እውን መረጃ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Musiqa


📌#ቀዳሚ_ምርጫዎ ➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ ➠ወቅታዊ መረጃዎች ➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች የምታገኙበት ቻናል
📌ጥቆማ ለመስጠት
👉 @ewun_mereja_bot
#እውነተኛ እና #ትኩስ #መረጃዎች
#እውንነት

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Musiqa
Statistika
Postlar filtri


#Update

ቻይና በአንዳንድ የአሜሪካ የግብርና ምርቶች ላይ ቀረጥ እንደምትጥል አሳወቀች፡፡

የቤጂንግ የፋይናንስ ሚኒስቴር በአንዳንድ የአሜሪካ የግብርና ምርቶች ላይ 15% ቀረጥ እንደሚጥል አስታውቋል፤ ከነዚህም መካከል ዶሮ፣ ስንዴ፣ በቆሎ እና ጥጥ ይገኙበታል።

እንደ አኩሪ አተር፣ አሳማ፣ የበሬ ሥጋ፣ ፍራፍሬ፣ አትክልት እና የወተት ተዋጽኦዎች ባሉ ሌሎች ምርቶች ላይ 10% ታሪፍ ጥሏል። ተግባራዊነቱም መጋቢት 10 ላይ ይጀምራል፡፡


ቻይና የአጸፋ እርምጃ መውሰድ የጀመረችው አሜሪካ በቻይና፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ላይ የታፍ ጭማሪ መጣሏን ተከትሉ ነው ።

አሜሪካ ከቻይና፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ በሚገቡ ምርቶች ላይ የጣለችው ታሪፍ ተግባራዊ ሆኗል።

ትራምፕ በካናዳ እና በሜክሲኮ ላይ 25% ታሪፍ እና በቻይና ላይ 20% ታሪፎችን ይፋ አድርገዋል፡፡

በመንግስት የሚተዳደረው ግሎባል ታይምስ ጋዜጣ ቤጂንግ የአሜሪካን የግብርና እና የምግብ ምርቶች ላይ ያነጣጠረ የመከላከያ እርምጃ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ተናግሯል።

ቻይና እ.ኤ.አ. በ2018 በአኩሪ አተር ፣በሬ ፣አሳማ ፣ስንዴ እና በቆሎ ላይ እስከ 25% የሚደርስ ታሪፍ ከጣለች በኋላ እንኳን ለአሜሪካ የግብርና ምርቶች ትልቋ ገበያ ሆና ቆይታለች፡፡

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ትራምፕ ረገብ ብሎ የነበረውን የንግድ ጦርነት አስጀመሩ

ሶስቱ የአሜሪካ ቀዳሚ የንግድ አጋሮች ለትራምፕ ታሪፍ አጻፋውን እንደሚመልሱ ዝተዋል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከካናዳ እና ሜክሲኮ በሚገቡ ምርቶች ላይ ከዛሬ ጀምሮ የ25 በመቶ ታሪፍ እንደሚጣል ገለጹ።
በየካቲት ወር መጀመሪያ የ10 በመቶ ታሪፍ ተጥሎባት የነበረው ቻይና ደግሞ የ10 በመቶ ጭማሪ ተደርጎባት ምርቶቿ ወደ አሜሪካ ሲገቡ የ20 በመቶ ቀረጥ ይጣልባታል ብለዋል።
ትራምፕ ሶስቱ የአሜሪካ ቀዳሚ የንግድ አጋሮች ፌንታኒል የተሰኘውን ገዳይ አደንዛዥ እጽ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ነው ታሪፉን የጣሉት።

