🎄💥እንቁ ᴛᴜʙᴇ™💥🎄


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


🎀..ችግሮችህ በሙሉ ሰው ሰራሾች ናቸው ስለዚህም በሰው ይፈታሉ ምንም አይነት ሰው ሰራሽ ችግሮች ከሰው አቅም በላይ ሊሆኑ አይችሉም••🎀

For any comment & cross👇
@KERODINA
ከቆያችሁ ብዙ ነገር ታገኛላችሁ
If you stay, you will find a lot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ፎቶዋቹ  ባማረ መልኩ #edit እንዲደረግ ከፈለጋቹ


DT Promotion dan repost
'https://t.me/addlist/37N4EgSzRtU3YjA0' rel='nofollow'>📱Bilbilli kee Orginaalaa yoo ta'e yeroo ati suura armaan gadii tuqxu information bilbila kee hunda ilaalta siif Fidaa
╭━━━━━━━╮
┃   ● ══  ▪      
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████
┃███████┃
┃███████┃
┃        🔘    ┃
╰━━━━━━━
Bilbilii Kee #Orginal Ykn #Copy Tahuu Isaa Adda Bafadhuu 👆👆

Waver👉 @FastVipProm


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰1️⃣8️⃣

ስልኬን ስከፍተው በጣም ብዙ ያልተሳካ ጥሪ ማሳወቂያ ገባልኝ አብዛኛው የማዘር ነው 17 ጊዚ ሞክራለች::

ሌላው ደሞ የማክቤል ነው ይሄ ደነዝ ምን ፈልጎ ነው እያልኩ( በውስጤ) ሌሎች የገቡልኝን textoch ሳላይ ወደ ማዘር ደወልኩ ::
ገና እንደጠራ አነሳቺው ሄሎ እማዬ በጣም ይቅርታ እሺ ደህና ነኝ እንዳታስቢ ስልኬ ቻርጅ ዘግቶብኝ ነበር ወደ ቤት እየመጣሁ ነው አልኳት ::

እናቴ ምንም አልተናገረችም በቀዘቀዘ ድምፅ እሺ ብቻ ብላ ስልኩን ዘጋቺው ብዙም ትኩረት አልሰጠሁትም ምክንያቱም እንደተናደደችብኝ ግልፅ ነው ቀለበቴን እያየሁ ለብቻዬ እስቃለሁ ልዑሌ እኔን እያየ ይስቃል እንዲሁ ስንሳሳቅ ሰፈሬ ደረስን::
በቃ ቻው ደህና ደር ፈጣሪ ያክብርልኝ ህይወቴን ከመበላሸትና ከምስቅልቅል ስላዳንክልኝ ብዬ ጉንጩን ስሜው ልወርድ ስል እጄን ያዘኝ ወደሱ ዞር ስል ከንፈሬን ግጥም አድርጎ ሳመኝ።
ልቤ ለ2 ክፍል አለ በጣም ከመደንገጤ የተነሳ እጄ ሁላ መንቀጥቀጥ ጀምሮ ነበር በእርግጥ ከንፈሬን ስሳም የመጀመሪያዬ አደለም ።
ተስሜ አቃለሁ ግን የትኛውም እንደዚህ አላስደነገጠኝም ደህና ደሪ አፈቅርሻለሁ ሲለኝ 
ቃላት ሁላ ጠፋብኝ ምላሴም ተሳስሯል ዝም ብዬ ከመኪናው ወረድኩ ቻው ብሎኝ ሄደ ።
እግሬ ሁላ ስራመድ ጉልበቴ እጥፍ እጥፍ ይላል ብቻዬን እንደ እብድ እስቃለሁ ከንፈሬን እነካለሁ ቀለቤቴን አያለሁ አረ ምን የማያደርገኝ ነገር አለ ።
በዚህ መሀል ግን ልዑሌ 1 ያለኝ ነገር ትዝ አለኝ ዘላለሜን ባይሆንም በህይወትp እስካለሁ እንከባከብሻለሁ 🤔🤔 ጥያቄ ሆነብኝ ለምንድነው ደጋግሞ ጤነኛ የሆነ ሰው ሳይ እቀናለሁ የሚለኝ ብዙ ጥያቄዎች ወደ ጭንቅላቴ መምጣት ሲጀምሩ ለራሴ  ፈጣሪ በአንድ ጀንበር ታሪክሽን ቀይሮልሻል በቃ ከሞት እንደታደገሽ ቁጠሪው ሌላ ነገር አታስቢ ደስታሽን አጣጥሚ አልኩኝ ።
ቤቴ ቀር ላይ ስደርስ  የውጪ በሩን ሳንኳኳ ትንሿ እህቴ መጥታ በሩን ከፈተችልኝና ቤት እንግዳ እየጠበቀሽ ነው ብላ ቀስርአት እንኳን ሳታየኝ ፊቷን አዙራ ወደቤት ገባች ማነው ደሞ እንግዳው አሁን የናቴን አይንስ እንዴት ብዬ ነው ማየው  እያልኩ ተከትያት ገባሁ.....ልክ  ስገባ ያ ማክቤል ተብዬ ውስጥ ተቀምጧል::,እንዴት ደሜ እንደፈላ ።

እያየሁት ሰላም ዋላቺሁ ብዬ ገባሁ ሁሉም ዝም አሉ እኔ ስገባ ማክቤል ተነሳና በቃ ልሂድ አይዞሽ እናቴ ብሎ ጉንጯን ስሟት ወጣ ተከትዬው ወጣሁ።

  ለምን መጣህ (በጣምተኮሳትሬ)
እናትሽ በጣም ተጨንቃ ደውላልኝ ነው አለ።
ለምን ላንተ ትደውላለች ካንተጋ ድጋሜ እንደማንገናኝ  አታቅም እንዴ አልኩት ቀለበቴን ለማሳየት እጄን አንዴ ፀጉሬ ላይ አንዴ ፊቴ ላይ እያደረኩ ።

እጄን አየና ባንዴ ፊቱ ቅይይር አለ እኔጃ ምናልባት አታቅም ይሆናል እሷን ጠይቂያት አለ ድምፁ ሁላ ሌላ ቅላፄ ነበረው እሰይ ቅጥል በል እያልኩ ነበር በውስጤ
ቀለበቱን ለማሳየት ነው ተከትዬው የወጣሁት!!!!

በቃ ቻው ብዬ ፊቴን ሳዞር ከፊት ለፊቴ ቆመና ቀለበትሽ በጣም ያምራል ምርጡ ነገር ሁላ ይገባሻል አለኝ::

እንባ እየተናነቀው ገርሞኝ ቀና ብዬ ሳየው እንባው ካይኑ አመለጠው ዞር ብሎ እንባውን ጠረገና አቅፎኝ በፍጥነት ከግቢ ወጣ ::

ከተጣላን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳዘነኝ ደሞም ገረመኝ ምን አስቦ ነው ዛሬ እንዲህ የሚሆነው ትናት እንደ አሮጌ ካልሲ አውጥቶ ጥሎኝ ዛሬ የራሴን life  ስጀምር የምን ማለቃቀስ ነው አቦ የራሱ ጉዳይ ሆ  ...

     ወደ ቤቴ ስገባ ቅድም ያላስተዋልኩትን አንድ ነገር ታዘብኩ የእናቴ አይን በጣምም ቀልቶ ነበር እንዳለቀሰች ግልፅ ነው አይኗን ሳየው በጣም ደነገጥኩ::

ምን ሆና ይሆን እያልኩ በልቤ ወደ እናቴ ተጠጋሁና አጠገቧ ሄጄ ቁጭ አልኩ እናቴ ለትንሿ እህቴ  ገብታ እንዲተኛ ነገረቻት ..... ተነስታ ሄደች  ።

እናቴ ፊቷን ወደኔ አዙራ ተስተካክላ ከተቀመጠች ቡሀላ

እኔ እስከዛሬ አስከፍቼሽ አቃለሁ ከሰው  አሳንሼሽ አቃለሁ አለቺኝ እንባዋን  እየጠረገች ግራ ያጋባል ሁኔታዋ ሁሉ እማዬ ምን ሆነሻል ስል አቋረጠችኝ።
ምንም ቃል እንዳተነፍሺ ሳወራ ብቻ አዳምጪኝ አለች እናቴን ለመጀመሪያጊዜ እንደዚህ ፈራኀት።

ዝም ብዬ የናቴን ሁኔታ እየተከታተልኩ የምታወራውን ማዳመጥ ጀመርኩ
    ምራቋን ዋጠችና አባትሽ ከሞተ ጀምሮ እንደሰው ቤት መቀመጥ ሳያምረኝ አዲስ መልበስ ሳልመኝ  አንቺ ከሰው እንዳታንሺ እህትሽ  ከጓደኞቿ  በታች እንዳትሆን  አድርጌ አሳደኳቺሁ ።

አባታችሁ የሚያደርግላቺሁን  ነገር
ሳላጎድል እያሟላሁ ለዚህ ደረጃ አድርሼሻለሁ ዛሬ ግን አንቺ እኔን እንደማንም ጥለሽኝ ለመሄድ ተነሳሽ እንደይሁዳ በመሳም ሸነገልሽኝ ለኔ ለናትሽ
ያውም እንደናት አይሉት እንደጓደኛ ሆኜ አሳድጌሽ .........

