ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


🥰 እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሄርን ያመስግነው።
መዝ. ፻፶ ፡ ፮
❝በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማነው?
1.ጴጥ 3፡13

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
መንፈሳዊ ፊልም ንጉስ ሰለሞን ክፍል 1

ታች ያለውን Link በመንካት Join ብለው ይቀላቀሉ እንዲሁም ለሌሎች ያጋሩ👇👇👇👇
https://t.me/Ethiopian_Ortodoks


ንጉስ ሰለሞን የተሰኘ መንፈሳዊ ፊልም ይጀመር እንዴ ቤተሰቦች 😊

Like ❤️👍🥰ተጫኗት እንኪ 😂


ሃይማኖት ተስፋ የምናደርገውን የሚያስረግጥ ነው

> /ዕብ ፲፩÷፩/

ሰው ረቂቅነቱ በምክንያት በዓይነ ሥጋ የማያየውን የእግዚአብሔር ህልውና የሚረዳው በእምነት ነው ። እንደዚሁም ከእርሱ በመራቋ ምክንያት የማያያትን ነገር ግን ተስፋ የሚያደርጋትን መንግስት ሰማያት በእውነት ለባልዋ እንደ አጌጠች ሙሽራ ተዘጋጅታ እንዳለች የሚያረጋግጠው በእምነት ነው ። / ራዕ . ፳፩÷፪ \ ። ስለዚህ እምነት የማናየውን የምታስረዳ ተስፋ የምናደርገውን የምታስረግጥ ናት ።

ቻናሉን_ለወዳጆቻችሁ_ሼር_በማድረግ_እንዲቀላቀሉ ጋብዙ❤️
@Ethiopian_Ortodoks


❤ ኪዳነ ምህረት እናቴ ❤


ስምሽ ይጣፍጣል ማር ነው ለአንደበቴ፣
ትውልድ የሚወድሽ ብፅዕት እመቤቴ።
በእጆችሽ የታቀፍሽ የዓለምን ዳኛ፣
ኪዳነ ምህረት የልቤ መፅናኛ❤



🥀 አለው ትበለን 🤲

2.5k 0 20 12 133

ዘወትር በጾም ሰዓት፦

➻ ዐይናችን ይጹም

➻ ልሳናችን ይጹም

➻ ጆሯችን ይጹም

ቸሩ መድኃኔዓለም አእምሮአችንን ይቆጣጠርልን መልካም ቀን ይኹንልን🙏❤⛪


ዕለተ ምጽአት በቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ

አቤቱ የሚያረጅ የሚጠፋ ይህ የተስፋ ዓለም ለእኛ ለክርስቲያን ወገኖችህ አይደለም የሚመጣውን ተስፋ እናደርጋለን ደጅም እንጸናለን እንጂ። አንተ ሰማይና ምድር ያልፋል ቃሌ ግን አያልፍም ብለሃልና።

በእለተ ምጽአት አምላክ ሲመጣ ሦስት ጊዜ ታላቅ የሆነ የመለከት መነፋት ይሆናል። ይህ የመለከት ድምጽም ሙታንን ሁሉ የሚያነቃ ነው።

በመጀመሪያው አዋጅ መለከት ሲነፋ በዓለም ዳርቻ ሁሉ የተበተነ የሥጋ ትቢያ ይሰበሰባል። በላይ ያለውና በታች ያለው በባሕር ያለውና በየብስ ያለው በአራዊትም ሆድ ያለው በልዩ ልዩ ሞት ፈጽሞ ያረጀና የጠፋ በምድር ላይ የወደቀ የሥጋ ቅርፍትም ሁሉ ወደ ቀደመ መገናኛው ይሰበሰባል።

በሁለተኛው አዋጅ መለከት ሲነፋ አጥንቶች ከሥጋና ከደም ጋር ይያያዛሉ ያለመንቀሳቀስ ያለመናወጥም እስከ ጊዜው ድረስ ፍጹም በድን ይሆናል።

