ያሬዳውያን


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


የየበዓላቱ ስርአተ #ዋዜማ ፤ #ማህሌት ፤ #ወረብ ከ7 ቀናት እንዲሁም የየሳምንቱ መዝሙራት እና ምስባክ በጽሑፍ እና በድምጽ የሚቀርቡበት ቻናል ነው
#ሁሉም_ነገር_ስለ_ማህሌት
ማህሌታውያን ቻናሉን share ያርጉ
ጥያቄ አስተያየት በግሩፓችን ይላኩ 🙏
እናመሰግናለን

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ሰዋስወ ግዕዝ dan repost
ከ118 ዓመት በፊት በበርሊን ዩኒቨርስቲ የግዕዝ እና የአማርኛ ቋንቋዎች መምህር አለቃ ታዬ ገብረማርያም እኝህ ነበሩ።

6.2k 0 17 23 193

ሰላም ለኪ እያለ(2)
ሃርና ወርቁን ስታስማማ
የገብርኤል ድምጽ ተሰማ
ተሰማ የመላኩ ድምጽ ተሰማ
ተሰማ የገብርኤል ድምጽ ተሰማ
አዝ፥
ውሃ ስትቀጂ ክንፉን እያማታ
ሊያበስርሽ የመጣው በታላቅ ደስታ
ከሞገስሽ ብዛት ከሞገስሽ ብዛት ሲታጠቅ ሲፈታ
አቅርቦልሽ ነበር የክብር ሰላምታ
አዝ፥
የምስራቹን ቃል ሚስጥር ተሸክሞ
ገብርኤል ተላከ ሊያረጋጋት ደግሞ
እርጋታ ተሞልታ እርጋታን ተሞልታ ነገሩን መርምራ
የመላኩን ብስራት ሰማችው በተራ
አዝ፥
ይደሰታል እንጂ መንፈሴ ባአምላኬ
በምስጋና ሳድር ዘወትር ተንበርክኬ
ሃሳቤ ለቅጽበት ሃሳቤ ለቅጽበት
ሌላ መች ያስባል
ለኔ ልጅን መውለድ እንዴት ይቻለኛል
አዝ፥
ካአንቺ ሚወለደው ለዑል ነው ክቡር
የተመሰገነ በሰማይ በምድር
ሚስጥሩ ሃያል ነው ሚስጥሩ ሃያል ነው
ይረቃል ይሰፋል
ካንቺ በቀር ይሄን ማን ይሸከመዋል
አዝ፥
እጹብ ነው ድንቅ ነው አንቺን የፈጠረ
አንቺን በመውደዱ ሰውን አከበረ
አለም ይባረካል አለም ይባረካል
በማእጸንሽ ፍሬ
ክብርሽን አልዘልቅም ዘርዝሬ ዘርዝሬ
አዝ፥
ሰላም ለኪ እያለ(2)
ሃርና ወርቁን ስታስማማ
የገብርኤል ድምጽ ተሰማ
ተሰማ የመላኩ ድምጽ ተሰማ
ተሰማ የገብርኤል ድምጽ ተሰማ


እሑድ - ዳግም ትንሳኤ

👉ዳግም ትንሣኤ ማለት ምን ማለት ነው?

በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ "ዳግም ትንሣኤ" ተብላ ትዘከራለች፣ ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ "ሰላም ለሁላችሁ ይኹን" በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፣ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት  "በኋላ እናንተ 'አየን' ብላችሁ ልትመሰክሩ፣ ልታስተምሩ፣ እኔ ግን  'ሰምቼአለሁ' ብዬ ልመሰክር፣ ላስተምር አይኾንም እኔም ካላየሁ አላምንም " አለ

👉ስለዚህም የሰውን ሁሉ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ  "ሰላም ለሁላችሁ ይኹን!"  በማለት በመካከላቸው ቆመ፣ ቶማስንም "ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን፣ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ" ብሎ አሳየው፡፡

👉እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ "ጌታዬ አምላኬ ብሎ መስክሮ የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ 'ዳግም ትንሣኤ' ተብሎ ይጠራል ይከበራል ዮሐ.20፥24-30

👉ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ ዳግማይ ትንሳኤ ተብሏል ።

👉ሁለተኛ ለምን ተገለጠ?

ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን፦ የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጎኔን ዳስስ ብሎታል ።

👉ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑን በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል፣ ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው፣ ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች (የዳሰሰች) እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች፣ እስከ አሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ።

ሰንበትን ሊያጸናልን የአይሁድ ሰንበት፣ እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም (ቅዳሜ) ናትበሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት፣ ከሙታን መካከል የተነሳባት፣ አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት (ዳግማይ ትንሳኤ)፣ መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች።

👉ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት፣ እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን) የምናሳልፈው ማለት አይደለም፣ እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው።

ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት፣ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል፣ በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ።

"ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው" ዮሐ.20፥29

👉አንድም ዳግም ማለት ሁለተኛ ማለት ነው፣ ጌታ ሁለት ጊዜ አልተነሳም፣ ዳግም የተባለው የትንሳኤው ስርዓት እና ቃለ እግዚአብሔር በዚህ ቀን ስለሚደገም ነው።

👉አንድም መነሳቱን ለ11ዱ ደቀመዛሙርት እንበለ ቶማስ ቢገልጥላቸው አምነው ለቶማስ ቢነግሩት የተቸነከሩ እግሮቹንና እጆቹን ካላየሁ ጣቴን በተወጋ ጎኑ ካላገባሁ አላምንም ብሎ ነበርና በሳምንቱ ያምን ዘንድ ቶማስ ባለበት
ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠላቸው፡፡ ዮሐ.20፥26 እስከ ፍጻሜው


👉ቤተክርስቲያን ይህንን መገለጥ ዳግም ትንሳኤ ትለዋለች፡፡

ፈጸምነ ይባላል ይህ ስያሜ ደግሞ የፋሲካን በዓል አከበርን ስርዓቱን ዛሬ ፈጸምን ለማለት ነው፡፡

አግብኦት ግብር ይባላል በዮሐ 17፥ 1 ጀምሮ በተገለጠው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት  ጌታ " አባ ወአቡየ ግብረ ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ " ያለውን መዘምራን በቅዳሴ ማጠቃለያ አካባቢ ስለሚዘምሩበት ነው፡፡

👉ቶማስ ለምን ተጠራጠረ ?

መጠራጠሩ ስለ 2 ነገር ነው፦

1.ሰዱቃዊ ስለነበረ ሰዱቃውያን ደግሞ ትንሳኤ ሙታን የለም ብለው የሚጠራጠሩ ናቸውና ሳላይ አላምንም ብሎ፤

2.ሌሎች ሐዋርያት ትንሳኤውን ሲሰብኩ ተነስቶ አይተነዋል ሲሉ እርሱ ደግሞ መነሳቱን ሰምቻለሁ ብሎ ማስተማር ስለሌለበት ለማየት ሳላይ አላምንም አለ፡፡

👉ጌታ የተገለጠላቸው ደጆች ተዘግተው ሳሉ ነበር ፡፡ ዮሐ.20፥26 ገብቶ ሰላም አላችሁ አስታረቅኋችሁ አላቸው፡፡

👉በተዘጋው ቤት እንዴት ገባ ?

ኤልሻዳይ ስለሆነ ሳራ ማሕጸኗ ተዘግቶ መውለድ ባልቻለች ጊዜ ልጅ የሰጣት ኤልሻዳይ ነው፡፡ ዘፍ.17፥1

ሀና ኤልሳቤጥ ሌሎችም እንዲሁ፡፡ ሉቃ 1፥ 37 እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር እንዲል ረቂቅ መለኮት ስጋን እንደተዋሃደ ለማጠየቅ ፦ በተዘጋ ቤት ገባ፡፡

