በኬንያ ከዛሬ ጀምሮ ለ1 ወር የሚቆይ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ ተደርጓልየኬንያ ኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ቁጥጥር ባለስልጣን (EPRA) ትናንት እንዳስታወቀው
የቤንዚን ዋጋ በሊትር የ1.95 የኬንያ ሽልንግ፣
የናፍጣ ዋጋ በሊትር የ2.20 የኬንያ ሽልንግ እና
የኬሮሲን ዋጋ በሊትር የ2.40 የኬንያ ሽልንግ የዋጋ ቅናሽ ተደርጎባቸዋል ብሏል።
ባለስልጣኑ ነዳጅ ከውጪ የሚገባበት ዋጋ በየካቲት እና መጋቢት ወር መቀነሱን የገለፀ ሲሆን:
ቤንዚን የ4.89%፣
ናፍጣ የ6.45% እና
ኬሮሲን የ6.53% የዋጋ ቅናሽ ማድረጋቸውን ገልጿል።
ቤንዚን በሊትር 174.63 ሽልንግ (178.97 ብር)፣
ናፍጣ በሊትር 164.86 ሽልንግ (168.96 ብር) እንደዚሁም
ኬሮሲን በሊትር 148.99 ሽልንግ (152.70 ብር) በሆነ ዋጋ በናይሮቢ እንደሚሸጡም ተገልጿል።
ኬንያ በነዳጅ ምርት ላይ የ16% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምትጥል ሲሆን ከላይ የተገለጸው ዋጋም ይህንን አካቶ እንደሆነ ተገልጿል።
Source: ethiomereja@Ethiopianbusinessdaily