በሦስተኛው አዋጅ መለከት ሲነፋ ሙታን እንደ ዓይን ጥቅሻ ፈጥነው ይነሳሉ ጻጽቃንና ኃጥአን ክፉም ቢሆን በጎም ቢሆን በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ የሠሩትን ከምድር የተከተላቸውን ሥራቸውን ተሸክመው ይነሣሉ ጻድቃንን በቀኝ ኃጥአንንም በግራህ ታቆማለህ። ለመረጥካቸውም በምሥጋና ቃል ትናገራቸዋለህ እንዲህ ብለህ፥-

እናንተ የአባቴ ቡሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን መንግሥተ ሰማያት ትወርሱ ዘንድ ወደ እኔ ኑ ብራብ አብልታችሁኛልና፣ ብጠማ አጠጥታችሁኛልና፣ እንግዳ ብሆን አሳድራችሁኛልና፣ ብታረዝ አልብሳችሁኛልና፣ ብታመም ጎብኝታችሁኛልና፣ ብታሠር መጥታችሁ ጠይቃችሁኛልና በማለት (ማቴ. 25፥34-36) እንደተነገር ሁሉ ዳግመኛም ወደ ግራው ተመልሰህ በወቀሳ ቃል እንዲህ ትላቸዋለህ ብራብ አላበላችሁኝምና፣ ብጠማ አላጠጣችሁኝምና፣ እንግዳ ብሆን አላሳደራችሁኝምና፣ ብራቆት አላለበሳችሁኝምና፣ ብታመም አልጎበኛችሁኝምና፣ ብታሠር አልጠየቃችሁኝምና በማለት (ማቴ 25፥ 42-23) ያን ጊዜ ዓመጽና ሽንገላን ይናገር የነበረ አፍና አንደበት ሁሉ ይዘጋል። ያንጊዜ ኃዘን ይደረጋል፡ የማይጠቅም ኃዘን ነው።  ያንጊዜ ጩኸት ይደረጋል የማይጠቅም ጩኸት ነው። ያንጊዜ ፍጅት ይሆናል የማይጠቅም ፍጅት ነው። ያንጊዜ ለቅሶ ይሆናል የማይጠቅም ለቅሶ ነው። የሚያስደነግጥ የነጐድጓድ ቃል የሚቆርጥና የሚከፍል የሚለይ ብርቱ ብልጭልጭታም ወደእነርሱ ይላካል ይኸውም የኃጥአን ዕድላቸው ነው።

ያን ጊዜም ምድር አደራዋን ትመልሳለች እናትም የሴት ልጅዋን ጩኸት አትሰማም። ያን ጊዜ በሕይወትዋ ዘመን የሰራችው የነፍስ ሥራዋ ይገለጻል።

ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ያን ጊዜ ትምረን ዘንድ ይቅርም ትለን ዘንድ በበላነው በቅዱስ ሥጋ በጠጣነው በክቡር ደምህ እንማጸንሃለን። ስለ እናትህ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ብለህ ስለ ሁሉ ቅዱሳን መላእክት ጻድቃን ሰማዕታት ነቢያት ሐዋርያት እንዲሁም ደናግላን መነኮሳት እንማጸንሃለን። አምላክ ሆይ ያን ጊዜ ማረን ራራልንም ይቅርም በለን።
    
(ቅዳሴ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ)

የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ሼር በማድረግ አዳርሱ🙏❤️

@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks


አምላክ ሆይ ወደኛ ባትመጣ ለብሰህ የማርያምን ሥጋ/፪/
ባክኖ የነበረው የአዳም ልጅ ወጤቱ ነበር የሚያሰጋ/፪/

🌷አቤቱ በመንግስትህ አስበን🤲


​​እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። 🙏✝

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ †††


ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል::

ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም (አልቦ ትንሳኤ) የሚሉ ናቸው:: መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ "ዲዲሞስ" ሲሆን ጌታችን "ቶማስ" ብሎታል::

ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: (ዮሐ. 11:16)

ጌታችን ትንሳኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም:-
1.ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው::
2.አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት "ትንሳኤውን አየን" እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን "ሰማሁ" ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር::

ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ (ጌታየና አምላኬ)" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን (መለኮትን) ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች::

ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት:: ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ (ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት)" ሲሉ ያከብሩታል::

ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል:: በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት:-
"ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ::
አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ::" ብለዋል ሊቃውንቱ::

በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል::

ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ38 ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል::

በመጨረሻም በ72 ዓ/ም በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል::

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን::

💚 @Ethiopian_Ortodoks 💚
💛 @Ethiopian_Ortodoks 💛
❤️ @Ethiopian_Ortodoks ❤️


እንኳን ለበዓለ ደብረ ዘይት በሰላም አደረሳችሁ።


ሰላም ተወዳጆች ከላይ ያለውን ቪዲዮ ሁላችሁም ፖስት አድርጉ
ይሄን ሎጎ ደግሞ የቲክቶክ ,ፌስቡክ, ኢንስታግራም እና ሌሎች ሶሻል ሚዲያዎቻችን ፕሮፍይል ፒክቸር በማድረግ አንድነታችንን እንግለፅ 🥰


ከእርሱ ጋር ኀብረት ፍጠሩ!

"እግዚአብሔርን ለማወቅ ለመውደድ ከእርሱ ጋር መተባበር አለባችሁ። ንባብ ብቻውን በቂ አይደለም። ንባብ የሚከፍትላችሁ መዝጊያውን ብቻ ነው። ከዚህ በኋላ እናንተ ትገቡና ከእግዚአብሔር ጋር ትኖራላችሁ ከዚያም ከእርሱ ጋር መኖር ጣፋጭ መሆኑን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።

ስለሆነም ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትን ትሞክሩታላችሁ እርሱ በሁሉም ነገር ውስጥ ተካፋይ እንዲሆንም ትፈቅዳላችሁ።

እንደ ባልጀራችሁ አድርጋችሁ ልትወዱት ሞክሩ አሳቦቻችሁንና ሚስጥሮቻችሁን ለእርሱ ንገሩት። ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ጠብቁና እርሱ ምን ያህል ከእናንተና ለእናንተ እንደሚሰራ ታያላችሁ። ከዚህ በተጨማሪ በአሳቦቻችሁና በተሰጥኦዎቻችሁ ከመተማመን የበለጠ በእርሱ ላይ መተማመንን ታውቃላችሁ።"

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ


+ ያልተናገረችው አህያ + 

ነቢዩ በለዓም በአህያ ላይ ተጭኖ ሲሔድ አህያው የእግዚአብሔርን መልአክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠጋች፡፡ በለዓም ተናድዶ መታት፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ አህያይቱ ድጋሚ መልአኩን አየች፡፡ ከበለዓም በታችም ተኛች፡፡ በለዓም ተበሳጭቶ አህያይቱን በበትሩ ደበደባት፡፡

እግዚአብሔርም የአህያይቱን አፍ ከፈተ ፦ ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌብህ ነው? አለችው፡፡ በለዓምም አህያይቱን ፦ ስላላገጥሽብኝ ነው ሰይፍ በእጄ ቢኖር ኖሮ እገድልሽ ነበር አላት፡፡ አህያይቱም በለዓምን ፦ ብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን? አለችው። እርሱም፦ እንዲህ አላደረግሽብኝም አላት’’ /ዘኁ 22፡27-30/

  ይህንን ታሪክ ባነበብሁ ቁጥር ሁልጊዜም የሚያስደንቀኝ የአህያይቱ መናገር ሳይሆን የበለዓም መልስ መሥጠት ነው፡፡

እግዚአብሔር ያሳያችሁ፡፡ በለዓም መልስ የሠጠው ከሎሌዎቹ ለአንዱ አይደለም፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‘ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩን ዕብደት አገደ’ /2ጴጥ 2፡16/ እንዳለው አህያ ስትናገር ታይቶ ተሰምቶ አያውቅም፡፡

መንገድ ላይ እየሔድህ ከሰፈርህ ውሾች አንዱ ‘እንዴት አደርህ?’ ቢልህ እግዚአብሔር ይመስገን ትላለህ? እርግጠኛ ነኝ ራስህን ስተህ ልትወድቅ ትችላለህ፡፡ ከተረጋጋህ በኋላም አእምሮህ ተነክቶ ‘ውሻው ተናገረ እኮ’ እያልክ ትኖራለህ፡፡