እንባዋን ሳየው አሳዘነቺኝ አይኗ ውስጥ ትልቅ የተስፋ መቁረጥ ምልክት ይነበብ ነበረ  ወዲያው ደብዳቤውን እንዳየቺው ገባኝ::

እናቴን በሆነ መንገድ ማስደሰት እንዳለብኝ እያሰብኩ ነው ግን በምን????????????????

ወዲያው አንድ ሀሳብ በውስጤ ብልጭ አለልኝና ከት ብዬ ሳኩ እናቴ ባንዴ እንባዋ ደረቀ ያበድኩ መስሏት መሰለኝ የናቴ አይን  አብሮኝ ይንከራተታል ።

ወዲያው surprise  እማዬ ብዬ ግራ እጄ ላይ ያደረኩትን ቀለበት አሳየኋት ምንድነው ምንድነው ይሄ ብላ እጄን እያገላበጠች ጣቴ ላይ ያደረኩትን ቀለበት ትመለከታለች ከዛ ደሞ ቀና ብላ እኔን ታየኛለች በጥያቄ አይን አፈጠጠችብኝ ጭንቅላቴ ውስጥ የመጡትን ውሸቶች መፈጣጠር ጀመረኩ።
ቀን  ልዑሌ  ደውሎ  እንደሚያፈቅረኝ ነገረኝና በጣም ደስ አለኝ ።

ልዑሌ ባስቸኳይ ላግኝሽ ብሎኝ ተገናኘን ከዛ ሳላስበው ተንበርክኮ እንዳገባው ጠየቀኝና እሺ አልኩት ።

እራት ልጋብዝሽ በዚሁ ሲለኝ አንቺንም ሰርፕራይዝ  ላድርግሽ ብዬ እቤት መጣሁና ወረቀቱን ሞነጫጭሬ ፅፌ ፊት ለፊት አስቀመጥኩት ሻንጣዬንም አንቺ እንደምታይው አድርጌ አዘጋጅቼው ሄድኩ አልኳት።
ይሄ ሁላ ውሸት ከየት እንደመጣ አላቅም ብቻ ግን የናቴ ፊት ባንዴ የደስታ ስሜት ሲላበስ እያየሁ ነበረ እናቴ ብድግ አለችና ጀርባዬን በጇ በሀይል መታችኝና ተጠመጠመችብኝ የምር መስሎኝ ደንግጬ ነበርኮ አፈር ያስበላሽ እያለች ትስመኛለች እጄን እያገላበጠች ታያለች ብቻ እንዴት እንዳሳዘነችኝ አማዬ እልልታውን ልታቀልጠው ነበር ባይመሽ ኖሮ ግን መሽቷል ።

ጥርስ በጥርስ እንደሆነች እና እራቱ እንዴት ነበር ብላ ጠየቀችኝ እኔም ስለ ልዑሌ ቤት ፊልም በሚመስል መልኩ መተረክ ጀመርኩ  ።


🔻ክፍል አስራ ዘጠኝ ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀

 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ
በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰1️⃣7️⃣

የተከፈተውን ዘፈን እየኮመኮምን እራታችንን ተመግብን እኔ ምንም እንዳልጠጣ ከለከለኝ ።

ስንጨርስ በቃ አሁን እንደንስ አለ(ከፊት ለፊቴ ቆሞ እጁን እየዘረጋልኝ እጄን እጁ ላይ አድርጌ ተነሳሁ ዝም ብለን እንቀሳቀሳለን አየዋለሁ ያየኛል ።
እኔ ከዚህ ህልም የምነቃበት ሰአት እንዳይደርስ ተሳቅቄ ሞትኩ እውነት አልመስልሽ አለኝ ሁሉም ነገር ።

እየደነስን እያለ ሆዴን በጣም ህመም ተሰማኝ
በቃ ልዑሌ ልቀመጥ ሆዴን አመመኝ አልኩት (ሆዴን በእጄ አየደገፍኩ) እሺ ልጃቺን እያስቸገረ ነው እንዴ አለኝ።

ደንግጬ ፍጥጥ አልኩበት ባክሽ እንዲህ አትይኝ ያው ሚስቴ ስትሆኚ የኔም ልጅ ነው ብዬ ነው ብሎ ጠቀስ አደረገኝ እየሳኩ ወደ ወንበሬ ተቀመጥኩ  እሺ ውዴ በጣም የምትወጂውን አንድ ዘፈን ንገሪኝ እና ልክፈትልሽ ከዛ ወደቤት እንሄዳለን አለኝ ።

     ትንሽ አሰብኩና ብዙ አለ የምወደው ግን አሁን የመጣልኝ የትልቁ ዳዊት ፅጌ
  እንዴትስ አደርጌ የሚለው ነው አልኩት።( እየተቅለሰለስኩ)
    ከፊት ለፊቴ መጥቶ ቆመና  ሰርፕራይዝ ነው አይንሽን ጨፍኚ አለኝ ያንተ ሰርፕራይዝ ደሞ ማብቂያ የለውም እንዴ
በቃ ይቺን ብቻ ግን ግለጪ ሳልልሽ ብትገልጪ ዋ አለኝ
እሺ ፕሮሚስ አልገልጥም ይኸው ጨፈንኩ ......
  ያለ ክላሲካል ዘፈኑ መንቆርቆር ጀመረ..
እንዴትስ አድርጌ
ፍቅሬን ልግለፅልሽ
ምን ቃል ተናግሬ ላሳይሽ
ጨነቀኝ ጠበበኝ
ጠፋኝ የምልሽ እወቂልኝ ባክሽ እንደምወድሽ
.
.
.
. 
ተመስጬ እየሰማሁ ዝም ሲል ከሆነ ሰመመን ነቃሁ አይኔን ስገልጥ ልዑሌ ብቻ ነው ከፊት ለፊቴ ያለው እንዴ የታለ አልኩትግራ ገብቶኝ 🙄
ማን ??
አሁን የዘፈነልኝ ሰው ነዋ
አረ ተረጋጊ እራሴ ነኝ የዘፈንኩልሽ
kkk እስኪ ሳልፈልግ አታስቀኝ !!

ምን ያስቅሻል ከምር እኔ ነኝ!
እስኪ ልዑሌ ማልልኝ
ሰላሜ ሙች እኔ ነኝ
ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ ጩኸት ይሁን ሳቅ በማይለይ መልኩ ጮክ ብዬ ሳኩ :: ምነው ምን ሆነሽ ነው ሴትዮ አለኝ የኔ ሳቅ እየተጋባበት አረ ድምፅህኮ የዘፋኝ ነው ( ከምርም ግን የልዑሌ ድምፅ ሌላ አለም ውስጥ ነበር የሚከተው ቅላፄው ድምፁ በቃ አስከ ጥግ ድረስ ነው ሰውነትን ሰርስሮ ሚገባው ሌላ አለም ውስጥ ነው የሚከተው ፈጣሪ ሳይደግስ አይጣላ ይሉ ነገር እኔ ፈጣሪን የማማርርበት ሳጣ ለምን ድምፅ አልሰጠኝም ብዬ እናደዳለሁ የመናደድ መብቱ እንደሌለኝኮ አቃለሁ ግን የሰው ልጅ ከተሰጠው ይልቅ የሌለውን የሩቁን ማየት  ይወዳል ለኔ የተሰጠኝ የራሴ የሆነ መክሊት እንዳለኝኮ አቃለሁ መክሊቴን በመፈለግ ፈንታ ግን የሌለኝን እያነሳሁ አማርራለሁ ግን አሁን በባሌ ክሶኛል😜😜😜)

ድሮ ልጅ እያለሁ ወደፊት ሀብታም ስሆን ሁሌ የሚዘፍንልኝ የሚያምር ድምፅ ያለው ሰው እቀጥራለሁ እል ነበር :;

ልዑሌ ግን ሀብታም ባይሆን ኖሮ ዘፋኝ እንደሚሆን ምንም ጥር ጥር የለኝም)

