Postlar filtri


Channel owner's dan repost
For sale 💰
Monetized telegram channel

Start making money 🤑
Any one who wants to buy this channel contact
@Zedreamer


የመውጫ ፈተና በዚሕ አመት ለምትወስዱ ተማሪዎች በሙሉ።

©️CoBE Registrar Office
📄

@exitnewss


Re exit Exam Registration!

ለቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ምዝገባ https://exam.ethernet.edu.et የሚለውን ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ የሚቻል መሆኑ እንገልጻለን።

📄

@exitnewss


" የ12ኛ ክፍል ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ ፥ " ይሄ አራተኛው ነው በአዲሱ የፈተና አሰጣጥ ፈተና የሚሰጥበት " ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከትምህርት ቤቶች ወጥቶ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አስገብቶ ፈተና እንዲሰጥ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ስለዘንድሮው የ2017 ዓ/ም ፈተና በተናገሩበት ወቅት 150 ሺህ ተማሪዎች ፈተናቸውን በኦንላይ እንዲወስዱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ብርሃኑ (ፕሮፌሰር) ፥ " እንደ ከዚህ ቀደሙ አድካሚ በሆነ ከቦታ ቦታ ልጆችን እያዘዋወሩ ከመሄድ ባለፈው ዓመት 29 ሺህ ተማሪ ነበር ኦንላይን ፈተና የሰጠነው ዘንድሮ ደግሞ 150 ሺህ ተማሪ ኦንላይን ፈተና ለመስጠት እየተዘጋጀን ነው " ብለዋል።

ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ቆርጠው ባይናገሩም ፈተናው ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንዲሰጥ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
📄

@officialexit


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
📄

@officialexit


ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ

👉የሁለተኛ ሴሚስቴር እና የመውጫ ፈተና ካላንደርን ስለ ማሳወቅ



ትምህርት ሚኒስቴር የ12 ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 18 /2017 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ያሳወቀ ሲሆን ከዚያ በፊት ዩኒቨርሲቲዎች ባወጡት አመታዊ  የጊዜ ሰሌዳ መሠረት

~2ኛ ሴሚስቴር ማጠቃለያ ፈተና የሚሰጠው ከግንቦት 25 እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ/ም

~ ለተመራቂ ተማሪዎች ማጠቃለያ ፈተና ከግንቦት 13-28/2017 ዓ/ም

~የመውጫ ፈተና  ከሰኔ 02/2017 ዓ/ም እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ/ም

~የምረቃ ስነ -ስርዓት ከ14 እና 15  2017 ዓ/ም  መሆኑን እናሳውቃለን

አ/ም/ዩ/ተማሪዎች ህብረት /ጽ/ቤት

   
📄

@exitnewss


#Update

ከሚያዝያ 1-3/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ አመልካቾች፥ የፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (Orientation) እና የሙከራ ፈተና (Mock Exam) ማክሰኞ መጋቢት 30/2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት የሚሰጥ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

📄

@exitnewss


#ExitExamCertificate

ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ቅፅ አዘጋጅቶ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልኳል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብሔራዊ የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በቅድመ-ምረቃ መውጫ ፈተናው የአፈጻጸም መመሪያ መሰረት፥ የመውጫ ፈተና ውጤት በተማሪዎች ሰርተፍኬት (Temporary Degree) ወይም ትራንስክሪፕት ላይ አልፏል (PASS) ወይም ወድቋል (FAIL) በሚል እንዲቀመጥ ሚኒስቴሩ አዟል።

በዚህም የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች የሚሰጡ ኮርሶችን ማጠናቀቃቸውን የሚያረጋገጥ ሰርተፊኬት የሚሰጣቸው ሲሆን፤ ጊዜያዊ ዲግሪ የሚሰጠው ተፈታኙ/ተፈታኟ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ ወስዶ/ወስዳ የማለፊያ ነጥብ ሲያስመዘግብ/ስታስመዘግብ ብቻ እንደሚሆን በሰርተፊኬቱ ይገለጻል።

(የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ እና የመውጫ ፈተና የውጤት ሰርተፍኬት ፎርማት ከላይ ተያይዟል።)
📄

@exitnewss


🦋Official Exit dan repost
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት  እንዲያስተምሩ ሊገደዱ ነው


ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።

ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ በቀረበ ጥናት ላይ  ውይይት ሲደረግ፣ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።

ላለፉት ዓመታት(እሳቸው  በኃላፊነት ከተሾሙ ጀምሮ)፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ  እንዲሆን ካደረጉ መንስዔዎች መካከል፣ የመምህራን ብቃትና የተነሳሽነት ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ጠቁመዋል።

ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲቻል የተለያዩ ተግበራት እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

''የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ'' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ "በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል"ሲሉ ተናግረዋል። ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።

ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።

ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።

በቅርቡ በመምህራን ላይ በተደረገ ግምገማ ፣ 100,000 የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩ መታወቁን የተናገሩት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አሰራሩ በከፍተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንዲቀንስ የበኩልን እንደሚወጣ አስረድተዋል።

ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎችን ክፍተት ለማስተካከል ከተያዙ ዘርፈ ብዙ የማትጊያ ሥርዓቶች አንዱ፣ መምህራን በአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸውና የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋሙ ለማድረግ፣ "የመምህራን ባንክ" ማቋቋም አንዱ እቅድ መሆኑን አንስተዋል።

ባንኩ "በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባዋል ብለን እንጠብቃለን" ያሉት ሚኒስትሩ፣ በ2019 ዓ.ም ደግም በእርግጠኝነት ወደ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ አሰራር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
📄

@officialexit




🦋Official Exit dan repost
MRT.pdf
208.2Kb
1. የፈተናው መርሃ-ግብር


ሁሉም ተፈታኝ መጋቢት 30/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል፤ የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራትና፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል::

2. በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡

3. ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎችን፣ እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

4. በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ) አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረማችሁን ማረጋገጥ ይኖርባችኋዋል፣

5. ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን QR code ያለው የፈተና መግቢያ /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እያሳሰብን:-

▪️ ተመዛኞች ወደ ጣቢያ ከመምጣታችሁ በፊት ከዚህ ማስታወቂያ ጋር የተያያዘውን attachment በመክፈት የመረጣችሁትን የፈተና ጣቢያዎች መመልከት ይኖርባችኋል።

▪️ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ አይፈቀድም፡፡

▪️ በፈተና ወቅት ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግር በስልክ ቁጥር 0115186275/ 0115186276 መደወል የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡
📄

@officialexit




#EidAlFitr

የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ እሁድ ይውላል።

ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ በመታየቷ 1446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ እሁድ ተከብሮ ይውላል።


📄

@officialexit




የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ ሆነ
****

ከሰኔ 2017 ዓ.ም ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ መቀመጡ ተገልጿል።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በሁሉም የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚመቻችም ነው ተቋሙ ያስታወቀው።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝና ከከፍተኛ ትምህርት መረጃ አገልግሎት ጋር በማስተሳሰር ጥራት ያለው መረጃ ለማግኘት እና የሚሰጡ ሀገር ሀቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ይረዳል።
📄

@exitnewss


ከታች ያለዉ የተከፈለበት ማስታወቂያ ነዉ


#NGAT_Result

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ተለቋል።

ተፈታኞች ውጤታችሁን 👇
https//:result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት NGAT የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ።

📄

@officialexit


Channel owner's dan repost
⚠️ በእርግጠኝነት ይሄ ነገር ከአንድ ጓደኛችሁ ወይም ከምታውቁት ሰው ተልኳላችኋል 💀

👋 ተጠንቀቁ ጋይስ ይሄን እና መሰል link መቼም በፍጹም እንዳነኩ
accountachu በሌላ ሰዉ ሙሉ በሙሉ access ያገኛል (hack ትደረጋላቹ) ተሳስታችሁ ከነካችሁ ደሞ ከላይ በምታዩት ፎቶ በመግባት እናንተ ከምታውቁት device ውጪ አስወግዱት📸

ለምታቁት ሰው ሁሉ ይሄን መልእክት ላኩላቸው ⭐

እስቲ አጋጥሞት የሚውቅ 👍

@timeforcryptocurrency


🦋Official Exit dan repost
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ብቃት ማረጋገጫ ማስፈፀሚያ ሠነድ በማዘጋጀት ገቢራዊ ሊያደርግ ነው።

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች፣ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት በማስፈፀሚያ ሠነዱ ላይ ውይይት አካሒደዋል።

ሠነዱ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በትምህርት ሚኒስቴር እየተተገበሩ ከሚገኙ የሪፎርም ሥራዎች አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

ሠነዱ በየደረጃው ላሉ የሥራ ኃላፊዎች፣ አሠልጣኞች እና ሠልጣኞች ወጥ የሆነ አሠራር ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈፃሚ ኤባ ሜጄና (ዶ/ር) አስገንዝበዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት የስርዓተ ትምህርት ለውጥ፣ የቅድመ-ምረቃ መውጫ ፈተና (Exit Exam) እንዲሁም የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

📄

@officialexit


Channel owner's dan repost
#NEWS


ለረጅም ጊዜ በፈረንሳይ የቁም እስር ተወስኖበት የነበረው የቴሌግራም መስራች እና ባለቤት በዛሬው ዕለት በፈረንሳይ ፍርድቤት ውሳኔ ከፈረንሳይ ወደተባበሩት አረብ ኤምሬትሷ ቅንጡ ከተማ ወደሆነችው ወደዱባይ አቅንቷል👐


ይኽንንም በማስመልከት $TON ፈጣን አቀባበል አድርጎለታል 🥰


ከእሱ የቁም እስር በኋላ አንገቱን በእጅጉ አቀርቅሮ የነበረው የTON blockchain ማንሰራሪያውን የጀመረ ይመስላል🥰


@timeforcryptocurrency

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.