በለዓም ግን ተናግራ የማታውቀው አህያ አፍ አውጥታ ስትናገር ሲያይ ትንሽ ደንገጥ እንኳን አላለም፡፡ ሌላ ቀን ሲያናግራት እንደኖረ ሰው ኮስተር ብሎ መመላለስ ጀመረ፡፡ አህያዋ አብረው ስለኖሩበት ዘመን የሥራ ልምድዋና የሥራ አፈጻጸምዋ ‘ብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን?’ ብላ ስትነግረው በለዓም ሠራተኛውን እንደሚያናግር አለቃ ተረጋግቶ ያለ ምንም መደንገጥ ራሱን እየነቀነቀ ከሰማ በኋላ ፦ እንዲህ አላደረግሽብኝም ብሎ ግምገማዋን ተቀብሎ ኂሱን ዋጠ፡፡

የበለዓምን ነገር እንተወውና የተናጋሪዋ አህያውንም ነገር እንርሳውና አንዲት መናገር ሲኖርባት ያልተናገረች አህያ ነገር ግን የበለጠ ይቆጫል፡፡

ይህች አህያ በሆሳዕና ዕለት ጌታችን የተጫነባት አህያ ናት፡፡ ይህች አህያ እንደ በለዓም አህያ ጌታዋ በበትሩ የሚደበድባት ሳይሆን ‘ለጌታ ያስፈልጉታል’ ብሎ ከነ ልጅዋ ያስፈታት አህያ ናት፡፡ የእርስዋ ጌታ በተኛችበት በበትር የሚቀጠቅጣት ሳትሆን እግርዋ መሬት እንዳይረግጥ ጌታዋ ያስነጠፈላት አህያ ናት፡፡

የእርስዋ ጌታ እንደ በለዓም መልአክ መንገድ የሚዘጋበት ሳይሆን መላእክት በፊቱ እየሰገዱ እንደ ሻሽ የሚነጠፉለት ነው፡፡ የበለዓምን አህያ አንደበት የከፈተ ጌታ ምነው የዚህችን አህያ አንደበት በከፈተው ኖሮ! ስንት ነገር በተናገረች ነበር?

  የሆሳዕናዋ አህያ አንደበትዋ ቢከፈት እንደ በለዓም አህያ ጌታዋን ከማማረር ይልቅ ከሕዝቡ ጋር አብራ ትዘምር ነበር፡፡ እንደ በለዓም አህያ  ‘ብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን?’ በማለት ፋንታ ‘ከብዙ ዘመን ጀምሮ ሰው ሲቀመጥብኝ የኖርሁ አህያ ነበርሁ፡፡ በውኑ ንጉሥን እሸከም ዘንድ ልማዴ ነበርን?’ ብላ ታመሰግን ነበር፡፡

ጌታ ሆይ እኛስ ስንት በለዓሞችን ተሸክመን ኖርን? ስንት በለዓሞች በተሸከምናቸው በታግስናቸው ልክ በማመስገን ፈንታ በበትር ደበደቡን? በብሶት በምሬት አፍ አውጥተን ስንናገር እንኳን ትንሽ አይደንቃቸውም፡፡

አንተው መጥተህ ገላግለን፡፡ ለምስጋና ቢስ በለዓሞች ‘ለጌታ ያስፈልጉታል’ ብለህ እንዲፈቱን ንገራቸው፡፡ አንተው ዙፋንህ አድርገን፡፡ አንተን መሸከም አይከብደንም፡፡ አንተን የያዝን እንደሆን መንገዳችን በዝማሬ የተሞላ ይሆናል፡፡ የሚንቁን ሁሉ አንተን ብለው ያከብሩናል፡፡ ምንም እንኳን አንተን ሊይዝህ የሚችል ባይኖርም በደስታ እንሸከምሃለን፡፡

