በወላይታ ሶዶ ነዳጅ ማደያዎች የማይገኘው ቤንዚን፤ በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ እንዴት እንደ ልብ ሊገኝ ቻለ?
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ እና የርዕሰ መስተዳድር መቀመጫ የሆነችው የወላይታ ሶዶ ከተማ፤ በሰባት በሮች እንግዶቿን ትቀበላለች። የህዝብ ትራንስፖርት እና የግል ተሽከርካሪዎችን የሚጠቀሙ ተጓዦች፤ በአረካ፣ ቦዲቲ፣ ኡምቦ እና ገሱባ ከተሞች አድርገው ወደ ወላይታ ሶዶ መግባት ይችላሉ። በጭዳ፣ ሆቢቻ፣ በዴሳ ከተሞች በኩል ያሉ መንገዶችን ለተጓዦች በአማራጭነት ያገለግላሉ።
ከአዲስ አበባ ከተማ 332 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው በወላይታ ሶዶ፤ ነዋሪዎች ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ በዋናነት የሚጠቀሙት በተለምዶ ባጃጅ ተብለው የሚጠሩትን ባለ ሶስት እግር ታክሲዎችን ሲሆን ሞተር ሳይክልም በነዋሪዎቹ ዘንድ ይዘወተራል። በከተማይቱ ከ12 ሺህ በላይ ባጃጆች እና ሞተር ብስክሌቶች እንደሚንቀሳቀሱ ከወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የወላይታ ሶዶ ከተማ ደም ስር የሆኑት እነዚህ መጓጓዣዎች በዋነኛነት የሚጠቀሙት ቤንዚን ቢሆንም፤ በአቅርቦት ረገድ ያለው ችግር የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችን ለከፍተኛ ምሬት ዳርጓል። ላለፈው አንድ ሳምንት በሶዶ ቆይታ ያደረገው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ፤ በከተማይቱ ውስጥ ባሉ የነዳጅ ማደያዎች ውስጥ ከፍተኛ የቤንዚን እጥረት መኖሩን አስተውሏል።
ካለፈው ረቡዕ ጥቅምት 20 ጀምሮ ደግሞ፤ የከተማይቱ ነዳጅ ማደያዎች “ቤንዚን የለም” የሚሉ ጉልህ ማስታወቂያዎችን መለጠፋቸውን ታዝቧል። የወላይታ ሶዶ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት፤ በከተማዋ የነዳጅ ማደያዎች ቤንዚን አለመኖሩን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጧል።
🔴 ለዝርዝሩ:- https://ethiopiainsider.com/2024/14522/
@EthiopiaInsiderNews