ቻይና በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር ለተጣለባት ታሪፍ ፈጣን ምላሽ ሰጥታለች፤ ከመጋቢት 10 2025 ጀምሮ በተወሰኑ ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ከ10 እስከ 15 በመቶ ታሪፍ እንደምትጥል አስታውቃለች።
ለሶስት አስርት አመታት ከአሜሪካ ጋር ከታሪፍ ነጻ የንግድ ትስስር የነበራቸው ካናዳ እና ሜክሲኮም በቀዳሚ የንግድ አጋራቸው ላይ የአጻፋ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል።
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶው ኦታዋ 20.7 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ባላቸው የአሜሪካ ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ እንደምትጥል ገልጸዋል። 
በትራምፕ አስተዳደር ከዛሬ ጀምሮ ተፈጻሚ እንዲሆን የታዘዘው ታሪፍ በ21 ቀናት ውስጥ ካልቆመም 86.2 ቢሊየን ዶላር በሚያወጡ የአሜሪካ ምርቶች ላይ ታሪፍ እንደሚጣል ነው የተናገሩት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም የአሜሪካ ቢራ፣ ወይን፣ ውስኪ፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች እና የፍሎሪዳ የብርቱካን ጭማቂ የታሪፉ ኢላማ እንደሚሆኑ መናገራቸውን ሬውተርስ አስታውሷል።
የኦንታሪዮ አስተዳዳሪ ዱንግ ፎርድ ግዛቷ ወደ አሜሪካ ኤሌክትሪክ ማስተላለፍና ንኬል መላክ እንደምታቆም ለኤንቢሲ ተናግረዋል።
የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት ክላውዲያ ሼንባም በአሜሪካ ላይ ስለሚወሰደው የአጻፋ እርምጃ የሚሰጡት መግለጫ እየተጠበቀ ነው።
በቻይና ላይ የተደራረበው ታሪፍ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቤጂንግ ምርቶች ላይ የጣሉት የ20 በመቶ ታሪፍ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው 370 ቢሊየን ዶላር በሚያወጡ ወደ አሜሪካ በገቡ የቻይና ምርቶች ላይ ከጣሉት የ25 በመቶ ታሪፍ ላይ የሚደመር ነው።
በትራምፕ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመን ታሪፍ የተጣለባቸው ምርቶች በባይደን አስተዳደርም ኢላማ ነበሩ። ባይደን ባለፈው አመት በቻይና "ሰሚኮንዳክተሮች" ላይ የ50 በመቶ፤ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ደግሞ የ100 በመቶ ታሪፍ መጣላቸው ይታወሳል።
ትራምፕ ዳግም ወደ ስልጣን ከተመለሱ በኋላ የጣሉት ታሪፍ ከዚህ በፊት በነበሩት ውሳኔዎች ያልተካተቱን እንደ ስማርት ስልኮች፣ ላፕቶፖች፣ ስማርት ስአቶች እና ድምጽ ማጉያዎች ቀረጥ እንዲጣልባቸው የሚያደርግ ነው።
ቤጂንግ በዛሬው እለት ይፋ ባደረገችው የአጻፋ ምላሽ ከአሜሪካ የሚገቡ እንደ ስጋ፣ የግብርና ምርቶች፣ ፍራፍሬ እና አትክልቶች እንዲሁም የወተት ውጤቶች ተጨማሪ ከ10-15 በመቶ ታሪፍ ይጣልባቸዋል።
የሀገሪቱ የንግድ ሚኒስቴር ዋሽንግተን የገጠማትን የፌንታኒል ቀውስ "በቻይና ላይ ለማላከክ" እየሞከረች ነው ሲል ወቀሳውን ማጣጣሉን ግሎባል ታይምስ አስነብቧል።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


"በዮክሬን ቀውስ ውስጥ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ አካላት (አሜሪካና  አውሮፓ  ) ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ አስጠነቀቁ" ።

"ኢትዮጵያ በአውሮፓ ውስጥ ያሉ ለውጦች በጥንቃቄ እየተመለከተችም ነው ብለዋል"

ዘገባው የብሄራዊ ቴሌቪዥን ነዉ ፡፡

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ማስጠንቀቂያ!!..

የአዲስ አበባ መጅሊስ ከዚህ በኋላ በመስጂዶች ጉዳይ አይታገስም።

1446ኛው ታላቁ የረመዳን ወር መስጂዶች ደምቀውና ተውበው ህዝበ ሙሊሙን በተገቢው መንገድ በመቀበል እያሰተናገዱ ነወ።
በአብዛኛዎቹ መስጂዶች ህዝበ ሙሰሊሙ እምነቱ በሚያዘው መሠረት ዒባዳውን እያከናወነ ሲሆን በጣት በሚቆጠሩ መስጂዶች ሁከት ለማስነሣት የተደረጉ ሙከራዎችን በየመሰጂዱ የሚገኙ ኮሚቴዎች፣ ሀዲሞችና ህብረተሰቡ ባደረገው ጥረት በቁጥጥር ሰር ሊውሉ ችሏል።

