🔖TradingView በፕላትፎርሙ ወደ2500 ቀናት ገደማ እንደተጠቀምኩ አስታወሰኝ። ጊዜ ይነጉዳል። በእነዚህ ጊዜያት በትሬዲጉ አለም በተለይ ደግሞ በክሪፕቶከረንሲው መስክ ማየት ያሉብኝን ሁሉ ሁነቶች ከታች እስከታች አይቻለው ብል ማጋነን አይሆንብኝም። በአፍጢሜ ተደፍቻለው፤ ጣሪያ እስክነካ ዘልያለው፤ በቃኝ ለማለት ከጫፍ እስክድረስ አማርሬያለው፤ አፌን በእጄ እስክይዝና ከማስበው በላይ እንዳልም የሚያረጉ ትርፋማ ግብይቶችን አይቻለው፤ ብቻ ምን አለፋችሁ እጅግ በጣም ለብዙ ሁነቶች እማኝ ሆኛለው።
📌ቅሉ ግን 2500 ቀናት ከቻርት ጋር መፋጠጡ ሳይሆን በእነዚህ የከፍታ እና ዝቅታ ቀናት መያዝ ያሉብንን ነገራቶች ይዘናል ወይ? የሚለው ቁምነገር ነው።
🗣️እናማ ምን ልልህ ነው ሶቅራጠስ እንዳለው "እኔ የማውቀው አለማወቄን ነው።"
🎯ትሬዲንግ እጅግ በጣም ሰፊ፤ የማያልቅ፤ በየእለቱ የሚጎለብት እና በዛ ውስጥም የሚለዋወጥ ግን ደግሞ ካወክበት አይደለም ያንተና የቤተሰብህን የማህበረሰብ እና የቀዬህንም ኪስ በፋይናንሱ ነፃ ማውጣት የሚያስችልህ መስክ ነው። ትእግስት፤ የማወቅ ፍላጎት እና ጉጉት በስተመጨረሻም ትጋት ካሉህ እመነኝ አይደለም 2500 ቀናት በ250 ቀናትም ሚስጥሩን አውቀኸው ቁልፉን በእጅ ማስገባት ይቻልሀል።
⭐እማኝ ነኝና ወንድማዊ ምክሬን ታደምጠኝ ዘንድ ለመጠየቅ ወደድኩ - በትሬዲንጉ ዓለም ታገስ፤ ተማር ፤ ታትር!!! ያንን ካደረክ መልሱ እሩቅ አይሆንም።
💬በስተመጨረሻም: Alt Season የጀመረ ለመሠላችሁ ገና ምኑንም እንዳልጀመርነው ለማስታወስ እወዳለው። አለፍ ሲል ደግሞ ከሰሞኑ እንዳያችሁት አይነት ደም በደም የሆነ የገበያ ሁነት ከዚህ በፊትም የነበረና ያለ ሁነት ነው። የራሳችሁን ጥናት አድርጋችሁ የተለያዩ ጠንካራ የምትሏቸውን አልት ኮይኖች ምረጡ: ካፒታላችሁን ከፋፍላችሁ ግዙ: ሚያዚያና ግንቦት ላይ ተመለሳችሁ ተመልከቱት። It's simple as that.