በአፋር ክልል ሳገንቶ ቀበሌ በመንቀጥቀጥ የፈለቀ እሳት ያዘለ ፈሳሽ “ብዙ ቤቶችን አቃጥሏል”- ነዋሪ
ቪዲዮ (2)፦ በአፋር ክልል፣ ዱለሳ ወረዳ፣ ሳገንቶ ቀበሌ ባለፉት ቀናት በተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦች ሳቢያ የፈለቀ እሳት ያዘለ ፈሳሽ “ ብዙ ቤቶችን ማቃጠሉን” አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።
ባለፉት ሁለት ቀናት፤ ሶስት ሺህ ገደማ የአካባቢው ነዋሪዎች ስፍራውን ለቅቀው መውጣታቸውን እና እስካሁን ድረስ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ነዋሪው አስረድተዋል።
ካሉአለ ከተባለ ስፍራ የመጡት እኚሁ የአካባቢው ነዋሪ፤ ከሰሞኑ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለውን ርዕደ መሬት የሚገልጹት “አስፈሪ” በሚል ቃል ነው።
“መሬት መንቀጥቀጥ ነበር። እንደገና ደግሞ እሳት ወጣ። የአካባቢው የመሬት መንቀጥቀጥ ራሱ የተለየ ነው። የቆመ ሰው ይወድቃል፤ ግመልም ይወድቃል፤ ከብትም ይወድቃል” ይላሉ ነዋሪው የሰሞኑን ሁኔታ ሲገልጹ።
“ውሃ የወጣበት አካባቢ ከሶስት ኪሎ ሜትር [ዙሪያ] የሚሆንበት ቦታ ላይ መሬት ስለሚንቀጠቀጥ ሰው በጣም ይፈራል” ሲሉም ነዋሪው ያክላሉ።
የሳገንቶ ቀበሌ ነዋሪው በእርሳቸው የመኖሪያ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጡ ባስከተለው ፍንዳታ የፈለቀ፤ “ውሃ የመሰለ ፈሳሽ” ለቤቶች መቃጠል ምክንያት መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።
“ብዙ ቤቶች ተቃጥለዋል። ከግቢ ውስጥ በሚወጣ ውሃ፤ ቤት ይቃጠላል። ውሃ ይባላል እንጂ እሳት ነው” ሲሉ ነዋሪው የፈሳሹን ምንነት ያስረዳሉ።
🔴 ተጨማሪ ለማንበብ:- https://ethiopiainsider.com/2025/14786/
🔴 ቪድዮውን ለመመልከት:- https://youtu.be/l7MkqLwhWRI?feature=shared
@EthiopiaInsiderNews