ኢትዮጵያ ጠላቶቿን እያንበረከከች ሉዓላዊነቷን አስከብራ የምትቀጥል ሀገር ናት - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
********************
ኢትዮጵያ ጠላቶቿን እያንበረከከች ሉዓላዊነቷን አስከብራ የምትቀጥል ሀገር መሆኗን የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል፡፡
ፊልድ ማርሻሉ ከዓድዋ ጀግኖች የድል እሴትን የወረሰው ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ላይ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚቃጣ ጥቃትን መመከት የሚያስችል አስተማማኝ ቁመና መገንባቱን ገልጸዋል፡፡
“ከዓድዋ ድል የምንማረው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዘብ መቆምን ነው” ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፤ ድሉ የቅኝ ግዛት ዓላማ አራማጆችን ቅስም የሰበረ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የዓድዋ ድል የጥቁር ህዝቦችን በራስ መተማመን የጨመረ መሆኑንም አውስተዋል፡፡
“እኛ የዓድዋ ልጆች በዚህ ድል መኩራት ብቻ ሳይሆን የአያቶቻችንን የአይበገሬነትና የድል አድራጊነት መንፈስ በመውረስ የሀገርን ሉዓላዊነትና ሰላም ማስቀጠል አለብን” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
129ኛው የዓድዋ ድል በዓል "ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል" በሚል መሪ ሐሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በመከበር ላይ ይገኛል።