ራስህ እንዲህ ብለሃልና ፦

‘እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ
እኔም አሳርፋችኋለሁ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ
ከእኔም ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና
ለነፍሳችሁም ዕረፍትን ታገኛላችሁ
ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና’ /ማቴ 11፡28/

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 17 2013 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

(መጋቢት 12 ቅዱስ ሚካኤል በለዓምን የተቋቋመበት መታሰቢያ ነው)
https://t.me/Ethiopian_Ortodoks
https://t.me/Ethiopian_Ortodoks

4k 0 40 1 41

ብዙ ጊዜ ውድቀት ከስኬት ቀድሞ ይመጣል። ነገር ግን በእያንዳንዱ ውድቀትህ ውስጥ ለስኬትህ የሚያበቃህን ልዩ ትምህርት ትማራለህ። በአዕምሮህ ውስጥ ትልቅ ነገር አስብ ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ እኛ የምንሆነው በአዕምሯችን ውስጥ በምስጢር የምናስበውን ነው። ለዚህም ነው ሰዎች የሚታዩበት ቦታ ሳይሆን የማይታሰቡበት ቦታ የሚደርሱት።
ደስታ ማጣት በህይወት ግልጽ የሆነ ትርጉምና ዓላማ ከማጣት ይመጣል።


እያንዳንዱ የሚገጥሙን ፈተናዎች ህይወትን ተወዳጅ የሚያደርጓት ማጣፈጫ ቅመሞች ናቸው። ህይወትን ትርጉም ያላትየምናደርጋት ደግሞ የሚሰነዘሩብንን ፈተናዎች በብቃትና በስሌት መቋቋም ስንችል ነው።

በዘላቂነት ለመለወጥ ካሰብክ
ግልፅ የሆነ ግብ እና በራስ የመተማመን መንፈስም ሊኖርህ ይገባል። የስኬታማነት አንዱ አስፈላጊ ምስጢር በራስ መተማመን ነው። በራስ ለመተማመን አስፈላጊ መሳሪያው ደግሞ የማያቋርጥ ዝግጁነት ነው። በራስ ላይ እምነት ማጣት ከሌሎች ውጫዊ እንቅፋቶች ይልቅ የአንድን ሰው አቅምና ችሎታ ሽባ ያደርጋል።=

መልካም ቀን ቤተሰብ🤗🙏


ለማንም እንዳትናገር!

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የአንድን ዲዳና ደንቆሮ አንደበት ‘ተከፈት’ ብሎ በአምላካዊ ኃይሉ ከፈተ፡፡ ይህንን ካደረገ በኋላ ግን ‘ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው እነርሱ ግን ባዘዛቸውም መጠን ይልቅ እጅግ አወሩት’’ (ማር 7:36)
‘አትንገር ብዬ ብነግረው አትንገር ብሎ ነገረው’ ይሏል እንግዲህ ይኼንን ነው፡፡

የመልካም ሰውነት አንዱ መለኪያ ምሥጢር ጠባቂነት ነው፡፡ እውነተኛ ባልንጀርነትም ምሥጢርን መስማት ሳይሆን የሰሙትን ጠብቆ መያዝ ነው፡፡ ይህ የሚሆንላቸው ሰዎች በማኅበረሰቡ ዘንድ ይከበራሉ በፈጣሪም ዘንድ ዋጋቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ በምድርም ቢሆን ለከፍተኛ ሓላፊነት የሚታጩትና ከፍ ያለ ክብር የሚሰጣቸው ሰዎች በማሰቃያ ሥፍራ ሳይቀር እየተንገላቱ ምሥጢር የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው፡፡

አንዳንድ ሰው ግን የሰማውን ምሥጢር ለሌላ ሰው ለማዝረክረክ ማሰቃያ አያስፈልገውም፡፡ አትንገር የተባለውን እስኪናገር ድረስ ሆዱን ይቆርጠዋል፡፡ እግሩን እሾህ የወጋው ሰው እስኪነቀልለት ድረስ እንደሚንገበገብ ይህ ዓይነት ዓመል የተጠናወተውም ሰው ምሥጢሩን ለሌላ ሰው እስኪያሰማ ድረስ ይንቆራጠጣል፡፡ ‘ቀሊል ሰው’ ይለዋል ጠቢቡ ሲራክ