ዛሬም ደጆች ቢዘጉም ጌታ ይመጣል ብዙ ሰዎች በሕመም ተይዘው የመዳን ደጃቸው ተዘግቶ ሳለ ጌታ የሚመጣው ዮሐ.5፥3-12

✍ነፍሳት በዲያብሎስ ቁራኝነት ተይዘው ገነት ተዘግታ ሳለ ኢየሱስ መጥቷል
      ሉቃ.2፥9

እስራኤላውያን የግብጽ ባርነት ቢያይልባቸው የነጻነት ደጃቸው ቢዘጋባቸውም ጌታ መጥቶ አድኗቸዋል  ዘጸ.3፥1-8

ሲወጡስ ከፊት ቀይ ባህር ከኀላ ፈርኦን ከቀኝና ግራ ገደልና ዳገት ቢገጥማቸውም አምላክ ደርሶላቸው አድኗቸዋል ዘጸ.14፥1

ለሶስና ከውግረት አድኗታል ሶስና 1፥1-23

ለአይሁድ (ዕብራውያን) ሐማ ያሳወጀውን የሞት ፍርድ ቀይሮላቸዋል
      አስቴር 1-10


ለሶስቱ ሕጻናት (ሰለስቱን ደቂቅ) ከእሳት አውጥቷቸዋል ዳን.3፥17

አላዛርን ከሞት አስነስቶታል ዮሐ.11፥1-48

ስለዚህ ሁሉን ቻይ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ምን ደጅ ቢዘጋ መክፈት ይችላልና እንመነው፣ እርሱን አምኖ ተስፋ ሚያደርግ አያፍርም መዝ 24፥3 ተብሎ ተጽፏልና፡፡ ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።

👉 ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ያሉትን ዕለታት ስያሜና ለምን እንደሚከበሩ ከብዙ በጥቂቱ አይተናል!!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር፡፡ አሜን
!!!




ከወዲሁ መርኃ ግብራችሁን አስተካክሉ !

በደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ማኅሌቱን ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ

@EOTCmahlet

8.7k 0 14 13 50

#የመጽሐፍ_ጥቆማ_ስለ_ማህሌት _ማወቅ_ለምትፈልጉ_ማህሌታውያን

🫴 "ያሬድና ዜማው" 🕊


በዚያ መጽሐፍ 👇
                       
                         #ድጓ  ምንድን ነው?
                       #አቋቋም ምንድን ነው?
                    #ተክሌ አቋቋም ምንድን ነው?
                         #ጎንደሬ አቋቋም?
                         #ሳንኳ አቋቋም?
                         #ላይ ቤት አቋቋም
                         #ታች ቤት አቋቋም
#ዝማሬ ምንድ ነው?
                        #ምዕራፍ  ምንድን ነው  ??

የእነዚህና መሰል ጥያቄዎችን ከነአገልግሎታቸው በሚገባ ተብራርቶ ያገኙታል "ያሬድና ዜማው"
የሚል መጽሐፍ ፈልገው ያንብቡ ሙሉ መልስ ያገኛሉ 🤲

ያሬዳውያን

#ሁሉም_ነገር_ስለ_ማህሌት

ውድ ማህሌታውያን ይህን ቻናል ለሌሎች ይደርስ ዘንድ #ሼር በማድረግ ይተባበሩን፤ እናመሰግናለን።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet

አስተያየት ካለ @eotcmahletawian ላይ

👉Telegram channel👇
     @EOTCmahlet


👇 tiktok
https://www.tiktok.com/@eotcmahlet?_t=8qHmxqNqF77&_r=1
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


👇 instagram
https://www.instagram.com/eotcmahlet?igsh=ZzNvZnBybnJmYWN3


አድሚኖቹን በቀጥታ ለማግኘት bot 👉 @Yaredaweyan_bot

🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈                 
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @EOTCmahlet
    #Join & #share
ያሬዳውያን on TikTok
@eotcmahlet 7743 Followers, 87 Following, 59.4k Likes - Watch awesome short videos created by ያሬዳውያን


እንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ ወሪዳ ምድረ ቆላ
በናዝሬት ወበገሊላ
ገብርኤል መጽአ እንዘ ይረውጽ በሰረግላ
ክንፉ ክንፉ ክንፉ ፀለላ
ተፈስሒ ተፈስሒ ለድንግል ይቤላ

ወደ ቆላው ምድር ወርዳ እመቤታችን ወርቅን ከሐር ጋር አስማምታ እየፈተለች ሳለች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ እየሮጠ መጣ፣ ክንፉንም እያማታ እየሰገደ ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ አላት

