በኬንያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ ሦስት ሰዎች ሞቱ
*******
በኬንያዋ የባሕር ጠረፍ ማሊንዲ ግዛት አንድ ቀላል አውሮፕላን በመውደቁ መሬት ላይ የነበሩ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው የፖሊስ ባለሥልጣን ተናግረዋል።
የአውሮፕላኑ አብራሪ እና በበረራ ሥልጠና ላይ የነበሩ ሁለት ተማሪዎች አደጋው ከመከሰቱ በፊት ከአውሮፕላኑ ላይ ዘልለው የወጡ ሲሆን፤ በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያትም ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሆነ ታውቋል።
ፖሊሶች የአደጋውን መንስኤ እየመረመሩ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳይከሰቱ በአውሮፕላን ማረፊያው ያለው ቅድመ ጥንቃቄ መጠናከር እንዳለበት የአካባቢው አፈ ጉባኤ ራሺድ ኦዲአምቦ ለአሶሺየትድ ፕሬስ ተናገረዋል።