በአክሱም 159 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ በሚል ላለፉት አንድ መቶ ቀናት ከትምህርት ገበታቸው ውጪ መሆናቸው ተነገረ
በትግራይ ክልል አክሱም የሚገኙ 159 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ ተከልክለዋል በሚል ላለፉት አንድ መቶ ቀናት ከትምህርት ገበታቸው ውጪ መሆናቸው ተገለጠ ።
በትግራይ ክልል በዋነኝነት በሴቶች መብት ጉዳይ ዙርያ የሚሠሩ ስድስት ሲቪክ ተቋማት ሕገወጥ ያሉትን ይህን የትምህርት ክልከላ ተቃውመዋል ። የአክሱም ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት በዚህ ጉዳይ ዙርያ ምላሽ መስጠት አልቻለም ።
ሒጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ በሚከለክል የአክሱም ከተማ ትምህርት ቤቶች መመርያ ምክንያት ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ እስካሁን 159 ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከትምህር ገበታ ውጪ ሆነው እንዳለ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ይገልፃል ።
ጉዳዩን አስመልክቶ የትግራይ ትምህርት ቢሮ ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ መመርያ አስተላልፎ የነበረ ቢሆንም ይህ መመርያ በትምህርት ቤቶች መጣሱን፣ ከዚህ በተጨማሪ የፍርድ ቤት ውሳኔም ጭምር አለመተግበሩን የእስልምና ጉዳዮች ምክርቤቱ ይገልፃል።
በዚህ በአክሱም የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ርምጃ ምክንያትም ሴት ተማሪዎች ከትምህርት ውጭ መሆናቸው ተገልጿል።
#DW
📄
@Exitnewss