ልዑሌ ድምፄ እንደሚያምርማ አቃለሁ በይ አሁን ተነሺ ወደቤትሽ እንሂድ ደሞ ማዘር  ሽማግሌ ስልክ አይሆንምገና ሳያገባት አሽመሽቶብኛል እንዳይሉ ብሎ ተነሳ እኔም ተከትዬው ተነሳሁ ያን የተንጣለለ ግቢ በአይኔ ሙሉ ለማየት እየከበደኝ ተሰናበትኩትና ወጣሁ መኪና ውስጥ ገብተን እየሄድን ለካ ትዝ ሲለኝ ከመግባታችን በፊቴ ልዑሌ ስልካችንን እናጥፋ ብሎኝ አጥፍቼዋለሁ::

ወይኔ ማዘር ደውላ ይሆናልኮ ብዬ ወደ ቦርሳዬ ገባሁና ስልኬን አወጣሁ ሰአት ሳይ 2:45 ይላል በጣም ነው የደነገጥኩት  ማዘር ስልኬን አጥፍቼ እስከዚህ ሰአት ሳመሽ ምን ልትሆን እንደምችል ማሰብ እራሱ አልፈልግም ::


🔻ክፍል አስራ ስምንት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀

 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰1️⃣6️⃣

አይኔን ገልጬ ስመለከት ማመን ስላቃተኝ መልሼ ጨፈንኩትና በድጋሜ ገለጥኩት  ሁነቱ በዛው ቀጥሏል ልዑሌ ከፊት ለፊቴ ተንበርክኮ የታገቢኛለሽ ወይ ጥያቄ እየጠየቀኝ ነበር  ::

   ግራ ተጋብቼ🤔🤔 ልዑሌ ሙድ እየያዝክብኝ ነው እንዴ አልኩት (እንባ በተናነቀው ድምፅ ) አረ ሰላሜ ስታስቢው እንዴት በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ላይ እቀልዳለሁ   ይልቅ እሺ በይኝ እና  ዘላለምሽን ደስተኛ እንደማረግሽ ቃል ባልገባልሽም  በህይወት እያለሁ ግን እንደማስደስትሽና ለአንዲት ሰከንድ አንደማይከፋሽ አረጋግጥልሻለሁ አለኝ። አይኑ በእንባ ተሞልቷ ።

የኔን እንባ ግን ማስቆም አልቻልኩም ዝም ብሎ ይፈሳል ፈጣሪዬን ከዚህ ህልም ለዘላለም እንዳይቀሰቅሰኝ አየለመንኩት ነው ።
     ግን ደግሞ ህልም አልነበረም ልዑሌ የምር እንዳገባው እየጠየቀኝ ነበር ።

ምን ማለት እንዳለብኝ እንኳን አላቅም ብቻ  ግራ ገብቶኝ ልዑሌ ግን እርግጠኛ ነህ ማለቴ በደንብ አስበህበታል : ቆይ ትናት ምን እንዳልኩ  እረሳኸው እንዴ እርጉዝ ነኝ የሌላ ሰው ልጅ በሆዴ አለ ነውኮ ያልኩህ እ እና እኔን የማግባት ድፍረቱስ ሞራሉስ አለህ ወይስ ደሞ እኔጃ ብቻ ጤነኛ አደለህም እንዴ ምን እያሰብክ ነው አልኩት በጥያቄ አይን እያየሁት ።

ቀና ብሎ አይን አይኔን እያየኝ  ከመቼውም በላይ እርግጠኛ ነኝ በቃ ለኔ ትንሽም ቢሆን ስሜት ካለሽ እሺ በይኝና አሁኑኑ ሰርግ ደግሰን እንጋባለን አለኝ::
አሁን እጆችሽን ስጭኝ ቀለበቱን ላድርግልሽ አለኝ ::

ልዑሌ እውነት ለመናገር ፕራንክ እያደረከኝ ድሮስ ከመጋባትሽ በፊት ማን ከወንድጋ ተኚ አለሽ ብለህ ልትቀልድብኝ እየመሰለኝ ነው ሌላውን ተወው ግንኮ እኔ የድሀ ልጅ ነኝ እእ ለክብርህና ላንተ አልመጥንም አልኩት
ልዑሌ ግን እኔ እነሱ ነገሮች ለኔ ግድ እንደሌላቸው ካንዴም ሁለቴ በደንብ ነግሬሻለሁ ሰላም ክርስቶስ ምስክሬ ነው ከልቤ ነው ላግባሽ ያልኩሽ።
ቆይ ሌላው ቢቀር ለ አንድ ቀን እንኳን እናትሽ ተደስታ ማየት አትፈልጊም ሰላም ግዴለሽም እሺ ቀይኝ አለኝ።
እጄን ዘረጋሁለት ቀለበቱን አደረገልኝ ትንሽ ጠቦኝ ነበር
ቀለበቱን ካደረገልኝ ቡሀላ ወደ ተንቆጠቆጠው ጠረጼዛችን አመራን ወንበር ስቦ በክብር አስቀመጠኝ ።
ማንም እንዲረብሸን ስለማንፈልግ ስልካችንን እናጥፋ አለኝ አጠፋን ::

🔻ክፍል አስራ ሰባት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀

 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰1️⃣5️⃣

መኪናዋ ወደፊት ትከፋለች እኔም በሀሳብ ተሰድጃለሁ እንባዬ ድንቅን ድቅን ይላል

ደሞ  አልፎ አልፎ ልዑሌ በአይኑ ሰረቅ እያደረገ ያየኛል።  የኔ ፊት ወይ ፍክችአልፈታም  አለ እኔ ለመውረድ ከሚታገለኝ እንባዬጋ ትልቅ ፀብ ውስጥ ገብቻለሁ ።

ፊቴ  እንደዛው እንደተቋጠረ ነበር የሆነ ቤተ መንግስት ይሁን ምን ይሁን አላቅም ብቻ የሆነ በር ላይ ስንደርስ መኪናውን አቁሞ እንድወርድ ጋበዘኝ ወረድኩ።
በጣም ግራ ተጋብቻለሁ
......ምንድነው አልኩት አይኔን  ወደ ልዑሌ አፍጥጬ,.........

ወደ ውስጥ እንግባ የምነግርሽ አለ።
ምናልባትም ትወጂው ይሆናል ወይም ትጠይውም ይሆናል እሱን አብረን እናያለን አለኝ።

ወደ ውስጥ መግባት ጀመርን።

ገና ግቢው ውስጥ ስንገባ ግቢው ለመርገጥ በራሱ ያሳሳል አርጓዴ ነገር የበዛበት ፀጥታ የሰፈነበት በአበቦች የታጀበ ጊቢ ነው።

የሆነ መናፈሻ ቦታ ነው የሚመስለው  የቤቱን አረ ምን የቤቱን የቤተ መንግስቱን ልበል እንጂ☺️ በር እየከፈተ አይን አይኔን ያየኛል በሩን ከፍቶ  ወደ ውስጥ ገባን።

በህይወቴ እንደዚህ አይነት ቤት ውስጥ ገብቼ እንደማላቅ በ10 ጣቴ መፈረም እችላለሁ ድብርቴን  ሁላ የቤቱ ውበትና ግርማ ሞገስ አጠፋው ( እኔ ምላችሁ ግን እንደዚህ አይነት ቤት የሚኖሩ ሰዎችም እኛም ከደሳሳ ጎጇችን ወተን ስንሞት ግን እኩል አፈር ላይ መቀበራችን አይገርማችሁም ። ካነሳሁላችሁ አይቀር በጣም ከሚገርመኝ አንድ ነገር ልንገራችሁ ቆይ ለምንድነው ብዙ ጊዜ ሀብታሞች በጣም ብዙ አይነት በሽታዎች የሚይዟቸው ከዛም ባለፈ በጣም እረጅም እድሜ የሚኖረው ከሀብታምና ከደሀ ማነው እእእ)
  
      ልዑሌ ከፊት ለፊቴ ቆመና አይንሽን ላስረው ነው አለኝ።
በፈገግታ እያየኝ (ይሄ ልጅ ግን ፈገግታው ህይወት ይዘራል ሰው እንዴት ካለምንም እንከን ይፈጠራል አልኩኝ በውስጤ)     እንዴ ለምን እኔ ጨለማ እፈራለሁ አልፈልግም አልኩት ተኮሳትሬ ::
አረ ሰላም ምን ሆነሻል ቢያንስ የመሰነባበቻችን ቀን እንኳን ብታምኚኝ ምናለበት ቀስ አድርጌ ነው የማስርሽ ብሎ አይኔን በስሱ አስሮኝ ወደ ደረጃ ይዞኝ ወጣ  በሱ መሪነት ደረጃውን ወጥተን ስንጨርስ   ግለጪ ስልሽ ብቻ ነው የምትገልጪው አለኝና ድምፁን አጠፋብኝ በጣም ነው ግራ የተጋባሁት ልዑሌ አልኩ ድምፄን ቀዝቀዝ አድርጌ   ተረጋጊ እስኪ አለኝ እየሳቀ ወዲያው የዘፈን እንጉርጉሮ ሰማሁ ይሄ ምን ያጃጅለዋል የምን ዘፈን ነው ቆይ .........