ምሥጢር ጠባቂነት ለወታደር የሞት ሽረት ጉዳይ ነው፡፡ በኮድ ማውራት ግድ የሆነውም ለዚህ ነው፡፡  ለሐኪም የሙያ ቃል ኪዳን ነው፡፡ ለጠበቃ የጥብቅና ፈቃድን ላለማጣት የሚጠበቅ ሕግ ነው፡፡ ለካህናት የንስሓ ልጆችን የመጠበቅ ሰማያዊ ቃልኪዳን ነው፡፡ ዓለም የምትናወጸው በዚህ መርሕ ኖረው ምሥጢር በማይጠብቁ ሰዎች ነው ማለት ይቀልላል፡፡ 

ጌታችን ያደረገው ፈውስ ቢሆንም ማስታወቂያ ሥሩልኝ ግን አላለም:: እንዳይናገሩ አዝዛቸው:: ከዚህም የምንማረው ብዙ ነው:: የሰውን መልካም ነገርም ቢሆን ምሥጢር መጠበቅ የግድ ነው፡፡ ለዚያ ሰው ሥራ እንቅፋት ላለመሆን ሲባል ዝም ማለት እርዳታ ነው:: የሰውን ኃጢአትና ነውር መደበቅ ደግሞ "ከባቴ አበሳ" (በደልን ሸፋኝ) አስብሎ በፈጣሪ ክብር ያስገኛል::

ሙሴን ወደ ስደት የዳረገው ምሥጢር መቋጠር የማይችል እስራኤላዊ ነበር፡፡ ሙሴ ለእርሱ አግዞ ግብጻዊውን ገድሎ ቢቀብርና ነጻ ቢያወጣው ‘አመስጋኝ አማሳኝ’ /አመስጋኝ አጥፊ/ እንዲሉ ሔዶ ወሬውን ነዛው፡፡ ወሬው በአጭር ጊዜ ተዳርሶ እስከ ፈር ኦን እልፍኝ ደረሰ፡፡ በአንድ መቋጠር በማይችል ወንፊት ሰው ምክንያት ሙሴ ከቤተ መንግሥት ወጥቶ የዱር ስደተኛ ሆነ፡፡

ጌታችን በዚህች ምድር ሲመላለስ ተአምራቱን እንዳይናገሩ ያደርግ የነበረው ተአምራቱ ቢነገሩ የሚጎዱ ሆነው አልነበረም፡፡ በአንድ ወገን መከራ ከፊቱ አስቀምጦ ክብርን መፈላለግ እንደማይገባ ሲያስተምረን ሲሆን በሌላ በኩል ግን ከጊዜው በፊት መከራን ሊያደርሱበት እንዳይነሳሱና የመጣበትን ዓላማ ቅድሚያ መፈጸም እንደሚገባው ሲያስረዳ ነበር፡፡

  ምሥጢር መጠበቅ በጎ ዕቅድንም ይጨምራል፡፡ ያለ ጊዜው የወጣ በጎ ዜናም ሆነ ዕቅድ በአፍ ይቀራል፡፡ ሳይሠራ ፈተና ይበዛበታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሳይሠሩ ቀድሞ ‘እሠራለሁ’’ ብሎ ነጋሪት መጎሰም ለጠላት ማንቂያ ደወል ነው፡፡ አበው ‘የሰይጣን ጆሮ አይስማ’ የሚሉት ለሰይጣን ብቻ አይደለም፡፡ አንዳንድ ነገር ሳይሠራ ተወርቶ ይዳረሳል፡፡ ክፋቱ በጣም ያወራከው ነገር የሰራኸው የሚመስልህ ነገር ነው፡፡ ብዙ ካወራህ በኋላ ያወራኸውን ከሰራኸው ለመለየት መቸገርህ አይቀርም፡፡ ዝም ብሎ መሥራትን የመሰለ ደግሞ ምንም ነገር የለም፡፡ ችግሩ ‘አሣ ሳትይዝ አሣ እጠብሳለሁ አትበል’  እንደሚባለው ከሥራ ማኒፌስቶው መቅደም የለበትም::

