Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በአሜሪካ በአንዲት የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን ፓስተሩ እየሰበከ እያለ አንድ የተቀባበለ ሽጉጥ የያዘ ወጣት በፓስተሩ ላይ ሽጉጡን ቃታውን ደጋግሞ ቢስብም ሽጉጡ አልሰራም ፣ አልተኩስም አለው። ከታች በቪዲዮ እንደምትመለከቱት የተቀባበለ ሽጉጥ በፓስተሩ ላይ ሽጉጡን ደጋግሞ ሲሞክር ይታያል ነገር ግን በሰባት እጥፍ ከሚነደው እሳት ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ አብድናዶን ያዳነ አምላክ ፓስተር ግሌን ጀርመኒ ጌታ አምላካችን ኢየሱስ ታድጎታል።
👇
ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ እውነተኛ ታሪክ በኢትዮጲያ የተከሰተ እንንገራችሁ የቀድሞ ስሟ ሀገርማርያም ወይም ቡሌ ሆራ የአሁን መጠሪያዋ በሆነች ከተማ ዙሪያ ባለች በአንዲት ገጠር አንድ ወንጌላዊ ለወንጌል አገልግሎት ተጉዞ ወንጌልን ሰብኮ በአንድ አርሶ አደር ቤት ይተኛል።
ጎረቤታቸው እንዴት ይሄን ሰው በቤታቸው ያሳድራሉ ይሄን ሰው መግደል አለብኝ ብሎ ያስባል ማታ ሁሉም ሲተኙ ወንጌላዊ በተኛበት ቦታ መሳሪያውን በወንጌላዊው ላይ ደቅኖ ሊተኩስ ቃታውን ሳበ ግን አልተኩስም አለው ደግሞ ሞከረ እንቢ አለው በሁኔታው በመገረም ራቅ ብሎ ሄዶ ጥይቱን ሲሞክር ይተኩሳል ሲነጋም ወንጌላዊው ባደረበት ቤት በመምጣት እያለቀሰ ማታ ሊገለው እንዳሰበ ነገር ግን አንተ የምታመልከው የምትሰብከው አምላክህ አድኖሃል የአንተን አምላክ አመልካለሁ ብሎ ንስሐ ገባ ጌታ ኢየሱስን የግል አዳኙ አድርጎ ተቀበለ ይህ ብቻ አልበቃ ብሎት መኖሪያ ቤቴን ለቤተክርስትያን ሰጥቻለሁ በማለት በመኖሪያ ቤቱ ላይ ዛሬ ትልቅ ቤተክርስትያን አለ ። ክብር ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እግዚአብሔር።
“በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር።”
ኢሳይያስ 54፥17