ቅጠሎች
አንዳንድ በህይወት የሚገጥሙን ሰዎች ልክ እንደ ዛፍ ቅጠሎች ናቸዉ።ለጥቂት ወቅቶች ብቻ አብረዉን የሚቆዩ፣እንደ ዛፍ ቅጠል ሁሉ ከእኛ የሚፈልጉትን ከአገኙ በኋላ በሚገጥሙን ቀላል የህይወት ነፋስና ወጀብ ወቅት አብረዉን የማይዘልቁ፤ ጊዜያዊ ጥላ ለመሆን ብቻ ወደ ህይወታችን የመጡ፣ ልንተማመንባቸዉ የማንችል በቀላሉ የሚረግፉ ደካሞች ናቸዉ።
ቅርንጫፎች
አንዳንዶች ደግሞ በዛፍ ቅርንጫፍ ይመሰላሉ።እነዚህ አይነት ሰዎች ከቅጠሎችን የታሻሉና ጠንካሮች ናቸዉ። እንደ ዛፍ ቅርንጫፎች ሁሉ ጫናዎችን ተቋቁመዉ አብረዉን ሊመዝለቅ የሚሞክሩ ቢሆንም፣ነገር ግን ሙሉ በሙሉ እምነታችንን የማንጥልባቸዉና ከባድ የህይወት ወጀብ በገጠመን ሰአት ተገንጥለዉ የሚቀሩ አይነት ሰዎች ናቸዉ።
ስሮች
ጥቂት እንደ ዛፍ ስሮች የሆኑ ሰዎች ልናገኝ እንችላለን።እነዚህ ሰዎች ስር ለዛፉ ጥንካሬና ጤንነት እንደሚታትር ሁሉ የእኛንም ህይወት በደስታና በጥንካሬ እንድንመራና ቀጥ ብለን እንድንቆም የሚረዱን ፣ልክ እንደ ዛፍ ስር ሁሉ በህይወት የሚገጥሙንን ወጀቦች እንድንቋቋም የሚያደርጉን፣ የሚመግቡን፣የሚያጠጡን ልዩ የሆኑ ሰዎች ናቸዉ።
ዛፎች ብዙ ቅጠሎች፣ ቅርንጫፎችና ጥቂት ስሮች አሏቸው።የአንተን/ቺን ህይወት ተመልከቱ ምን ያህል ቅጠሎች፣ቅርንጫፎችና ስሮች አሏችሁ?እናንተስ በሌሎች ህይወት ዉስጥ የቱኛዉን ናችሁ?