በተለይም ጠሮ መስጂድ ፣ሎሚ ሜዳ(ዓሊ) መስጂድና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የሚገኘው ሀምዛ መሰጂድ የረመዳንን መግባት ተከትሎ በአንዳንድ ሰውር አላማ ያላቸው ግለሰቦች ሁከትና ብጥብጥ በማሰነሣት ከፍተኛ ችግር ሲፈጥሩ የቆዩ አካላት መሸሸጊያ ሆኖ የቆየ ቢሆንም መጅሊስ ከዛሬ ነገ ይቀየራሉ ብሎ ሁኔታውን አባታዊ በሆነ ትዕግሰት ይዞት ቆይቷል።

መጅሊሰ በእነዚህ ጥቂት መስጂዶች የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶችን ቢያደርግም ዕድሉን ባለመጠቀም ቡድኑ መሰጂድ ሰብሮ በመግባት፣ ጄነሬተር በማጥፋት፣ ለደህንነት የተገጠመ ካሜራን በመሰባበር እና አማኞች የተረጋጋ ዒባዳ(የአምልኮ ስርዓት) እንዳይከውኑና የረመዳንን ወር የብጥብጥና የረብሻ አውድማ የማድረግ እንቅሰቃሴያቸውን ቀጥለውበታል።

ከወራት በፊት ማዕከላቸውንና የብጥብጥ መነሻቸውን ዓሊ መስጂድ በማድረግ ሴቶችና ህፃናትን ከፊት በማሰለፍና የተወሰኑ ግለሰቦችን በገንዘብ በመደለል የተጀመረው ውንብድና ኢማሞችን ማይክ ቀምቶ በመደብደብ የተራዊ ሰላት እንዲቋረጥ እሰከ ማድረግ ደርሰዋል

ይህ በግልፅ በሚታወቁ ግለሰቦች የሚመራው ቡድን በተመረጡና ለማምለጥ ምቹ በሆኑ መስጂዶች ከተለያየ አካባቢ ተጠራርተው በመግባት አወል ሰፍን (የሰላቱን የመጀመሪያ ረድፍ) ለመሰጂድም ሆነ ለሸማግሌዎች ክብር የሌላቸው አሰቀድመው በመያዝ ረብሻ በማሰነሣት መሰጂዱን አውከዋል።

በየጊዜው በየመስጂዱ እየተዘዋወሩ ሁከት የሚፈጥሩ አካላት በሚገባ የሚታወቁና መረጃ ያለን ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ ለህዝብ እንደምናሳውቅ እየገለፅን መጅሊሱ ከዚህ በላይ እንደማይታገሰና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የፀሎት ቦታዎች ሠላማዊ እንዲሆኑ መስራቱን እንደሚቀጥል ለህዝበ ሙስሊሙ ያሣውቃል።

መጅሊሱ ካለበት ሀላፊነትና ተጠያቂነት አኳያ ጉዳዩን በትዕግሰት መያዙ አግባብ ቢሆንም በዚህ የሠላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የመተዛዘን ወር በሁለቱ መስጂዶች በተፈጠረው አሳፋሪ ተግባር ክፉኛ ማዘኑን እየገለፀ ሙስሊሙ ማሕበረሰብ ዒባዳውን(የአምልኮ ሥርዐቱን) የሚፈፅምባቸው መስጂዶች ሠላማቸው እንዲጠበቅ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሠራ በድጋሚ ለመግለፅ ይወዳል።

የአ/አ/ከ/እ/ጉ/ከ/ም ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ኦብነግ፣ ከስድስት ዓመት በፊት አሥመራ ላይ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ከተፈራረመው የሰላም ስምምነት መውጣቱን አስታውቋል።

