በ2017 ተቋማዊ ነፃነትን የጠበቀ የፍትህ ስርዓትን ለማጠናከር ይሰራል - የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት
*****************
የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2017 ዓ.ም መደበኛ የዳኝነት የስራ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር በመከናወን ላይ ይገኛል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረቱ በ2016 በርካታ ሪፎርሞች መደረጋቸውን አስታውሰው፤ በተለይም በቴክኖሎጂ የተደራጀ አሰራር በሰፊው መተግበሩን አንስተዋል።
በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በተስተዋሉ ግድፈቶች ላይ እርምት መወሰዱን ያነሱ ሲሆን ከተለያዩ ተቋማት በጋራ ተሰርቷል ብለዋል።
በ2017 ዓ.ም ተቋማዊ ነፃነትን የጠበቀ የፍትህ ስርዓትን ማጠናከር፣ ለዳኞች ምቹ የስራ ሁኔታ መፍጠር፣ የተጠያቂነት ስርዓትን በአግባቡ መተግበር፣ የሽግግር ፍትህ ልዩ ችሎትን ማቋቋምና ሌሎችም የማሻሻያና አዳዲስ አሰራሮች በፍ/ቤቶች ይከወናሉም ነው ያሉት።
ይህን ለማሳካትም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትጋት እና በስነ-ምግባር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
በሰለሞን ከበደ