አይንሽን ግለጪ አለኝ ለመግለጥ ጓግቼ ነበር  ምንም ነገር ሊያደርግ ይችላል የሚል ግምት የለኝም ።
ምን ጉድ ሊያሳየኝ ነው ብዬ ግን ፈራሁ።

መቼስ እንደተጨፈንኩ አልቀር ብዬ አይኔን ቀስ አድርጌ በስሱ የታሰረው ጨርቅ ፈታሁት አይኔን ስገልጥ የሆነ አለም ውስጥ የገባሁ ነው የመሰለኝ ፊልም የማይ መስሎኝም ነበር።


🔻ክፍል አስራ ስድስት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 
      ‌‌‌‌‌‌‌        ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰1️⃣4️⃣

ግን ይሄን ሁላ ነገር ያደረኩት አውቄ ፈልጌው አይደለም ::

በዛ በተረገመ ማክቤል በተባለ የሰው አውሬ እንጂ ብቻ ከራሴጋ እየተብሰለሰልኩ  ወደ ክፍሌ ገባሁና ስልኬን ማጣጠፍ ጀመርኩ ።(እኔን የሚገርመኝ ብር ሳይኖረኝ ማረፊያ ሳላመቻች ብቻዬን አይሉት ልጅ ተሸክሜ ወዴት ልሄድ ነው ምዘገጃጀው)

በሀሳብ ጭልጥ ብዬ
ስልኬ ጮኸ ልዑሌ ነበር ስልኩን ሳየው ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ላንሳው አላንሳው እያልኩ ከራሴጋ እየተማከርኩ ስልኩ ዘጋ ።
እንደዛ ምን እንዳስደነገጠኝ ባላውቅም ልብ ምቴ ሁላ ነበር የተዛባው  ። እውነት ለመናገር መደወሉ አስገርሞኝም ጭምር ነው አይኔን እንኳን ሳያየኝ ፊቱን አዙሮ የሄደው ሰውዬ ዛሬ ምን አስደወለው ።

ወዲያው ደግሞ ደወለ ያለማንገራገር አነሳሁት ።
በተቆራረጠም በተኮሳተረም ድምፅ ሄሎ አልኩት...

ሰላሜ እንዴት ነሽ ምነው text አትመልሽም ስልክም አታነሺም ምን ሆነሽ ነው አለኝ ::
ድምፄ እየተቆራረጠ አይ አላየሁትም ነበር textun....

ስልኩን ግን ላነሳው ስል ነው የዘጋው አልኩት እሺ አሁን የት ነሽ መቼስ ከቤት አልወጣሽም አቃለሁ በቃ textun እይውና መልሰሽ ደውይልኝ እጠብቅሻለሁ... ብሎ ስልኩን ዘጋው ::

  textun ከፍቼ ሳየው ሁለት ነው የላከው

የመጀመሪያው ውዴ ትናንት ስለተፈጠረው ነገር በጣም ይቅርታ ከራሴጋ አልነበርኩም በጣም ላወራሽ የምፈልገው ነገር አለኝ አስቸኳይ ነው ይላል ......

ሁለተኛው ደግሞ ምነው ዝም አልሽ አኩርፈሺኛል እንዴ ይቅርታ ሰላም ግን ከመሄድሽ በፊት አንዴ ብቻ ላግኝሽ ይላል.. ..ልክ አንብቤ ስጨርስ ደወልኩለት አነሳው
ለምን እንደፈለከኝ በስልክ ንገረኝ በአካል መገናኘት አልችልም ልሄድ ነው አልኩት:: እሺ ትሄጃለሽ ግን በአካል አጊቼሽ ነው ላናግርሽ የምፈልገው እራስሽ አልነበርሽ እንዴ እንደምታፈቅሪኝና እንደምትወጂኝ የነገርሽኝ እና ምትወጂውን ሰው አትሰናበቺውም እንዴ ሲለኝ አላስቻለኝም  አይኑን አይቼው ልምጣ ብዬ አሰብኩ

እሺ የት እንገናኝ ስለው አስፋልቱጋ እየጠበኩሽ ነው ውጪ አለኝና ስልኩ ተዘጋ::
እንዴ እንዴት መጣ ግራ ገባኝ ብቻ እያጣጠፍኩ የነበረውን ልብስ ጥዬ ልወጣ ስል የለበስኩትን ልብስ ሳየው አስጠላኝ ድጋሜ  ወደ ክፍሌ ገበቼ ሆዴን በደንብ የማያሳይ ግን የሚያምር ልብስ ፍለጋ ልብሶቼን ዝብርቅርቃቸውን አወጣኋቸው በስተመጨረሻም አይኔ ያረፈበትን ቀሚስ ለብሼ :ከንፈሬን በስሱ ተቀብቼ :ወጣሁ ::

ልክ ስወጣ ያ ማክቤል ተብዬው ከቤታቺን ፊት ለፊት ቁጭ ብሏል ሳየው ደሜ ነው የፈላው ይሄን ሰሞን ደሞ እየተከታተለኝ ነው ወይስ አጋጣሚ ነው ... ግራ ገባኝ

ግን ምንም እንዳልመሰለኝ ሆኜ ገልመጥ  አድርጌው አለፍኩ

ልክ አስፋልቱጋ  ስደርስ ልዑሌ ከእስከዛሬው በተለየ በጣም አምሮበት ነበር ።
ፊቱም ደስ ያለው ይመስላል ያንን የዘፈዘፍኩትን ፊቴን ይዤ ከፊት ለፊቱ አንገቴን ደፍቼ  ቆምኩ ።
አረ  ለቦጭሽን ሰብስቢው ብሎ ጉንጬን ነካ ነካ አደረገኝና አንገቴ ስር ሳመኝ።
መኪናውንም ከፍቶ እንድገባ ጋበዘኝ ገባሁ ።
እሱም ገብቶ መኪናው ሲንቀሳቀስ ማክቤል ተብዬው ዛሬም ከኋላዬ ተከትሎኝ ነበር ልዑሌ አይቶት እንዳላየ ዝም አለ እኔም ዝም አልኩ ።
ወዴት ነው ምንሄደው ቸኩያለሁ አልኩት ይቅርታ ትንሽ ደቀቂ ብቻ ስጭኝ ባይሆን ለሱ ካሳ እስከምትሄጅበት እሸኝሻለሁ አለኝ

🔻ክፍል አስራ አምስት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌        ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰1️⃣3️⃣

እዛው ተቀምጬ ጮኩኝ አለቀስኩኝ ግን ማንም አድማጭ አልነበረም ::

አይ ልዑሌ ቢያንስ መጥፎ ሴት ነሽ ለምን ተልከሰከሽ እንኳን ሳይለኝ ፊቱን አዙሮብኝ ሄደ።
ተግባሩ ከቃላቱ በላይ ነገረኝ ።
ልክ ካጠገቤ ተነስቶ ሲሄድ ከበፊቱ የበለጠ ልቤ ተሰበረ ሆዴን ባር ባር አለኝ ።።

ምናለ ወደቤቴ ስሄድ መኪና ገጭቶ በደፋኝ ብዬ ተመኘሁ ::

በቃ ቀጥታ ወደ ቤቴ ሄጄ ትንሽ ልብስl በፌስታል ነገር ይዤ ልውጣ ብይ አስፋልት ለአስፋልት እንደሰካራም እየተገላጀጅኩ ትንሽ ተራመድኩና ታክሲ ውስጥ ገብቼ ወደ ሰፈሬ ሔድኩ ::.