መንግሥት ለንግግር ዝግጁ መኾኑን በመግለጡ ለንግግር አንድ ቡድን ሰሞኑን ወደ ናይሮቢ ልኮ እንደነበር የገለጠው ግንባሩ፣ መንግሥት ግን በንግግሩ ላይ ሳይገኝ ቀርቷል በማለት ከሷል። ይልቁንም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሞሐመሐድ፣ የኦብነግ አባል ያልኾኑ ግለሰቦችን ሰብስበው ኦብነግ ከመንግሥት ጋር እየተነጋገረ በማስመሰል ዓለማቀፉን ኅብረተሰብ ለማሳሳት ሞክረዋል በማለት ግንባሩ ወቅሷል። መንግሥት በሰላም ስምምነቱ መሠረት፣ የግንባሩን የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ኅብረተሰቡ ለመቀላቀል አለመቻሉን፣ ግንባሩ ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዳያደርግ እንቅፋት መኾኑንና ግንባሩ በምርጫ ቦርድ በኩል ሕጋዊ ሰውነት እንዳይኖረው ማድረጉንም የግንባሩ መግለጫ ዘርዝሯል። በሶማሌ ሕዝብ የግዛት አንድነትና የሃብት ባለቤትነት ዙሪያ ንግግር እንዲደረግ ግንባሩ ላቀረበው ተደጋጋሚ ጥሪ መንግሥት አፈናንና ጭፍለቃን መርጧል ያለው የግንባሩ መግለጫ፣ ግንባሩ ከእንግዲህ የሶማሌ ሕዝብን የራስን ዕድል በራስ መወሰን መብት ለማስከበር ሌሎች አማራጮችን እንደሚከተል ገልጧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የግንባሩን ምክትል ሊቀመንበር ጨምሮ የግንባሩን ማዕከላዊ ኮሚቴ እንወክላለን ያሉ ግለሰቦች ይህንኑ የግንባሩን መግለጫ እንደማያውቁትና መግለጫውም ግንባሩን እንደማይወክል መግለጣታቸውን የመንግሥት የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ግለሰቦቹ፣ ኦብነግ ለአሥመራው የሰላም ስምምነት አኹንም ተገዢ እንደኾነ አስታውቀዋል ተብሏል።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


call 📞0914280819
መርጌታ ውዴ የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች
1🍀 ለገበያ
2🍀 ለመስተፍቀር
3🍀 ለመፍትሄ ሀብት
4🍀 ለበረከት
5🍀 ለጥይት መከላከያ
6🍀 ለስንፈተ ወሲብ
7🍀 የተወሰደ ገንዘብ ለማስመለስ
8🍀 ራዕይ የሚያሳይ
9🍀 ለዓቃቤ ርዕስ
10🍀 ለመክስት
11🍀 ለቀለም(ለትምህርት)
12🍀 ሰላቢ የማያስጠጋ
13🍀 ለመፍትሔ ስራይ
14🍀 ጋኔን ለያዘው ሰው
15🍀 ለሁሉ ሠናይ
16🍀 ለቁራኛ
17🍀 ለአምፅኦ
18🍀 ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ
19🍀 ለግርማ ሞገስ
20🍀 ለቁማር
21🍀 ለዓይነ ጥላ
22🍀 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
23🍀 ለሁሉ መስተፋቅር
24🍀 ጸሎተ ዕለታት
25 🍀ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
26🍀 ለእጅ ስራ

ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ ለማንኛውም ነገር ያናግሩን መፍትሄ አለን!!!
ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
☎ 📞📞
0914280819
 
ባላቹህበት እንሰራለን


በሳዑዲ ዓረቢያና በኦማን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 470 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በዚህ ሳምንት ውስጥ 180 ወንዶች፣ 109 ሴቶች እና 13 ጨቅላ ህፃናት በድምሩ 302 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገር የተመለሱ ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 56 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

በተያያዘ ዜና በሳምንቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 157 ወንዶች 11 ሴቶች በድምሩ 168 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው የተመለሱ መሆኑ ታውቋል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ስራ እስካሁን 91 ሺህ 420 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ሆሊውድ በመሬት መንቀጥቀጥ መመታቷ ተሰማ

የኦስካር ሽልማት በተካሄደባት ትናንት ምሽት፣ የካቲት 23/ 2017 ዓ.ም ሆሊውድ በርዕደ መሬት ተመትታ ነበር ተባለ።
የርዕደ መሬቱ ማዕከል የነበረው የኦስካር ሽልማት ከተዘጋጀበት ሰሜናዊ ሆሊውድ፣ ዶልቢ ቲያትር አቅራቢያ መሆኑም ተገልጿል።

3.9 ሬክተር ስኬል የተመዘገበው ርዕደ መሬት ስላደረሰው ጉዳት የተገለጸ ነገር የለም።

ርዕደ መሬቱ የተከሰተው የኦስካር ሽልማትን ተከትሎ ታዋቂው ቫኒቲ ፌይር መጽሄት በሚያዘጋጀውና በርካታ ታዋቂ ሰዎች ድግስ ላይ ተሰባስበው በነበረበት ወቅት ነው።

ርዕደ መሬቱ የተከሰተበት ሰዓት በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ አራት ሰዓት ገደማ ነበር።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