አንዳንዴ ደግሞ "በምሥጢር እየሥራ" መሆኑን የሚያወራም ሰው አለ:: ጳውሎስ ኞኞ በጻፈው አሁን የማላስታውሰው ጽሑፍ ላይ በድሮ ዘመን ደረታቸው ላይ "የምሥጢር ፖሊስ" የሚል ጽሑፍ የተለጠፈባቸው ሰላዮች ነበሩ ይባላል:: ምሥጢሩም እንዳይቀር ጉራውም እንዳይቀር ነው ነገሩ:: እንዲህ ያለ ነገር ስንት ሥራ አበላሽቶአል መሰላችሁ?!

ዝም ማለት የቻለ ተቋም ወይም ግለሰብ ባይሠራ እንኳን ዝምታው ግርማ ይሆነዋል፡፡ ‘ሬሳ የሚፈራው ለምንድር ነው? ቢሉ ዝም ስለሚል’’ ይባላል፡፡ ዝም የሚል ወገን ባይሠራ እንኳን ‘ዝም ያለው ምን እየሠራ ነው?’’ ያሰኛል፡፡ መረዳት ከቻልን ውስጥ ውስጡን የልባቸውን እየሠሩ ፣ በፈለጉት ቦታ የፈለጉትን እያስቀመጡ ፣ ንብረት እያፈሩ ፣ እየተደራጁ ጸጥ የሚሉ እንዳሉ ሁሉ ላይ ላዩን ደግሞ እያወሩ ምንም የማይሠሩ ዓለምን ሞልተዋታል፡፡

ሥጋትንህንም ሁሉ መደበቅ አንድ ብልህነት ነው፡፡ አንዱን ሰውዬ ዘራፊዎች አግኝተው ቅጥቅጥ አደረጉት ይባላል፡፡ ኪሱን ሲፈትሹ ግን  ያገኙት አምስት ብር ብቻ ነው፡፡ ብስጭት ብለው ‘’አንተ ለ አምስት ብር ብለህ ልትሞት ነበር እንዴ?’’ ሲሉት ‘አይ እኔማ ካልሲዬ ውስጥ የደበቅኩትን አምስት መቶ ብር ትወስዱብኛላችሁ ብዬ ፈርቼ ነው’ ብሎ አረፈው፡፡

በዚህ ዘመን አንደበትን ያለመሰብሰብ ችግር እንደዚህ ሰውዬ እየጎዳንም ነው፡፡ እንዲህ ሊያደርጉ ነው ፣ እንዲህ ሊሠሩ ነው ወዘተ በሚል ጥቆማ ተበረታትተው ብዙ ክፉ የሠሩና የሚሠሩ ዘራፊዎች አሉ፡፡ አንዳንዴም እንደ ባለ አምስት መቶ ብሩ ሰውዬ ያላሰቡትን ያሳሰብናቸው ቀማኞች አሉ፡፡ የማይተዋወቁትን ሰዎች ሳናውቅ አብረን ሰድበን አንድ ያደረግናቸው ፣ የማይታወቁትን ሰዎች በነቀፋ ጀግና ያደረግናቸው ብዙ ናቸው፡፡
የዚህ ዘመን መሻገሪያ ወርቃማ ሕግ አንደበትን መቆጠብ ፤ የቻለ ድምጽ አጥፍቶ በጎ መሥራት ፣ ያልቻለም የሚሠሩ ሥራዎችን በአንዳንድ ነጋሪቶች አለማደናቀፍ ነው፡፡

‘ኢየሱስም ያዩትን እንዳይናገሩ አዘዛቸው’’        

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
https://t.me/Ethiopian_Ortodoks


ጸሎት የነፍስ ምግብ ነው. ነፍስህን አታስርባት, ነፍስህን ከምታስርባት ስጋህ ቢራብ ይሻላል.