እቤት ስገባ ማዘር እቤት መጥታ ቡና እያፈላች አገኘኋት
እንዴ ማሚ እንዴት ቶሎ መጣሽ ዛሬ ስላት አይ ትንሽ ጨጓራዬን አሞኝ አስፈቅጄ መጥቼ ነው ያው ታውቂ የለ ማታ ያቺን ምስር ቀመሰች ብሎ እንዲሁ አዋለኝኮ::
ሲብስብኝ አስፈቅጄ መጣሁ አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው እንዲህ ግርጥት ያልሺው ደሞ አልቅሰሻል እንዴ ብላ ከተቀመጠችበት ወደኔ መጣችና እጄን ጎተት አድርጋ ሶፋ ላይ አስቀመጠችኝ::

ልጄ ከመቼ ጀምሮ ነው ከኔ መደበቅ የጀመርሽው እውነቱን ንገሪኝ የሆንሽውን አለችኝ::

ማም ምንም የለም ባለፈው ነግሬሽ የለ በሱ ምክንያት ነው በቃ ሌላ ምንም የለም ማም በጣም እንደተጨነቀች ከፊቷ ላ ማየት ችያለሁ ::

ወይ ለምን ሄደሽ ሁሉንም ፍርጥርጥ አድርገሽ አትነግሪውም ከዛ ቡሀላ አንቺም አትጎጂም ቁርጥሽን ታውቂያለሽ ልጄ እንዲህ ሆነሽ ከማይ ሞቴን እመርጣለሁ ለ1 ደቂቃ  ፊትሽ እንዲጠቁር አልፈልግም ታዉቂያለሽ እዚህ ምድር ላይ ለመኖሬ ምክንያቴ እናንተ ልጆቼ ናችሁ አሁን አንቺ ደርሰሻል ልጄ ወግ ማዕረግ እንድታሳይኝ እፈልጋለሁ ::

ከሰው እኩል እንድታደርጊኝ እፈልጋለሁ አለቺኝ እናቴ እንዲህ ስታወራ አሳዘነችኝ የምር ምናለበት የምትፈልገውን አድርጌ ባስደስታት ብዬ ተመኘሁ ::

ግን አልችልም ማክቤልን የበለጠ እንድጠላው አደረገኝ እርግጠኛ ሆኜ መናገር የምችለው ነገር ቢኖር እንደሱ የጠላሁት ሰው እዚህ ምድር ላይ እንደሌለ ነው::

ከማምጋ ትንሽ ካወራን ቡሀላ ወደ ክፍሌ ገባሁ እንደለመድኩት አልጋዬ ላይ ተዘርሬ ማሰብ ጀመርኩ ::
ልዑሌ ቢያንስ አንድ ቃል እንኳን አትሂጂ እንዲህ አታድርጊ ሳይለኝ ጥሎኝ መሄድ ለኔ ጭራሽ ምንም አይነት ስሜት እንደሌለው ነው ያረጋገጠልኝ::

በግማሹ ደስ ብሎኛል ቢያንስ ልዑሌ እኔን ስላጣ ምንም አይጎዳም አሁን የሚያስጨንቀኝ ሳቋን መልኳን ሞራሏን ደም ግባቷን ለኔ ሰጥታ እሷ የተጎሳቆለችውን እናቴን አንድ ነገር እንኳን ሳላደርግላት ሳልጠቅማት ጥያት መሄዴን ሳስብ ውስጤ ይቆስላል ::

ግን በቃ ቢያንስ ከወለድኩ ቡሀላ ሁሉንም ብነግራት ይሻለኛል ብዬ አሰብኩ ከወለድኩ ቡሀላ ተመልሼ እመጣለሁ እያልኩ ከራሴጋ ካወራሁ ቡሀላ ለናቴ ደብዳቤ ልፅፍላት አስቤ ወረቀትና እስክሪብቶ አዘጋጀሁ  ግን ምን ብዬ ልጀምር ግራ ገባኝ ግን መፃፍ እንዳለብኝ ደሞ አቃለሁ መጀመሪያ በጣም እንደምወዳት ፃፍኩላ ሲቀጥል የሆነ ቀን በጣም እንደማኮራት ጥያት የሄድኩት ግድ ሆኖብኝ እሷን አንገቷን ላለማስደፋት ብዬ እንደሆነ ፃፍኩላት ከዛ በላይ ግን መቀጠል አቃተኝ ትራሴ ውስጥ  አስቀምጬው ተኛሁ::

በጠዋት ተነስቼ ከዚህ ሰፈር እንደምጠፋ ወስኜ ጨርሻለሁ ::

ጠዋት ስነሳ ሰአቱ ለምሳ ሰዐት እየተቃረበ ነበር  እናቴም የሰሞኑን ሁኔታ ካየች ቡሀላ ጠዋት እኔ ካልተነሳሁ እሷ መቀስቀስ አቁማለች።

ምናለበት ማታ አላርም ብሞላ ብዬ እየተነጫነጭኩ ተነስቼ ልብሶቼን ማስተካከል ጀመርኩ ቤት ውስጥ ማንም የለም እህቴም  ትምህርት ቤት ሄዳለች ::

ብቻየን መሆኔ ለኔ ጥሩ እንደሆነ እያሰብኩ::............. ነፃነት ይሰጡኛል ብዬ የማስባቸውን ልብሶች ከተትኩ ከድሮም ቀጫጫ አለመሆኔ እርግዝናዬ ጭራሽ እንዳያስታውቅ አድርጎታል:: ልብሴን ከታትቼ ጨረስኩ ደብዳቤውን ፊት ለፊት ላይ በደንብ እንደሚታይ ካረጋገጥኩ ቡሀላ :
ቤቱን ዞር ዞር ብዬ ለመሰናበት ከክፍሌ ወጣሁ ምናልባት ተመልሼ እዚህ ቤት ላልመለስ : እችላለሁ ምናልባት እራሴን ላጠፋ እችላለሁ :

ብቻ የምወስነው ከዚህ ቤትና ከዚህ ሰፈር ርቄ ከሄድኩ ቡሀላ ነው ::

      ለመጨረሻ ጊዜ የናቴን ፈገግታ ለማየት ፈለኩና ቤቱን አፀዳድቼ ቡናውን አቀራርቤ የሚገርም ምሳ ሰርቼ ጠበቋት ምሳ ልትበላ ቤት ስትመጣ ቤቱ ሁላ ፏ ብሎ ስታገኘው በጣም ደስ አላት ዛሬ ምን ተገኘ አለች እየሳቀች አረ እማዬ አንቺን ለማስደሰት ነዋ እኔኮ በጣም ነው እምወድሽ አልኳት የሰራሁትን ምሳ እያቀርብኩ እኔምኮ እወድሻለሁ ልጄ ብላ ግንባሬን ሳም አደረገችኝ።።

ከናቴጋ እየተጨዋወትን ወደ ስራ የመመለሻ ሰአቷ ደረሰና ተሰናብታኝ ሄደች።
እቃውን አጣጥቤ አነሳስቼ ስጨርስ ሰዐት ሳይ 8 ሰአት አልፏል ::

ብቻዬን ቤት ውስጥ ድምፅ እያወጣሁ አለቅሳለሁ ማንም አይዞሽ ያልፋል የሚለኝ የለም ::

አይገርምም እንደዛ ምትሳሳልኝ እናቴ እንኳን ይሄን ጭንቀቴን ልትካፈለኝ አትችልም ( ግርም ከሚለኝ ነገር አንዱ ለልጅ ከወላጆች በላይ የሚቀርብ ሰው ባይኖርም ግን ስናድግ አብዛኛውን ጭንቀታችንን አያውቁም ፍቅር ስንጀምር : ስናቆም : ስንጎዳ : ስለነገ ስንጨነቅ : ያፈቀርነው ድንገት ጎድቶን ትልቅ ህመም ውስጥ ገብተን  ግን ሁሌም ለቤተሰብ እንደጤነኛ ልጆች ነን )
የኔ እናት እንኳን እስከአሁን ድረስ ሚስጥረኛዬ ገመና ሸፋኜ ነበረች
እኔ ግን ገመናዋን ልሸፍንላት የምትፈልጋትን አይነት ልጅ ልሆንላት አልቻልኩ እሷ ሰራተኛ እኔ የቤት እመቤት ሆኜ አረፍነው እሱም ሳይበቃ ሌላ ሸክም ልጨምርባት አልችልም


🔻ክፍል አስራ አራት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰1️⃣2️⃣

ቦታውጋ ስንደርስ ከመኪናው እንድወርድ ጋበዘኝና ወረድኩ:
የባለፈው እራሱ ቦታ ላይ ሄደን ተቀመጥን አቀማመጣችን ግን የዛሬው ዝም ብሎ ፊት ለፊት ነበር::
ልዑሌ እንዲህ ግን ስትሆኚ ታስጠያለሽ እሺ አያምርብሽም አለኝ ለማሳቅ መሞከሩ ነው ግን አልተሳካም
የበለጠ ልቤ እየመታ ነው ልቤ የሆነ በቃ ወጥታ ልትበር ያህል እያስጨነቀችኝ ነበር  አይን አይኔን እያየ እእ ንገሪኛ አለኝ።
ለመስማት እንደጓጓ ግልፅ ነው በሱ ቤት ጥሩ ዜና የምነግረው መስሎታል በመጀመሪያ የሆነ ነገር ልነግርህ እፈልጋለሁ በጣም እድለኛና ልዩ ሰው እንደሆንክ እንድታውቅ እፈልጋለሁ።

ፈጣሪ እንዳንተ ሁሉን ነገር አሟልቶ የሰጠው ሰው የለም .......አቋረጠኝ ተሳስተሻል ፈጣሪ አንድ በጣም የምፈልገውን ነገር ነጥቆኛል እሱን የሆነ ቀን ታቂው ይሆናል አለኝ::

