Enat Bank


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


Enat Bank is a private commercial bank in Ethiopia. Enat Bank is established to provide banking service to all clients with special focus for women economy empowerment by providing financial and non-financial services.
ማን እንደ እናት!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri




እናት ባንክ ‹‹አዳዲስ የቢዝነስ ሥራ መሪዎችን ማሳደግ›› በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ በአሜሪካን ኢምባሲ በተካሄደው መድረክ ልምድና ተሞክሮውን አጋራ ፡፡
መድረኩ አለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ የተካሄደ ሲሆን፤በዚሁ መድረክ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች፣ኢንቨስተሮችና ወጣት ሴቶች ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ ሴቶች ያለቸውን የፋይናንስ አያያዝ፣የሴት የቢዝነስ ሥራ መሪዎችን አቅም በማጎልበት፣የንግድ ሥራን ማሳደግ፣የኢኮኖሚ ዕድገትን በማፋጠን ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ ልምዳቸውን አጋርተዋል፡፡
የእናት ባንክ የማርኬቲግ ኮሙኒኬሽንና የደንበኞች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር ወይዘሮ አክሊል ግርማ፤እናት ባንክ የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም ለማጎልበት እየሰራቸው ያሉ ተግባራትን በተመለከተ በማብራራት ያለውን ልምድ አጋርተዋል፡፡
የሴቶች አቅም ለመገንባትና ብቁ ሴት የቢዝነስ ሥራ መሪ ለማፍራት ቀጣይነት ባለው መልኩ በትብብር መስራት እንደሚያሰፈልግ ተናግረዋል፡፡
ባንኩ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበት እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
——————***——————
Follow us:
https://tiktok.com/@enatbank_tik
https://youtube.com/@enatbank
https://instagram.com/enatbank_ins
https://t.me/EnatBank_official
https://www.facebook.com/enatbank.eth
https://twitter.com/bankenat
https://www.linkedin.com/company/enat-bank-s-c
https://whatsapp.com/channel/0029Va5THJVKAwEhqj4NB40E
Website: https://enatbanksc.com








እናት ባንክ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅት ለሶስት ቀናት ባዘጋጀው ኤግዚቪሽንና ባዛር ተሳተፈ፡፡
ባንካችን  በቦታው በመገኘት  ምርትና  አገልግሎቱን አስተዋውቋል፡፡
ባንኩ  በአነስተኛና መካከለኛ  የንግድ ሥራ የተሰማሩ እናቶች ምርታቸውን ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ የገቢያ ትስስር  እንዲፈጥሩ የበኩሉን ድጋፍ አድርጓል፡፡ 
ኤግዚቪሽንና ባዛሩ የአለም  አቀፍ  የሴቶች  ቀን ምክንያት  የተዘጋጀ ሲሆን፣ ይህም የእናት ባንክ ምርትና  አገልግሎቱን እንዲያስተዋውቅ እንዲሁም እናቶች  በሀገር ውስጥ የተመረቱ አልባሳቶችንና ሌሎችንም ምርቶች እንዲያስተዋውቁ መልካም ዕድል ፈጥሯል፡፡       
ባንካችን  የሴቶችን  ኢኮኖሚያዊ  ተጠቃሚነት  ለማጎልበት ከሚሰሩ ተቋማት ጋር በመተባበር ድጋፉን አጠናክሮ  ይቀጥላል፡፡
——————***——————
Follow us:
https://tiktok.com/@enatbank_tik
https://youtube.com/@enatbank
https://instagram.com/enatbank_ins
https://t.me/EnatBank_official
https://www.facebook.com/enatbank.eth
https://twitter.com/bankenat
https://www.linkedin.com/company/enat-bank-s-c
https://whatsapp.com/channel/0029Va5THJVKAwEhqj4NB40E
Website: https://enatbanksc.com












እንኳን ለዓለም 0ቀፍ የሴቶች ቀን በሰላምና በጤና አደረስዎ!

እናት ባንክ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ለ114ኛጊዜ፣ በአገራችን ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሴቶችን ቀን (March 8) አስመልክቶ በአጋርነት ዐብረውት ከሚሠሩ የሕክምና ተቋማት ጋር በመተባበር፣ ለውድ ደንበኞቹ በልዩ የዋጋ ቅናሽ ለአንድ ወር የሚቆይ የሕክምና አገልግሎት ማቅርቡን ሲገልጽ ደስታ ይሰማዋል።

በመሆኑም፣ በመቅረዝ ሆስፒታል፣ በአዲስ ሕይወት ሆስፒታል፣ በዋሽንግተን የሕክምና ማዕከል እና በስዊዝ ዲያጎነስቲክስ ኢትዮጵያ ወደ ተሠኙት አጋር የሕክምና ተቋማት በመኼድ፣ ለዘላቂ ጤናዎ የቅድመ ምርመራና የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ በአክብሮት እንጋብዛለን። በ“እናት ጤና” የቁጠባ ሒሳብ ቤተ ሰብ ሲሆኑ፣ ከፍተኛ የወለድ ምጣኔና በልዩ የዋጋ ቅናሽ ጥራት ያለው ቀልጣፋ የሕክምና አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

ማን እንደ እናት!

እናት ባንክ





14 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.