የዳሸን ባንክ 29ኛ ዓመት የምስረታ በዓልና የሠራተኞች ቀን እየተከበረ ይገኛል።
ዳሸን ባንክ የተመሰረተበት 29ኛ ዓመት እና የሠራተኞች ቀን የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እና ሠራተኞች በተገኙበት በሚሊንየም አዳራሽ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ባደረጉት ንግግር ዳሸን ባንክ በሠራተኞቹ ያልተቆጠበ ጥረት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ገልፀዋል። ለዚህም ለሁሉም ሠራተኞች የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
በዳሸን ባንክ ለ25 ዓመታት ላገለገሉ ሠራተኞች የምስጋና የምስክር ወረቀትና የወርቅ ቀለበት ተበርክቶላቸዋል።
የዋና ስራ አስፈፃሚው ልዩ ተሸላሚ የሆኑት የባንኩ ትሬዠሪ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ አንዷለም በለጠ በተመደቡባቸው ቦታዎች ሁሉ በትጋትና ያለ ጊዜ ገደብ በማገልገላቸውና ለባንኩ ስኬታማ የስራ አፈፃፀም ላበረከቱት አስተዋጽኦ የወርቅ ቀለበት ተሸላሚ ሆነዋል።
የዳሸን ባንክ 29ኛ ዓመት የምስረታ በዓልና የሠራተኞች ቀን በሌሎች የባንኩ ቀጠና ፅህፈት ቤቶች አማካኝነት ከአዲስ አበባ ውጪ ይከበራል።