ምንድነው ንገረኝ ድጋሜ ላንገናኝ እንችላለን ስለው በጣም ደነገጠ ማለት አለኝ ከመቀመጫው እየተስተካከለ መጀመሪያ አንተ ንገረኝ አልኩት የኔንማ ታቂዋለሽ ያው ፍቅር ነዋ እናትና አባቴ ሞተዋል 2 ወንድሞች አሉኝ::

እነሱም ስለገንዘብ እንጂ ሌላ ነገር ግድ አይሰጣቸውም::
በጣም ብቸኝነት ይሰማኛል  ከስራ ውዬ ስገባ ከገንዘቤና ከመኪናዬጋ አላወራም  በዛን ሰአት እቤት ቁጭ ብላ ውሎዬ እንዴት እንደነበር ምን እንዳስደሰተኝ : ምን እንዳስከፋኝ ምትጠይቀኝ እናት ብትኖረኝ ግን ደስ ይለኝ ነበር።

ሲለኝ በጣም አሳዘነኝ የሚከፈለውን መስዋትነት ከፍዬ አብሬው ብቆይ ደስ ይለኝ ነበር ግን ከአቅሜ በላይ ነው።

ገና ላወራ ስጀምር እንባዬ ቀደመኝ ልዑሌ ደንግጦ  ወደ እራሱ አስጠግቶ እቅፍ አደረገኝና ከኪሱ ሶፍት አውጥቶ እንባዬን እየጠረገ ምን ሆነሽ ነው ሰላሚና ንገሪኝ  እንጂ በፈጣሪ ስም በጣም እያስጨነቅሽኝ ነው ።
እንዴ ምንድነው እንዲህ መሆን  አለኝ።

እኔም ታሪኩን እንዲህ ብዬ ጀመርኩለት ከማክቤልጋ ከመለያየታችን በፊት አብረን አድረን ነበር ባሌ የሚሆን መስሎኝ ነበር የሚያፈቅረኝ መስሎኝ ነበር እሱ ግን አንድ በቂ ምክንያት እንኳን ሳይሰጠኝ እንደቆሻሻ አውጥቶ ጣለኝ::

      እና እሱን አሁን ምናመጣው ሰላም?? አለኝ ::

እንዳታቋርጠኝ አስጨርሰኝ አልኩት እየተቆጣሁ ::
አሺ በቃ አላቋርጥሽም ቀጥይ ብሎ ዝም አለ ::
ምን  እንደተፈጠረ ሳላውቅ አልፈልግሽም አለኝ ።
ማለቴ አንተን የተዋወኩ ሰሞን ከዛም አንተጋ ደውዬ ላግኝህ አልኩህ አገኘሁህ አወራን ተግባባን በህይወቴ ውስጥ አንተ ስትመጣ ሁሉም ነገር ያበቃ መስሎኝ ነበር ድጋሜ ስለ ማክቤል ላለመሳብ ወስኜ ነበር ከውስጤ አውጥቼ እንደቆሻሻ ጥዬው ነበር ።
በሱ ቦታ አንተን ተክቼ በውስጤ አንግሼህ ነበር የምር ልዑሌ ወድጄህም አፍቅሬህም ነበር። በዚህ አጭር ጊዜ እንዴት እሱን እረስቸሽ እኔን አፈቀርሽኝ ልትለኝ ትችላለህi ግን እኔጃ አላቅም እኔ ላንተ እመጥንሀለሁ ብዬ አደለም ግን በቃ እንዲሁ የምትለይ ሰው ነህ::
ግን በቃ ፈጣሪ ለሰራሁት ሀጥያት ሊቀጣኝ ፈልጎ ነው መሰለኝ ይሄን ዱብዳ አወረደብኝ።
እኮ ዱብዳው ምንድነው ንገሪኛ ?? አለ

እሺ እኔ ባለፈው ሆዴን በጣም እያመመኝ ሲያስቸግረኝ ወደ hospital ሄድኩ ከዛ ምርመራ ሳደርግ  እርጉዝ መሆኔን ነገሩኝ አቃለሁ በጣም ያሳፍራል ሳላገኝህ ዝም ብዬ ለሰጠፋ ነበር ግን ልቤ እንቢ ብሎኝ ነው (እንባዬ ይፈሳል)

ልዑሌ የጠበኩትን ያህል አልደነገጠም 

 እናም ላስወርድ ስሄድ   ማስወረድ አትችይም አሉኝ በቃ ልዑሌ ምን አይነት የማረባ ሰው እንደሆንኩ የገባኝ አሁን ነው ከዚህ ቡሀላ ድጋሜ ላታየኝ ትችላለህ::.
ከሰው በታች ሆና ያሳደገችኝን እናቴን ማሳፈር አልፈልግም ።በሰፈሩ ሰው መጠቋቆሚያ አላደርጋትም ይሄን ከማደርግ ሞቴን እመርጣለሁ ...........እኔ እያወራሁ ልዑሌ ቃል ሳይናገር ከመቀመጫው ተነስቶ ወደ መኪናው አመራ ::
ደንግጬ እኔም ቆምኩ ዞር ብሎ እንኳን ሳያየኝ መኪናውን አስነስቶ እዛው ጥሎኝ ሄደ ...

🔻ክፍል አስራ ሶስት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌       ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰1️⃣1️⃣

በቃ እኔ ማቀው ቤት አለ እዛ ሄደ ምሳ እንብላ ።
ስንጨርስ ባለፈው የሄድንበት ቦታ እንሄዳለን አለ ።
የትኛው ቦታ አልኩት ባለፈው የምጠይቅህ ጥያቄ አለ ብለሽኝ የሄድንበት ቦታ አለኝ እሺ በቃ እንሂድ ተስማምቻለሁ ብዬው ወደ ትካዚዬ ገባሁ ከሀሳቤ ያነቃኝ የልዑል ድምፅ ነበር በቃ ደርሰናል ውረጂ መኪናዬን አቁሜ መጣሁ አለኝ ።
እኔም ወርጄ ቆምኩ መኪናውን አቁሞ መጣ ወደ ውስጥ ገብተን ተቀመጥን ምግብ አዘዝን እኔ ግን ምግቡ ምንም ሊበላልኝ አልቻለም እሱ እንዳይደብረው ብዬ ነው ያዘዝኩት እሱ ሲበላ አይን አይኑን አየዋለሁ ቀና ሲል አጎነብሳለሁ ሁኔታዬ ለሱም ግራ እንዳጋባው ከፊቱ ላይ ያስታውቃል አስሬ ብይ እንጂ ብይ እንጂ ይለኛል አይ በቃኝ ምሳ በልቼ ስጨርስ ነው የደወልከው አሁንም አንተ እንዳይደብርህ ነው ያዘዝኩት እንጂ ልበላ አይደለም አልኩት አረ የሆነ ነገርማ ሆነሻል በቃ እኔም በቃኝ አስደበርሽኝኮ አለኝ ።

እሺ በቃ እንውጣ ግን የኔን ምግብኮ አልነካሁትም ለምን ቴካዌ አስደርገን ጎዳና ላይ ለተኛ አንድ ሰው አንሰጠውም ችግር የለውማ ስለው አረ የምን ችግር ሌላም አስጨምረን እናስደርግና ስናልፍ ላገኘነው ጎዳና ተዳዳሪ እንሰጠዋለን ብሎ አስተናጋጇን ጠራና ነገራት ትንሽ ቆይታ አስተናጋጇ በጥቁር ፌስታል ይዛ መጥታ ሰጠችው ሂሳቡን ከፍሎ ወጣን።

እየሄድን እያለ ተደርድረው የተቀመጡ ጎዳና ተዳዳሪዎች አይተን መኪናውን አቁሞ ወረድን።
ምግቡን የያዝኩት እኔ ነበርኩ ከተቀመጡት ውስጥ አንድ ህፃን ልጅ ጠራሁና ምግቡን ሰጠሁት ኪሴ የነበረውን 50 ብርም ጨምሬ ሰጠሁት።

ልጁ በጣም ነበር ደስ ያለው ልክ ሎተሪ እንደደረሰው ነገር እየሮጠ ተሰብስበው ወደ ተቀመጡት ሰዎች ሄደ ፌስታሉ ውስጥ ምግብ እንዳለ እርግጠኞች ነበሩ መሰለኝ ገና ልጁ ወደነሱ ሲመጣ ነበር እጃቸውን የሰበሰቡት በቃ ሁሉም እየተሳሳቁ እየተሻሙ መብላት ጀመሩ ልዑሌ ምስጥ ብሎ እያያቸው ነበር