ሁሉንም ይቅር በል በማንም ላይ አትፍረድ

እራስህን በምድር ካለ ሰው ሁሉ የከፋ እንደሆንክ ቁጥር እናም ትድናለህ.በቻልከው አቅም ደግሞ ይበልጥ ዝምተኛ ሁን።

🌷መልካም ሌሊት🥰✝


እምነት፡ተስፋ፡ፍቅር፡እነዚህ፡ሦስቱ፡ጸንተው፡ይኖራሉ ከነዚህም፡የሚበልጠው፡
ፍቅር ነው።

💒 መልካም ምሽት😍🙏🙏

4.3k 0 18 7 135

ምርኩዜ🥺
ክፍል ፫
ምንድን ነው ነገሩ እናንተ እነማን ናችሁ አለ ምንም መልስ ሳይሰጧቸው አስረው ወሰዷቸው ያላቸውን ሃብት ሁሉንም በስማቸው ካስዞሯቸው በኋላ አባቱን እና እናቱን ከፊቱ ገድለዋቸው ተሰወሩ ቅዱሴ እናትና አባቱን ብቻውን ገንዞ አፈር አልብሶ ወደዚህ መጣ ከዚያች ቀን ጀምሮ እንደምታዩት ሆኖ ቀረ አሁን ነው እንደውም ሰው መቅረብ የጀመረው በቃ ሁልጊዜ ምርኩዜ ለምን ተውከኝ እያለ ወደ ሚካኤል ስዕለ አድህኖ ይጮሃል አሁን ላይ የኔ ልጅ ለቅዱሴ ሰው ብር ቢሰጠው እንዳይገርምሽ እሱ በፊት በጣም ለጋስ ስለነበረ ነው በአንድ ጊዜ የሁሉም ፊት ተቀየረ ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ነው አባባ ተዉ ልጆቼ አታልቅሱ እንባ የሚመልስ ቢሆን የቤቱ አሽከሮች ያለቀሱለት ይፈውሰው ነበር ተዉ የባሰ አታምጣ ነው የሚባለው ታዲያ አባባ ጋሽ ግርማ እንደዚህ የሚሆኑት በቅዱስ ቤተሰብ ብር ነው አለችው በትክክል የኔ ልጅ ቆይ በሀገራችን ህግ የለም እንዴ መከሰስ አለበት አለች አዎ በትክክል እያሉ ሁሉም አዳመቁት አይ ልጆቼ ይህንን ሳናስብ ቀርተን ነው የሚመስላችሁ ግርማ እንደምታስቡት ቀላል ሰው አይደለም በየቦታው ሰው አለው በየቢሮው አቃጣሪ አለው ብንከሰው እኛ ስም በማጥፋት እንታሰራለን እንጂ እሱ ጭራሽ አይነካም ግን መፍትሄው ቀላል ነው ያው ሁላችሁም ቅዱስ እንዲድን ከፈለጋችሁ አለ ምንድን ነው አባባ እኔ ተስማምቻለሁ እኔም እኔም እንደዛው ጎሽ ልጆቼ እግዚአብሔር ይስጣችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ አሁን ወደ መፍትሄው ስንገባ በመጀመሪያ ሁለታችሁ ቅዱሴን በሰንሰለት ታስሩና ታመጡታላችሁ………



ይቀጥላል
✍ብርሃኑ ባውቄ

5.3k 0 46 17 91

ከሻሸመኔ ተነስተው ከንግስ ሲመለሱ ህይወታቸውን በመኪና አደጋ በአሰቃቂ ሁኔታ ላጡ  ወንድም እህቶች ነብስ ይማር ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይላክልን ።

😭

#ኦርቶዶክሳዊ_አስተምህሮ

5.3k 0 8 34 271

Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በፆም አሳ ይበላል ወይስ አይበላም ?
መምህራችን በደንብ አብራርተውታል 😊

#Share

💚 @Ethiopian_Ortodoks 💚
💛 @Ethiopian_Ortodoks 💛
❤️ @Ethiopian_Ortodoks ❤️


ኦርቶዶክስ ማለት ምን ማለት ነው ለናንተ ?

4.8k 0 17 23 136
20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.