ድንግልን ካበሰረ ከራማው ልዑል ከቅዱስ ገብርኤል ረድኤቱን በረከቱን ያሳድርብን🤲

የመልአኩ ጥበቃ አይለየን 🤲

መልካም ሰንበተ ክርስቲያን ይሁንላችሁ

አስተያየት ካለ @eotcmahletawian ላይ

👉Telegram channel👇
     @EOTCmahlet

👉YouTube channel👇
https://www.youtube.com/@EOTCmahlet/featured#

    #Join & #share


🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈                 
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @EOTCmahlet
    #Join & #share

 












❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️
ድኅረ ቁርባን ዘዳግም ትንሳኤ
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
አቡን
በ፪ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ በከመ ይቤ እግዚእነ
በወንጌል፤ ግብረ ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ፤ወነገርኩ ስመከ ለሰብእ፤ ግ፤ አባ ወአቡየ ሰብሐኒ በስብሐቲከ፤ ግብረ ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ፤ ግብረ ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ።

አቡን
በ፬ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ይቤ ክርስቶስ ነገርኩ ስመከ ለሰብእ፤ ከመ ያእምሩከ ለአምላክ ሕያው፤ ቀድሶሙ አባ ከመ ይኩኑ ቅዱሳነ ዘእምኀቤከ፤ ኀበ ሀሎኩ አነ ህየ የሀልው ምስሌየ፤ ወይንግሩ ስብሐትየ ወዘአቡየ፤ ዘሀሎ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም።


💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
ስርዓተ ማኅሌት ዘሚያዝያ ማርያም ወርሀ በዓል
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ...
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ ለሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
አበው ቅዱሳን፤እለ በሥላሴ አግመሩ ሕማማተ መስቀል፤ተስፋ ነፍሶሙ ረከቡ በማርያም ድንግል።

ዚቅ ዘላይ ቤት
እንዘ ይቀውማ ኀበ መስቀሉ፤ማርያም እሙ ወማርያም መግደላዊት፤ተሰቅለ፤ወሐመ በእንቲአነ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet

በላይ ቤት ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክር ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረት ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእም ቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡

ዚቅ
ዘመንክር በአርያሙ እግዚአብሔር ስሙ፤ዝንጓጌ መስቀል አመ ተወፈየ ነዋ ወልድኪ ይቤላ ለእሙ ፤ፍቅረ ዮሐንስ ኢያንተገ በጊዜ ሕማሙ፤ላዕለ ጒንደ መስቀል አመ ውኅዘ ደሙ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።

ዚቅ
ሃይማኖት ተናገራ ኢየሱስ ወይቤላ፤በሐኪ ማርያም መግደላዊት፤ተንሥአ እምነ ሙታን።

ዚቅ ዘላይ ቤት
ቤዝ ተላዊተ ኦሬያሬስ ቤዝ፤ጥቀ ሐዋዝ፤ማርያም አርዝ ዘቤተ ትንሣኤ በለዝ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክአ ማርያም
ሰላም ለመላትሕኪ በእሳተ አንብዕ እለ ዉዕያ፤ጊዜ ሰቀሉ በኩረኪ ዉሉደ ራኄል ወልያ፤ማርያም ድንግል ለነፍስየ ደብረ ምስካያ፤አድኅንኒ እምአፈ ደም ዘአናብስተ ሐቅል አርአያ፤ከመ ማኅፈር ጠቢብ ወምእመን ኬንያ።

ዚቅ
በከመ በከየት እሙ ንዑ ንብኪ አንብዐ መረረ፤ከመ ኢይኅድገነ በትንሣኤሁ።

ዚቅ ዘላይ ቤት
አርመመት በእንብዕ ሶቤሃ፤ተዘኪራ መሐላ፤ወኪዳነ ዘክርስቶስ ዘተካየደት ምስሌሁ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክአ ማርያም
ሰላም ለአማዑትኪ ነበልባለ ኀዘን ዘአውዐዮ፤አመ ወዐለ ወልድኪ ስቁለ በቀራንዮ፤ማርያም ድንግል ፀምረ ጠል ዘተነብዮ፤ጌጋይየ ለአስተርሥርዮ እንተ አልብኪ ተፈልዮ፤በሥርዓተ ካህን ላዕሌየ አንኂ ጸልዮ።

