👉የመሬት መንቀጥቀጥ (Seismic load)
🏷የመሬት መንቀጥቀጥ በአንድ የግንባታ ንድፍ (በተለይ በስትራክቸራል ዲዛይን ሥራ) ሂደት ከግምት ውስጥ የሚገባ ከዋናዎቹ ጫናዎች (loads) መካከል ነው።
ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ማባዣ (seismic factor) ለተለየያዩ አካባቢዎች የተቀመጠ ሲሆን ማብዣ ቁጥሩ የሚወሰነው ቀድሞ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ታሪክ (Historical records) መሰረት ነው።
በዚህ አግባብ በቀድሞው EBCS ምትክ የተቋቋመው በኢትዮጵያ የልኬት ኤጀንሲ (Ethiopian Standard Agency) በ2015 (እ.ኤ.አ) ለስትራክቸራል ዲዛይን ሥራ ከግምት ውስጥ እንዲገባ ባዘጋጀው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረትን በወሰነበት CES 160 ልኬት መሰረት ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ማባዣ አምስት (5) እንዲሆን ያረቀቀ ሲሆን ይህ ልኬት የተሰጣቸው አካባቢዎች፦
🏷1ኛ)፦ በአፋር ክልል፦ አፍዴራ፣ አርጎባ ልዪ፣ አሳይታ፣ አዋሽ ሸለቆ፣ ዳልፋጊ፣ ዱብቲ፣ ዱሌቻ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ ሀደሌላ፣ ሰመራ፣ ሰሙሮቢና ገላሎ
🏷2ኛ)፦ በአማራ ክልል፦ አንኮበር፣ አንጾኪያ ገምዛ፣ አርቱማ ፉርሲ፣ ባሶና ወራና፣ መንዝ ግሼ፣ ጅሌ ጥሙጋ፣ ቀወት፣ መንዝ ጌራ፣ መንዝ ማማ፣ ሞጃና ወደራ፣ ወይን አምባ፣ ጣርማ በር ናቸው።
⭐️በእነዚህ አካባቢዎች ዙሪያ ያሉ አካባቢዎች የሀገሪቱ ስምጥ ሸለቆ ዞኖች ስለሆኑ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት የሚስተዋልባቸው ናቸው።
❇️ነገር ግን በዚህ ሰሞን የሚስተዋለው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በሬክታል ስኬል እስከ 5.2 የደረሰ መሆኑ ተዘግቧል።
⏺ይህ ማለት የሀገሪቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ልኬት ከተቀመጠው ስታንዳርድ ያለፈ ሆኖ የተመዘገበ ታሪክ ስለሆነ የስታንዳርድ (standard) ማስተካከያ ሊያስፈልገን ነው ማለት ነው።
💫የ FACEBOOK ገፃችንም ይወዳጁ👇
https://www.facebook.com/ethioconp