እኩለ ለሊት አልፏል። እንቅልፍ በአይኔ መዞር ካቆመ ሰነባብቷል። ዞሬ ሳየው ገፅታው ሰላማዊ ነው። እሱ ብቻ ነው ወይስ ሁሉም ሰው ሲተኛ ያሳዝናል? እንደህፃን ያሳሳል።አተኛኘቱ ጥፋት የሌለበት ንፁህ ያስመስለዋል።
ዳሩ እሱ ምን አጠፋ?! አንደኛ ደረጃ ተማሪ ሆኜ ከመፅሀፌ ጀርባ የፃፍኩትን የ"ምርጥ ባል" ደረጃ በሙሉ ያሟላል።እኔ ነኝ የእሱን የምርጥ ሚስት ደረጃ ማሟላት ያልቻልኩት።
ችግሩ ማለቴ ችግሬ ምንድነው? መውደድ ረስቻለሁ ወይ ጠፍቶብኛል ነው። ብዙ ቦታ ልቤን አባክኜው ነው መሰለኝ አሁን ስመኘው የነበረው ሰው እግዜር እንኪ ሲለኝ መቀበል ያቃተኝ
የለመድኩት መከልከል ነው እድሌ ወስዶ የሚጥለኝ ጭራሽ እጣ ክፍሌ ካልሆነ ሰው ጋር ነበረ። እልል ያለ ፍቅር ውስጥ ነኝ ተዉኝ ብዬ ማወጅ ስጀምር ድንቅፍቅፉ እየበዛ ምናልባት ለእኔ ባይለው እያልኩ ያተኮሰችውን ልቤን ማብረድ ነበረ የለመድኩት። አሁን እንኪ ይኸው የተፈቀደልሽ ስባል በየት በኩል ልብ በግድ ውደድ ይባላል?!
አታለልኩት እንዳልል እዚህ ደረጃ ሳንደርስ ገና ጓደኝነታችን ድክ ድክ ማለት ሲጀምር ነግሬው ነበረ የሚሆን አይመስለኝም ብዬው ነበረ። "ለጊዜው የኔ ፍቅር ይበቃል በጊዜ ሂደት ትወጂኝ ይሆናል" ብሎ ነበር የጀመርነው ከዛስ?! ሁሉም አንድ አንድ ሲሉ ጓደኞቼ "እሱ ካመለጠሽ እድሜ ልክሽን ነው የሚያንገበግብሽ" እያሉ ሲያስፈራሩኝ
የሆነ እቃ ሊያቀብለኝ ቤቴ መጥቶ እያወራን በአጋጣሚ እናቴም መጥታ ተገናኝተው ትንሽ እንዳወሩ ልሂድ ብሎ ሲነሳ ካልቆየህ ብላው እኔን ረስተው ሲጫወቱ ውለው "አትጥፋ ታድያ" ብላው ሲለያዩ
የተቋጨ ነጠላዋን ደግማ እየቋጨች "ያው በጊዜ መሰብሰብ ጥሩ ነው ሁልጊዜ እድል የለም" እያለች በዘወርዋራው እንዳገባው እንደፈለገች ስትነግረኝ
"ምነው እድሌን ባልዘጋ ምናልባት በጊዜ ሂደት እወደው ይሆናል" ብዬ ከጓደኝነት የዘለለ ምንም ሳይሰማኝ አገባሁት።
ያጎደለው ነገር ቢኖር እኮ ለሁሉም መልካም ነበረ። ያልሞቀ ያልበረደ ማንነቱ ለፀብ እንኳን አልመች አለኝ። ሌላ ሰው ቢሆን አይናደድም ወይ ትግስቱ አያልቅም እላለሁ እንደሱ ልትወደው ሴት ይገባው አልነበር እላለሁ።
እንደዚህ እንቅልፍ አጥቼ እያየሁት ስፀፀት ወደራሱ ጎተት አድርጎ ያቅፈኝና "ብዙ አታስቢ በጊዜው ሁሉም ይሆናል አሁን ተኚ" ይለኛል
✍ናኒ
https://t.me/justhoughtsss