ሳየው አረ ሰውዬ ነቃ በል ወይ ሂድና ተቀላቀላቸው ብዬ ወደ መኪናው ገባሁ እሱም ተከትሎኝ ገባና መንዳት ጀመረ።

ታቃለህ ልጁ ግን በጣም ነው ያሳዘነኝ ይሄኔ የሱ እኩዮች ትምህርት ቤት ገብተው እየተማሩ  ነው ያሻቸውን ለብሰው ያሻቸውን በልተው እሱ ግን ገና በጨቅላ እድሜው የሰው ፊት ይገርፈዋል
የሰው እጅ ይጠብቃል። አንዳንዶች በሱ እድሜ ምን አነሳችሁ ምን ጎደላችሁ አፈር እንዳይነካችሁ ተብለው ያድጋሉ አንዳንዶች ደሞ እንደሱ ገና በልጅነታቸው የችግር ጅራፍ ይገርፋቸዋል
አሁን ይሄ ልጅ ምንን ተስፋ አድርጎ ነው የሚኖረው አልኩት።
እንባዬ እየተናነቀኝ ልዑሌ ፈጠን ብሎ ነገን  ተስፋ አድርጎ ነው የሚኖረው
እሱ ፈጣሪ ያደለው ጤና አለው ሰው በተለያየ በሽታ  ነገ እንደሚሞት እያወቀ ይኖር የለ እንዴ።
የልጁን ህይወት ደሞ ብሩህ ማድረግ የምንችለው እኛ ነን ለምሳሌ አንቺ ለምን ብር ሰጠሽው ለሱ ብር መስጠት ማለት ልጁ የበለጠ እየጎዳሽው ነው ይሄ ልጅ በእርግጠኝነት የሆነ ሱስ አለበት እሱ እንኳን ባይኖርበት ጓደኞቹ ይኖርባቸዋል ስለዚህ ይሄን ብር ለሱሳቸው ማስታገሻ አዋሉት ማለት ነው።
ነገም መቶ ሌላው ሰው ብር ሲሰጣቸው እሱንም ለሱስ ያውሉታል ስለዚህ ሱሳቸውን እያስፋፉ ይሄዳሉ ማለት ነው።

ይሄን ብር ከምሰጫቸው ይልቅ የ5 ብር ዳቦ ገስተሽ ብሰጫቸው ግን ከርሀብ ነው ምታስታግሻቸው ገባሽ አለኝ ።
ወደኔ እያየ ሲያወራ በጣም ስሜታዊ ሆኖ ነበር ንግግሩ ደሞ ምንም ሀሰት የለውም እስከዛሬ ግን አስተውዬው አላቅም ነበር።

ለጎዳና ተዳዳሪዎች ብር ስሰጣቸው ትልቅ ውለታ የዋልኩላቸው ይመስለኝ ነበር ለካ እየጎዳኋቸው ነበር ስለው አይ ከዚህ ቡሀላም ካወቅሽ አንድ ነገር ነው በይ እየደረስን ነው ወሬውን ለመናገር ተዘጋጂ አለኝ እኔ ግን በውስጤ አልንገረው እንዴ! ቢያንስ ለትንሽ ቀን አብሬው ልቆይ እንዴ? እላለሁ አንዱ ልቤ ደሞ ወደፊት ነገሩ እየከፋ እንደሚሄድና ካሁኑ ንገሪውና  ወደ አንዱ ቤተክርስቲያን ትጠፊያለሽ ይለኛል ብዙ አሰብኩበት ግን ለልዑሌ መናገር ግድ ሆኖ አገኘሁት በቃ ሁሉንም ነግሬው ካሁን ቡሀላ ባላገኘው ይሻለኛል.......


🔻ክፍል አስራ ሁለት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማዕበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰1️⃣0️⃣

ከሆስፒታል ወጣሁ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ምን እንደማስብ አላውቅም ።

ብቻ መንገድ ላይ ግራ ተጋብቼ ስጓዝ ልዑሌ ደወለ ገና ስልኬ ላይ ስልኩ ሲጠራ እደነግጣለሁ ድምፁን ስሰማ የውስጤ ጭንቀት ሁላ ነው ሚጠፋው: ስልኩን ሳየው ፈገግ እንዳልኩ እንኳን ሳይታወቀኝ ፈገግ እላለሁ  :

ስልኩን  አንስቼ ሄሎ አልኩት እንዴት ነሽ የኔ ቀውስ ምነው ጠፋሽ ለመናፈቅ ባልሆነ አለኝ እየሳቀ ::
ወይ መናፈቅ እያልኩ በውስጤ ለመረሳት ነው እንጂ አልኩት አይ አንቺማ እንዴት ትረሻለሽ እሺ ዛሬስ አንገናኝም እንዴ ? ሲለኝ በጣም ነው የደነገጥኩት ምክንያቱም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ እሱን ማየት አልችልም እንዴት ብዬ ነው አይኑን የማየው በሌላ በኩል ደግሞ ቢያንስ አይኑን ባየው ሰላም እንደሚሰማኝም አቃለሁ እሺ በቃ ከፈለክ አሁን ከፈለክ ማታ ካፌ ሳልጨርሰው አይ አሁን ይሻላል እስካሁን ምሳ አልበላሁም  እሺ የት እንገናኝ አለኝ ::
አንተ ደስ ያለህ ቦታ በቃ ሰፈር ጠብቂኝ እና መጥቼ እወስድሻለሁ ብሎኝ ስልኩን ዘጋው::
የተለመደችው ቦታዬጋ ሄጄ ቁጭ አልኩኝ መጮህ ማልቀስ ተመኘሁ ግን አቅም አነሰኝ ።።
እናቴ እኔን በድህነት አሳደገችኝ እኔ ደሞ ልጄን በድህነት ላሳድገው ነው ?እንደዛ የለፋችልኝ እናቴ ለስራዋ ምከፍላት ይሄንን ነው 😢 እዛ ትንሽ  ከተቀመጥኩ ማበዴ ስለማይቀር ተነስቼ  እስከ አስፋልቱ በእግሬ መራመድ ጀመርኩ።

ትንሽ እንደተራመድኩ ማክቤል ከሆነች ልጅጋ ተቃቅፈው እየተሟዘዙ ከፊት ለፊቴ መጡ ሳየው ደሜ ነው የፈላው ሄጄ ባንቀው ደስ ይለኝ ነበር ።
ልጅቷ የባለፈዋ ልጅ መስላኝ ነበር ግን አይደለችም ሌላ ናት ልክ ሲያየኝ  አንዴ ይስማታል አንዴ ያቅፋታል ብቻ የሚያደርጋትን ነበር ያሳጣው እኔ አንገቴን ደፍቼ ወደፊቴ መራመዱን ተያያዝኩት
አነሱም እኔን እየተከተሉ በሚመስል መልኩ ፍጥነታቸውን ጨምረው ተራመዱ  አጠገቤ ሲደርስ ሰላም ነው ሰላሚና አለኝ እያገጠጠና እያፌዘ መልስ ሳልሰጠው ወደፊቴ ሄድኩ።
ትንሽ እንደተራመድኩ ልዑሌ ደውሎ እንደደረሰና እየጠበቀኝ እንደሆነ ነገረኝ  ቶሎ ቶሎ ወደፊት መራመድ ጀመርኩ ልክ አስፋልቱጋ ስደርስ ልዑሌ መኪናውን አቁሞ ከመኪናው ወርዶ እየጠበቀኝ ነበር ሲያየኝ ፈገግ አለና ወደኔ መቶ አቀፈኝ ሲያቅፈኝ የሚነዝረኝ ነገር ነው ማይገባኝ ኤሌትሪክ ይዞ የሚዞር ይመስል።

እውነት ለመናገር ስላየሁት በጣም ነው ደስ ያለኝ ግን ፊቴ አሁንም እንደተዘፈዘፈ ነው እጄን ይዞኝ ወደ መኪናው ሊያስገባኝ እያለ    የድሮ ፍቅረኛሽን ቦዲይ ጋርድነት ቀጠርሽው እንዴ አለኝ እየሳቀ
ማለት አልኩት ግራ ገብቶኝ እና ለምንድነው ከኋላ ከኋላሽ የሚከተልሽ አለኝ ዞር ስል አቶ ማክቤል 2 እጁን ኪሱ ከቶ ከኋላዬ እየተከተለኝ ነበር እንዴ ጉድ ፈላ ልጅቷን ምን ውስጥ ከተታት አሁን አብራው አልነበረች እንዴ ለራሴም ጥያቄ ፈጠረብኝ ቢሆንም  ከልቤ ነበር የሳኩት ልዑሌ የመኪናውን በር ከፍቶልኝ በክብር ካስገባኝ ቡሀላ ወደ መኪናው ገባ።

ማክቤል ቆሞ እያየኝ ነበር በውስጤ እሰይ ቅጥል በል እያልኩኝ እየሳኩ ሳየው ነበር መኪናው መቀሳቀስ ሲጀምር ማክቤልም ተንቀሳቀሰ የትን የምንሄደው አልኩትን  ልዑሌን በቀዘቀዘ ድምፅ የት መሄድ ትፈልጊያለሽ ደስ ያለሺን ቦታ ምረጪ አለ አይ አንተ ደስ ያለህ ቦታ ከቻልክ ብቻችንን የምንሆንበት ቦታ ቢሆን ደስ ይለኛል ምሳ ከበላን ቡሀላ የምነግርህ ነገር አለኝ አስቸኳይ ነው አልኩት ።
እና ለምንድነው ድምፅሽ የቀዘቀዘው ዛሬ የደበረሽ ነገር አለ እንዴ ነገሩስ አስቸኳይ ነው እንዴ በጥያቄ ሲያጣድፈኝ እሱን ስነግርህ ታቀዋለህ መጀመሪያ ምሳውን እንብላ መቼስ በጣም እርቦሀላ ......