ዚቅ
ሐፃቤ ርስሐትየ ይኩን አንብዕኪ ዘአንጸፍጸፈ ዲበ ምድር፤አመ ወልድኪ ይፄዓር፤በመልዕልተ መስቀል ጊዜ ቀትር፤እንዘ ያመሐፅን ኪያኪ እም ኀበ ረድኡ ዘያፈቅር።

ዓዲ ዚቅ
አዘክሪ ድንግል ለወልድኪ ዕርቃኖ፤አመ ዕለብዎ አይሁድ ክዳኖ፤ለአማዑተ ከርስኪ ነበልባለ ኀዘን ዘአርስኖ።

ዚቅ ዘላይ ቤት
መድኃኔዓለም ወልድኪ ሥጋ ዚአኪ ዘለብሰ፤ ሐፃውንተ መስቀል ተአገሰ፤ በዓውደ ጲላጦስ ተወቅሰ አማዑትኪ ተከዉሰ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አንገርጋሪ፦
እንዘ ይቀውማ ኀበ መስቀሉ፤ማርያም እሙ ወማርያም መግደላዊት፤ተሰቅለ፤ወሐመ በእንቲአነ።

አመላለስ፦
ተሰቅለ ወሐመ በእንቲአነ/2
ወሐመ በእንቲአነ ወሐመ በእንቲአነ/2/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet

እስመ ለዓለም ዘዘወትር
ማዕከለ ክልኤ ፈያት ተሰቅለ ወአውረድዎ እምዲበ መስቀል፤ወቀበርዎ ሀገረ ኀበ ምሕዋረ አንስት፤ማርያም ወላዲተ አምላክ፤ወማርያም መግደላዊት።


🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈                 
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @EOTCmahlet
    #Join & share #


GC Program.pdf
1.8Mb
✝ምርቃት✝


ዝርዝር መርሐ ግብሩን ከውስጥ ገብተው ያንብቡ

"በጳውሎስ ኦንላይን ቅኔ ቤት"


°ባሕረ ሐሳብ ቀዳማይ...16 
°ባሕረ ሐሳብ ካልዓይ.....18 
°ግእዝ ቀዳማይ............6 
°ግእዝ ካልዓይ............11 
°ቅኔ..........................7
በድምሩ 58 ተማሪዎች ይመረቃሉ።
ሚያዝያ 19/2017 ዓ.ም
ከምሽ 3:00-6:00

✝በቴሌግራም ኦንላይን
ቀጥታ ሥርጭት በነጻ ይከታተሉ

ለበለጠ መረጃ
በቴሌግራም
@pawli37
በስልክ
+251915642585


ዐዲሱ ቻናል ጠቃሚ ነው
https://t.me/GeezPoetry

ኹሉንም ትምህርቶች በቅደም ተከተል የሚላክበት ስለኾነ ይቀላቀሉ። ቅኔ በቀላሉ ይወቁ

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
የምርቃት መርሐ ግብሩን

➡️ለአብነት ትምህርት ቤቶች
➡️ለግቢ ጉባኤያት
➡️ለሰንበት ትምህርት ቤቶች
➡️ለመንፈሳዊ ሚዲያዎች

ወዘተ በመላክ ጥሪ እንድታስተላልፉልን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏


ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች የቀጣዮቹን በዓላት ማለትም

1.ግንቦት 1 ቅድስት ልደታ ለማርያም
2.ግንቦት 11 በዓለ ቅዱስ ያሬድ
3.ግንቦት 12 በዓለ ተክለሃይማኖት ጻድቅ
4.ግንቦት 21 በዓለ ቅድስት ድንግል ማርያም (ደብረ ምጥማቅ )

ስርአተ ዋዜማ እንዲሁም ስርአተ ማህሌት ቀደም ብለን እንልካለን ይጠብቁን



@EOTCmahlet

share

11.6k 0 11 18 149



ወይቤ አምላክ ተንሥአ፣
ወይቤ አምላክ ተንሥአ ወይቤ አምላክ ተንሥአ




እናት አለኝ

እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ
ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ
ለዘላለም ንፅሕት በመሆኗ
ከእኔ ጋር ነው ሕያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሐዘኔን አልፌ
አፅናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ
ከጥፋት ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በሕይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ
በእናትነት ሕይወቴን ጎብኝታ
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ
ሰንሰለቴ ከእግሬ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ
ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

17.5k 0 175 30 260
20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.