"የፈጠራ ክስ ቀርቦብኛል"- ኤርትራ

ተመድ እና የአውሮፓ ህብረት የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር ገብተው ጥቃት እየፈፀሙ መሆናቸውን ተከትሎ ያቀረበባትን ክስ ኤርትራ አስተባበለች።


የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስቴር የማነ ገ/መስቀል በx ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አውሮፓ ህብረት እና ተመድ እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ተመሳሳይ እና የፈጠራ ክስ በኤርትራ ላይ መስርቷል ሲሉ ገልፀዋል።


በጄኔቫው ስብሰባ ላይ ኤርትራ በትግራይ ክልል ወረዳዎች ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየፈፀመች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ይሁንና ኤርትራ ክሱን የፈጠራ ክስ ነው ስትል አስተባብላለች።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከ9መቶ ጊዜ በላይ ጥሳለች ሲል የጋዛ መንግስት ከሰሰ፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ከጥር 19 ጀምሮ እስራኤል ስምምነቱን ከ9መቶ ጊዜ በላይ ጥሳለች ሲል አስታዉቋል፡፡

ስምምነቱ ተግባራዊ በሆነበት ወቅት እንኳን በተለያዩ የፍልስጤም ግዛቶች ዉስጥ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማዊያን በእስራኤል ጥቃት ህይወታቸዉ እንዲያልፍ እና ከባድ ጉዳት እንዲደርስባቸዉ ሆኗል ነዉ ያለዉ፡፡

ጥቃቱ የአየር እና የከባድ መሳሪያ ድብደባ፣ የሰብዓዊ ድጋፎች እንዳይገቡ ማድረግ፣ በዜጎች ላይ ተኩስ መክፈት ፣ ቤቶችን እና መኪኖችን ማቃጠልን ያካተተ ነበር ሲል አስታዉቋል፡፡

በተጨማሪም ወደ ጋዛ ነዳጅ እንዳይገባ በማድረግ እና ከ2መቶ60 ሺህ በላይ ድንኳኖች እና መጠለያዎች እንዳይደርሱ በማድረግ ጭምር የተደረገ ነዉ ብሎታል፡፡

የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ እና አሸማጋዮች እስራኤል ጥቃት ማድረሷን እንድታቆም እና በተኩስ አቁም ስምምነቱ መሰረት የገባችዉን ሃላፊነት እንድትወጣ ጫና እንዲያደርጉባት ጠይቋል፡፡

የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር፤ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ በእስራኤል ጥቃት ህይወታቸዉ ያለፉ ፍልስጤማዊያን ቁጥር 1መቶ16 ደርሷል፤ የተጎጂዎች ቁጥር ደግሞ ከ4መቶ90 በላይ ሆኗል ሲል አስታዉቋል ሲል ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


በጋምቤላ ክልል ከ 10 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ ተባለ።

በክልሉ ባለፉት ሁለት አመታት በተፈጠረ ግጭት በሶስት  ወረዳዎች ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች  ከመኖሪያ ቀያቸዉ መፈናቀላቸዉ ተነግሮናል።


በክልሉ ተከስቶ በነበረዉ ከፍተኛ  ግጭት እና  አለመረጋጋት ምክንያት በተለይ በጆር÷ ኢታንግ÷ አኮቦ ወረዳዎች ላይ 10 ሺህ 333 ሰዎች ተፈናቅለዋል።

በጋምቤላ ክልል የኑዌር እና አኝዋክ ብሄረሰቦች በሚገኙበት ኢታንግ ልዩ ወረዳ በባለፉት ሁለት አመታት ግጭት የ አስር ቀበሌ ነዋሪዎች ቅያቸውን ጥለዉ መሸሻቸዉ ተገልፆል።

ከኢትዩ ኤፍኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት የጋምቤላ ክልል የአደጋ ስጋት  ስራ አመራር አገልግሎት ዳይሬክተር ጃክ ጆይ በነባር ብሄረሰቦቹ መካከል  መነሻ ሆኖ በነበረዉ ግጭት በዚህ ወረዳ ብቻ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ሁለት ሰዎች ተፈናቅለዉበታል ብለዋል።

በተጨማሪም ከዚህ ዉስጥ በጆር እና አኮቦ ወረዳ ዉስጥ በነበሩ 8 ቀበሌ ዎች ከ 5 ሺህ በላይ  የሚሆኑ ተፈናቃይ  ነዋሪዎች አሉ  ተብሏል። 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን በኢታንግ ልዩ ወረዳ ላይ በተወሰኑ ነዋሪዎች መካከል የተነሳዉ አለመግባባት ብሄርን መሰረት አድርጎ ወደ ዉጥረት መሸጋገሩን ኮምሽኑ ከነዋሪዎች መስማቱን በወቅቱ  ገልፆ ነበር።

