‹‹በመገዳደል የምትገኙ ሰላምና ዳቦ አጥቶ ለተቸገረው ሕዝባችሁ ስትሉ ለሰላማዊ መፍትሔ ዕድል ስጡ››
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ የዘንድሮውን የትንሣኤ በዓል አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የተናገሩት። ቅዱስ ፓትርያርኩ በሚያዝያ 12 ቀን 2017 ዓ.ም. የፋሲካ መልዕክታቸው፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ በእምነትና ሥነ ምግባር እየተመራን፣ በደልን በይቅርታ እየዘጋን፣ እስከ ጋብቻ በሚዘልቅ ባህለ ዕርቅ ደምን እያደረቅን፣ በወንድማማችነት ፍቅር ተስማምተን በሺሕ ለሚቆጠሩ ዘመናት እንዳልኖርን፣ እነሆ ዛሬ ለታላቅነታችን በማይመጥን ሁናቴ መለያየትና መጣላት ብሎም እርስ በርስ መገዳደል ዕለታዊ ተግባራችን አድርገን እንገኛለን ብለዋል፡፡ ‹‹ይህ በጣም አሳዛኝ ክሥተት ነው፤ ይህንን ሳናስተካክል የምናከብረው በዓለ ትንሣኤም እዚህ ግባ የሚባል ደስታ ሊያስገኝልን እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ እየሆነ ያለው ሁሉ ማንንም አይጠቅምም፤ በዕርቅ፣ በይቅርታና በውይይት የማይፈታ ችግር ያለ ይመስል ይህን ያህል መጨካከን እንዴት እንደ መፍትሔ ተደርጎ ይወሰ...
ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140544/