የሁላችንም!
********
ብዙ ህብር ያላት ኢትዮጵያ በተለይም በወርሃ መስከረም እንደ ፀደይ ትደምቃለች።
መስከረም ለኢትዮጵያውያን ከወርነት ባለፈ ልዩ ትርጉም አለው፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከስጋት ወደ ተስፋ የመሸጋገሪያ ተናፋቂ ጊዜ ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን ከክረምት ወደ ፀደይ ሲሸጋገሩ አዲሱን ዘመን በሠላም ለመዋጀት ጸብን በእርቅ፣ ቂምን ደግሞ በይቅርታ አሽረው ለአዲሱ ዘመን ላደረሳቸው ፈጣሪ ምስጋና ያቀርባሉ፡፡
የመስከረምን መጥባት በምስጋና ከሚቀበሉ የሀገራችን ህዝቦች መካከል የኦሮሞ ህዝብ አንዱ ነው፡፡
የኦሮሞ ህዝብ ወደ አዲስ ዓመት ሲሸጋገር ከፈጣሪው ስለተሰጠው አዲስ ጊዜ፣ ፀጋ፣ ሰላም እና በረከት እርጥብ ሳር ይዞ ወደ ወንዝ ዳር በመውረድ ሆያ…መሬ …ሆ እያለ አምላኩን ያመሰግናል።
ይህ ክብረ በዓል በየዓመቱ ሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ አርሰዴን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በድምቀት ይከበራል።
ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ወደ ቢሾፍቱ ያቀኑ የበዓሉ ተሳታፊዎች ኢሬቻ የምስጋና ቀን በመሆኑ የሁሉም በዓል መሆኑን ለኢቢሲ ሳይበር ተናግረዋል፡፡
ኢቢሲ ሳይበር ያነጋገራቸው ከወላይታ፣ ከጋሞ እና ከሲዳማ የመጡ ወጣቶች በቢሾፍቱ የገጠማቸው የህዝቡ ደግነት እና እንግዳ ተቀባይነት በእጅጉ እንዳስደነቃቸው ገልጸዋል፡፡
ወጣቶቹ በዓሉን በአብሮነት እና በወንድማማችነት ስሜት በሠላም ማክበር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
በናርዶስ አዳነ