አቶ ጃክ በጋምቤላ ክልል የአመራር ለዉጡን ተከትሎ ሁለቱ ብሄረሰቦችን ዉይይት እንዲያደርጉ እና ተፈናቃዩችን ወደ ቀያቸው  ለመመለስ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

በሶስቱ ወረዳዎች የተፈናቀሉ አብዛኞቹ የአኝዋክ ብሄረሰቦች በመሆናቸዉ ወደ ቀያቸዉ እንዲመለሱ ከስምምነት መደረሱን ዳይሬክተሩ ለጣቢያችን ገልፀዋል።

ተፈናቃዮቹ አሁን ላይ በኢታንግ ልዩ ወረዳ ባለ መጠለያ የሚገኙ ሲሆን የተቃጠሉ ቤቶቻቸዉን መገንባት እና መልሶ ማቋቋም እንዲቻል  ለማድረግ ስራ መጀመሩን አቶ ጃክ ተናግረዋል።


ከዚህ ቀደም ጣቢያችን አነጋግሯቸዉ የነበረዉ የጋምቤላ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ሀላፊዉ አቶ ማበር ኮር አሁን ላይ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ስለመገኘቱ ነግረዉናል።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ቲክቶክ ሕፃናትን በሚያካትቱ የወሲብ የቀጥታ ስርጭት ትርፍ እያገኘ ነው ተባለ

ቲክ ቶክ ገና ከ15 ዓመት በታች በሆኑ እና በአሥራዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች በሚከናወኑ ወሲባዊ የቀጥታ ስርጭት ትርፋማ እየሆነ እንደሚገኝ ተመላክቷል። በኬንያ የሚኖሩ ሦስት ሴቶችን እንደተናገሩት ይህን ተግባር የጀመሩት በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያሉ ነው። በሌሎች የመልእክት መላላኪያ መድረኮች ለሚላክ ወሲባዊ ይዘት በግልፅ ለማስተዋወቅ እና ክፍያ ለመደራደር ቲክቶክን እንደተጠቀሙ ተናግረዋል።

ቲክ ቶክ “ለመሰል ብዝበዛ ምንም ትዕግስት የለኝም” ሲል ለቢቢሲ አስታውቋል። የቀጥታ ስርጭቶች ከኬንያ በቲክ ቶክ ታዋቂ ናቸው ። በእያንዳንዱ ምሽት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ሴቶች  በአለም ዙሪያ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚመለከቱት ገጾች ላይ ሲጨፍሩ ይታያል።ናይሮቢ ውስጥ ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ነው፣ እና የቲክ ቶክ ህይወት ሙሉ በሙሉ እንደቀጠለ ነው። አንዲት ሴት ካሜራዋን አብርታ በመቀመጫዋ ስትጨፍር ወይም ቀስቃሽ ምስል ስትነሳ ሙዚቃ በኃይ ይደመጣል፣ ሌሎች ተጠቃሚዎች እርስ በርሳቸው ይጨዋወታሉ። ስሜት ገላጭ ምስሎች "ስጦታዎች" ከዚያም ይቀጥላሉ።ባየናቸው አንዳንድ የቀጥታ ስርጭቶች ላይ የጾታዊ አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ ኮድ የተደረገባቸው የወሲብ ቃላት ጥቅም ላይ ውለዋል ሲል ቢቢሲ ዙግቧል።

የኢሞጂ ስጦታዎች ለቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት ክፍያ ሆነው ያገለግላሉ ። ምክንያቱም ቲክቶክ ግልጽ የሆኑ ወሲባዊ ድርጊቶችን እና እርቃን ይዘቶችን ስለሚያስወግድ ነው።በሌሎች መድረኮች ላይ የበለጠ ግልጽነት ያለው ይዘት ይላካል። ስጦታዎች ወደ ገንዘብ ሊለወጡ ይችላሉ።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል

የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በየካቲት ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የነዳጅ ማደያዎች በነዳጅ ውጤቶች ግብይት አዋጁና በአሠራር መመሪያው መሠረት ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን በታማኝነት እንዲያገለግሉ ለኢፕድ በላከው መረጃ አመላክቷል።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


call 📞0914280819
መርጌታ ውዴ የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች
1🍀 ለገበያ
2🍀 ለመስተፍቀር
3🍀 ለመፍትሄ ሀብት
4🍀 ለበረከት
5🍀 ለጥይት መከላከያ
6🍀 ለስንፈተ ወሲብ
7🍀 የተወሰደ ገንዘብ ለማስመለስ
8🍀 ራዕይ የሚያሳይ
9🍀 ለዓቃቤ ርዕስ
10🍀 ለመክስት
11🍀 ለቀለም(ለትምህርት)
12🍀 ሰላቢ የማያስጠጋ
13🍀 ለመፍትሔ ስራይ
14🍀 ጋኔን ለያዘው ሰው
15🍀 ለሁሉ ሠናይ
16🍀 ለቁራኛ
17🍀 ለአምፅኦ
18🍀 ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ
19🍀 ለግርማ ሞገስ
20🍀 ለቁማር
21🍀 ለዓይነ ጥላ
22🍀 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
23🍀 ለሁሉ መስተፋቅር
24🍀 ጸሎተ ዕለታት
25 🍀ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
26🍀 ለእጅ ስራ

ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ ለማንኛውም ነገር ያናግሩን መፍትሄ አለን!!!
ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
☎ 📞📞
0914280819
 
ባላቹህበት እንሰራለን


የባህር በር ለማግኘት ቆርጫለሁ ያለችው ኢትዮጵያ ከወደ ኬኒያ ያልተጠበቀ የምስራች ሰምታለች።

የኬንያው ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶ ኢትዮጵያ የላሙ ወደብን እንድትጠቀም የሚያስችል ስምምነት መፈፀማቸውን ተናግረዋል፡፡ በላሙ ካውንቲ ተገኝተው ፕሬዝደንቱ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸውን ምርቶች በዚህ ወደብ በኩል ማስገባት የሚያስችል ስምምነት ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር አዲስ ወደብ ለማግኘት ይፋ ባልተደረገ ሰነድ ስምምነት እየፈጸመች መሆኑ ጭምጭምታ በሚሰማበት ሰዓት ነው የኬኒያው ፕሬዝዳንት ይሄን ያበሰሩት።

ፕሬዝዳንት ሩታ ይሄን ሲናገሩም “በቅርቡ ኢትዮጵያ ይህንን ወደብ መጠቀም እንድትችል ስምምነት አድርገናል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ የሚያስገባቸውን ምርቶች በላሙ ወደብ በኩል ማስገባት ሲጀምር ለበርካታ ሰዎች የስራ አድል የምንፈጥር ከመሆኑም በላይ የአካባቢውን ኢኮኖሚ እናሳድጋለን” ያሉ ሲሆን በቅርብ ቀናት ውስጥ በላሙ ወደብ የአካባቢው አገራት መሪዎች የሚገኙበት ግብዣ እንደሚከናወንም አስታውቀዋል፡፡ 

ከሞምባሳ ቀጥሎ የኬንያ ሁለተኛው ትልቁ ወደብ የሆነው ላሙ የመንገድ ስራ ግንባታ ከተጀመረ ከአስር አመታት በላይ ያለፈው ሲሆን መንገዱ በኢትዮጵያ በኩል አድርጎ እስከ ደቡብ ሱዳን የሚዘረጋ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶ እንደገለፁት በዚህ ፕሮጀክት የላሙ ወደብ በሶስት ክፍሎች የማልማት ስራ እንደሚከናወንለት እቅድ የተያዘ ሲሆን አንደኛው ምእራፍ ተጠናቆ አሁን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆኗል ሲል ካፒታል ኒውስ ዘግቧል፡፡

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ከአዲግራት ከተማ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 5.2 የተለካ ርዕደ መሬት ተከሰተ

ዛሬ እሁድ ከአዲግራት ከተማ 46 ኪሎ ሜትር በስተምስራቅ ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ ላይ በሬክተር ስኬል 5.2 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት ገለጸ። ርዕደ መሬቱ የተከሰተው ከቀኑ 5 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ላይ መሆኑንም መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአፋር ክልል ባሉ አካባቢዎች ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰትም፤ በትግራይ ክልል ከተሞች አቅራቢያ ርዕደ መሬት ሲመዘገብ ግን በዚህ ዓመት የመጀመሪያው ነው። የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ቀጠና የተከሰተ መሆኑን የጠቆመው የአውሮፓ ሜዲትራንያን ሴይስሞሎጂ ማዕከል (EMSC)፤ መጠኑም በሬክተር ስኬል 5.3 የተለካ እንደሆነ አስታውቋል።

