ከ1.1 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሴቶችን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።
በኢትዮጵያ ለ25 ዓመታት ሲሰራ የቆየው አይፓስ የተሰኘ መንግስታዊ ያለሆነ ድርጅት ለ6 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሻለ የስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ለመስጠት ያስችለኛል ያለውን ፕሮጀክት በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል።
ፕሮጀክቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት በኢትዮጵያ ከሚፈጠሩ እርግዝናዎች 42 በመቶው ያልተፈለገ እንደሆነ እና ከዚህ ውስጥም አብዛኛው እርግዝና የሚፈጠረው በአስገድዶ መድፈር መሆኑን ጥናቶች እንደሚጠቁሙ ተጠቅሷል።
ፕሮጀክቱ ከፍተኛ ችግሮች አለባቸው ብሎ የለያቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማዳረስ አቅዶ ይሰራል የተባለ ሲሆን በአምስት ክልሎች ማለትም በመካከለኛ ኢትዮጵያ ፣ በአማራ ፣ በኦሮሚያ ፣ በትግራይና በቤኒሻንጉል ጉምዝ የሚተገበር መሆኑን ነው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጸው።
በአስገድዶ መድፈር እና ከዛም ጋር በተያያዘ ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ወጣት ሴቶችና ልጃገረዶች ፣ የአካል ጉዳት የገጠማቸው ወጣቶች እንደዚሁም ደግሞ ከየገጠሩ ተሰደው መጥተው የተለያዩ ፋብሪካዎች (ኢንዱስትሪያል ፓርክ) ውስጥ የሚሰሩ ወጣት ሴቶችን ተደራሽ የሚያደርግም ጭምር ነው ተብሎለታል።
ለፕሮጀክቱ 2,450 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች ዝግጁ ሆነዋል የተባለ ሲሆን ከ1.1 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሴቶችና ልጃገረዶችን በቀጥታ እንዲሁም ከ5.5 ሚሊዮን የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተዘዋዋሪ ተደራሽ ያደርጋል ተብሏል።
Source: tikvahethmagazine
@Ethiopianbusinessdaily