👉ከሰሚት-ፔፕሲ- ጎሮ እስከ ቦሌ ያለው መንገድ ለሳምንት ያክል ሊዘጋ ነው
🚧በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2ኛው ዙር እየለሙ ካሉት የኮሪደር ልማት መስመሮች መካከል የሰሚት-ፔፕሲ- ጎሮ እስከ ቦሌ መንገድ ከየካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሳምንታት ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
መስመሩ ለትራፊክ ዝግ እንዲሆን የተፈለገው ስራውን በፍጥነት በመጨረስ መንገዱን ለተጠቃሚው ክፍት ለማድረግ እንዲቻል መሆኑን ባለስልጣኑ አመልክቷል፡፡
በመሆኑም መንገዱ ተጠቃሚዎች ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከፔፕሲ - ጎሮ እና ከጎሮ - ፔፕሲ መንገድ በሁለቱም እቅጣጫ መንገዱ የሚዘጋ በመሆኑ ከፒፕሲ ወደ ጎሮ የሚጓዙ አሽከርከሪዎች በጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወደ ኢንዱስትሪ መንደር ቦሌ ወረዳ 11 በኩል ጎሮ የሚያገናኘውን መንገድ እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡፡
ከጎሮ ወደ ፒፕሲ የሚመለሱ ተጓዦች ደግሞ በጃክሮስ - ፊጋ- ሰሀሊተ ምህረት ወደ ዋና መስመር በመግባት መጠቀም እንደሚችሉም ባለስልጣኑ አስገንዝቧል፡፡
በተጨማሪ ሌሎች አማራጭ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡፡
ተገልጋዮች የመንገዱ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ለሚያሳዩት ትብብርም ባለስልጣኑ ከወዲሁ ምስጋና ማቅረቡን ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
@etconp