በኤርትራ ከአንድ ሳምንት በፊት የደረሰ ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 4.6 ሆኖ ተመዝግቧል። የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው በቀይ ባህር ሰሜናዊ አቅጣጫ ከአስመራ 24 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ አካባቢ ነበር። በሀገሪቱ ባለፈው ታህሳስ ወር አጋማሽም እንዲሁ ተመሳሳይ ርዕደ መሬት ተመዝግቧል።

በሐምሌ 2015 ዓ.ም. በኤርትራ ባህር ዳርቻ ዳህላክ ደሴት አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተደጋጋሚ ንዝረቶች አስከትሎ እንደነበር ይታወሳል። ንዝረቱን በሽሬ፣ አዲግራት፣ አድዋ፣ አክሱም እና መቐለ ከተማ ያሉ ነዋሪዎች መስማታቸውን በወቅቱ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸው ነበር።

Via:ኢትዮጵያ ኢንሳይደር


@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ኢንተርናሽናል ሜዲካል ኮር የተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በቋራ ወረዳ ከታኅሳስ ወር መጨረሻ ወዲህ በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ አምስት ሰዎች እንደሞቱና 270 ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ አስታውቋል።

ባካባቢው ያለው የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት፣ የንጽህና አጠባበቅ ጉድለትና የሰዎች እንቅስቃሴ በሽታው በስፋት እንዲሠራጭ ሊያደርገው እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል ተብሏል። በዞኑ በሽታው ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ባንድ የጸበል ቦታ ውስጥ ከተከሰተ ወዲህ፣ በክልሉ በ16 ዞኖች በ60 ወረዳዎች የተሠራጨ ሲኾን፣ እስካሁን 4 ሺሕ 983 ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ የድርጅቱ መረጃ ያመለክታል።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ኢትዮጵያ ላሙ ወደብን ተጠቅማ ምርቶችን ለማስገባት ተስማምታለች ሲሉ ፕሬዝዳንት ሩቶ ገለጹ

ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከየብስ ተከብባ ከምትገኘው ኢትዮጵያ ጋር ወደቡን ወደ ውስጥ ሀገር ለሚገቡ ምርቶች ማጓጓዣነት ለመጠቀም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

የላሙ ወደብ የክልሉ የንግድ ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል ኬንያ እና ጎረቤት ሀገራት ባደረጉት ስምምነት መሰረት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሊደረግበት ተዘጋጅቷል።

ፕሬዝዳንት ሩቶ በላሙ ምስራቅ ክልል በንዳው ደሴት የመጀመሪያውን የኬንያ ከግሪድ ውጪ የፀሐይ ኃይል ተደራሽነት ፕሮጀክት በሐሙስ ዕለት ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት "ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የላሙን ወደብ መጠቀም ለመጀመር ተስማምተናል፤ ይህም ተጨማሪ የስራ እድሎችን ለመፍጠር እና የዚህን ክልል ኢኮኖሚ ለማሳደግ ያስችለናል" ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ከሞምባሳ ወደብ ቀጥሎ ሁለተኛ የሆነውን የላሙን ወደብ ላይ የሀገራት መሪዎችን በቅርቡ እንደሚያስተናግዱ ገልጸዋል።በዚህም በላሙ ወደብ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ዘመናዊ ማቆሚያዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።

Via Capital Newspaper

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


እንኳን ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


የአሜሪካው ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) የገንዘብ እርዳታ ካቆመ ወዲህ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች መካከል 85 በመቶዎቹ ሥራቸውን ማቆማቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

በተለይ በሰብዓዊ መብቶች፣ በሰላም፣ በጤና እና ልማት ዘርፎች የሚሠሩ ድርጅቶች ይበልጥ ተጎጂ እንደኾኑ የጠቀሰው ዘገባው፣ በትግራይ ለ100 ሺሕ የጦርነት ተፈናቃዮች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ያቀርብ የነበረ መንግሥታዊ ያልኾነ ድርጅትም ሥራ ማቆሙን አመልክቷል።

መንግሥትም፣ የውጭ ዜጋ የሆኑ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ የሚያግድ ሕግ እያዘጋጀ መኾኑን ምንጮች መናገራቸውን የዜና ምንጩ ዘገባ ያመለክታል።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.