አርሴማን ጥሩልኝ🥺
ክፍል ፲
በድንጋጤ ራሴን ስቼ ወደኩኝ ከደቂቃዎች በኋላ ስነቃ ራሴን አልጋ ላይ ተኝቼ ነበር ያገኘሁት ወይኔ እግዚአብሔር በልጅ ባረከኝ ባለቤቴን መርሻ መፅናኛ ሰጠኸኝ ብዬ ሳመሰግን ቤቴን ባዶ ልታደርገው ነው ምናለ ሁለታችንንም ብትወስደን ያለሷ ዘመድ እንደሌለኝ እያወክ ምነው አንቺስ ብትሆኚ ቅድስት አርሴማ ላንቺ የደገስኩት ፀበል ፃዲቅ ለለቀስተኛ ልታደርጊው ፈልገሽ ነው ምነው እናቴ አንድ ልጄን እሷ ብቻ እንዳለችኝ እያወቅሽ ብዬ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩኝ የእማማ አነጋገር በጣም ይመስጣል እዛው የነበርኩ ያህል ነበር የተሰማኝ እማሆይ ሲያወሩ በደስታ ያለቅሳሉ እሺ ከዛስ አልኩኝ በጉጉት ከአልጋ ወርጄ ወደ ልጄ ሄድኩና ያሉኝን ሁሉ አንድም ሳላስቀር ነገርኳት ልጄ በጣም አለቀሰች እማዬ አለች አቤት ልጄ አልኳት አሁኑኑ ወደ ለቡ አርሴማ ውሰጂ ወደ ለቡ አርሴማ ውሰጂኝ አለችኝ አይ የኔ ልጅ ይሄ ግልኮስ ከተነቀለ እኮ አሁን ትሞችብኛለሽ ቢያንስ ትንሽ ጊዜ እናውራ ልጄ አልኳት አይ አሁኑኑ ውሰጂኝ ከሞትኩም እዛው ለቡ አርሴማ ልቀበር አለች እሺ ግን ነገ ልውሰድሽ ልጄ አልኳት እውነት ለመናገር ቢያንስ ዛሬ አይን አይንዋን እያየሁ ልደር ብዬ ነው ለሊቱን ሙሉ ቁጭ ብዬ ሳያት አደርኩ ጠዋት 3 ሰአት አካባቢ እያለቀስኩ ከጎረቤቶቼ ጋር አብረን ይዘናት ወጣን ካሁን ካሁን ትንፋሽ አጥሯት ሞተች እያልኩኝ እያለቀስን በሆስፒታል አልጋ ይዘናት ለቡ አርሴማ ገባን እያለቀሰች ልጄ ለቅድስት አርሴማ ተሳለች ልጄ ቅድስት አርሴማ ሆይ እኔ ልጅሽን ከዚህ ካንሰር የተባለ በሽታ ከገላገልሽን ህይወቴን ካስተካከልሽው እድሜ ልኬን ያንቺ አገልጋይ ሆኜ መንኩሼ እኖራለሁ አለች ስቅስቅ ብዬ ነበር ያለቀስኩት እኔም ለቅድስት አርሴማ ስለት ልሳልላት በርከክ አልኩኝና ጀመርኩኝ ሰማዕቷ ሆይ ……
ይቀጥላል
✍ብርሃኑ ባውቄ