንም ለመደገፍና ማሻሻል ላይ ያተኮረ ነዉ።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.bhu.edu.et/
ቴሌግራም -https://t.me/BuleHoraUniversity
ፌስቡክ - https://facebook.com/BuleHoraUniversity
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ



9 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.