🔻ክፍል አስራ አንድ ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌
‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰9️⃣

ምን ማለት ነው ድንገት ተነስቶ ተለያይተናል ማለት እ እኔ ስለሰርጋችሁ ቀን መርዘምና ማጠር ነበር ሳስብ የነበረው እቃቃ ጨዋታ ነበር እንዴ የያዛችሁት እእ ለምንድነው የተለያያችሁት ንገሪኝ????
እማ ደሞ አሁን ስለሱ ማውራት አልፈልግም ስለ አዲሱ ልጅ መስማት ከፈለግሽ ልንገርሽ ካልፈለግሽ ደሞ በቃ ልተኛ አንቺም ሂጂና እረፍት አድርጊ አልኳት ፊቴን እያዞርኩባት 😒😒
አይ ልጄ በቃ ስለማክቤል አልጠይቅሽም ንገሪኝ ስለ አዲሱ ልጅ ።
ለምድነው እንዲህ ምታለቅሽው ለምን ከፋሽ ፍቅር ሲይዝሽ የመጀመሪያሽ አደለምኮ የማክበል ጊዜኮ እንዲህ አልሆንሽም ልጄ አሁን ምን ተፈጥሮ ነው ንገሪኝ ግልፁን ።

እሱማ አዎ እማዬ የማክቤል ጊዜኮ መጀመሪያ የፍቅር ጥያቄ ስላቀረበልኝ የኔ እንደሚሆን አውቄ ነበር ይሄ ግን ስሜቱ ምን እንደሆነ አይገባኝም አንዳንዴ አውቆ የራቀኝ ይመስለኛል በእርግጥ ገና ከተዋወቅን 3 ወር ምናምን ነው ግን በጣም ነው የምወደው አንዳንዴ በጣም ሀብታም ስለሆነ እኔ እንደሱ ሀብታም ስላልሆንኩ እየናቀኝ ይመስለኛል ።
አይኑ ውስጥ የፍቅር ስሜት አያለሁ: ሲያየኝ ደስ እንደሚለው አቃለሁ :
ግን እሱ ምንም እናዳልመሰለው ያስመስላል በቃ ግን ሳስበው አይወደኝም አልኳት እያለቀሰኩ ውስጤ ያለው ስሜትና ከህክምና ማስረጃውጋ ተደማምሮ  እንባዬ ሲፈስ ወደር የለውም ነበር ;::
ቀና ብዬ እናቴን ሳያት ፍጥጥ ብላ እያየችኝ ለምጠይቅሽ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ ስጭኝ አለችኝ እስተያየቷ ያስፈራል::
በጉጉት እየጠበኩ የናቴን አይን አይኗን ሳያት ኮስተር ብላ እውነት ልጁን ሀብቱን መልኩን አይተሽ አይደለም ያፈቀርሽው አለችኝ ::
አረ ማሚ ሙች በሱ አይደለም እኔ ስለሱ ሀብትና ንብረት ምናገባኝ ብለሽ ነው ወደፊት ድንገት ባሌ ቢሆን ከሱና ከፀባዩጋ እንጂ ከገንዘቡጋ አልኖር ማሚ ሁሌ ሲገባ  ሲወጣ ጨቅጫቃ ከሆነ ለኔ የሚገባኝን ፍቅር ካለገሰኝ የሱ ገንዘብ ለኔ ምን ያደርግልኛ እማ እኔ ደሀም ሆነ ሀብታም የማገባው ባል ከቤት ወቶ እስኪመጣ እንዲናፍቀኝ እፈልጋለሁ ።
ሁሌ ደስታ ሳቅ ጨዋታ የነገሰበት ቤተሰብ እንጂ በሀብት የታጠረ ፍቅር የሌሌለው ሰው አልፈልግም  አልኳት ።
ንግግሬ ከልቤ ነበረ ማሚም ደስ ብሏት በቃ ታገሺው ልጁ ያንቺ ነው።
ቢዘገይም አይቀርም ብላ በተስፋ ሞልታኝ መች እንደማስተዋውቃት ጠየቀችኝ እኔም አንድ ቀን ነበረ ምላሼ።

እሺ በቃ እረፊ ብላኝ ከክፍሌ ወጣች እሷ እንደወጣችልኝ የክፍሌን በር ከውስጥ ቆልፌ አልጋ ላይ ተዘረርኩና  ያለችኝን ማሰብ ጀመርኩ ምናለ እውነት በሆነ ብዬ ተመኘሁ።
ግን ደሞ ልዑሌ የኔ እንደማይሆን ከመቼው በላይ አረጋግጫለሁ አረ እንደውም ድጋሜ ሁላ አጠገቡ ላልደርስ ወስኛለሁ እኔ ያን ያህል ጨካኝ መሆን አልፈልግም በተለይ ደግሞ ልዑሌ ላይ ሁሉንም ነገር ልንገረው ወይስ ዝም ብዬ ስልኬን አጠፋፍቼ ልጥፋ አላቅም ብቻ በጣም ግራ ገብቶኛል ምን እንደማረግ ጨቆኛል በዚህ ሰአት ሚስጥሬን የማማክረው ጓደኛ ቢኖረኝ ደስ ይለኝ ነበር ግን መናገር በራሱ ያሳፍራል ውርደት መስሎ ታየኝ በቃ ምሽቱን ሙሉ ሳስብ ሳለቅስ አመሸሁ በዛው እንቅልፍ ጣለኝ ጠዋት ስነሳ ከጠዋቱ 4 ሰአት ሆኗል ።
እናቴ የማታውን ነገር ስላየች ሳትቀሰቅሰኝ ነው ወደስራ የሄደችው ።

ተነስቼ ተጣጥቤ ለባብሼ ቀጥታ ወደ ሆስፒታል ሄድኩኝ ለማስወረድ ፈልጌ ነበር ያው የገመትኩት አልቀረም ማስወረጃ ጊዜው አልፏል (አንዳንዴ በህይወታችን ውስጥ ሳንፈልግ ጭካኔን ሀጥያትን አስተምረውን የሚያልፉ ብዙ ሰዎች አሉ)

በቃ ምን እንደማደርግ ነው የጨነቀኝ ለማንም ሳልናገር ብን ብዬ ልጥፋ እንዴ እላለሁ


🔻ክፍል አስር ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰8️⃣

ብቻዬን ቁጭ ብዬ ማብሰልሰል ጀመርኩ ::
   ማክቤል   ከኔ የበለጠች ቆንጆ ስለያዘ የሆነች ቅናት ብጤ ተሰምታኛለች እኔምኮ ከሱ የበለጠውን ይዣለሁ ብዬ እራሴን ላፅናና ሞከርኩ ግን ልዑሌ የኔ  እንደሆነ እርግጠኛ አልነበርኩም ።።


ትንሽ ቆየሁና ተነስቼ ወደሆስፒታል ሄድኩ ይቅርታ ተራዬ አልፎኛል መሰለኝ ውጤቱ አንቺጋ ስለሆነ ብትነግሪኝ አልኳት ውጤት ለመናገር ስትጣራ የነበረችዋን ዶክተር
ኦኦ አንቺ ነሽ ስምሽ ሲጠራ የጠፋሽው
ነው ግቢ አለችኝ ።
ገባሁ ቁጭ አልኩኝ
መጀመሪያ ብዙ ጥያቄዎችን ጠየቀችኝ ከማንጋ ነው ምትኖሪው ስራ አለሽ ፍቅረኛ አለሽ ወይ የኑሮ ሁኔታሽ እንዴት ነው ብቻ ብዙ ከጠየቀችኝ ከመለስኩላት ቡሀላ ወጤቱን ነገረችኝ .....

የምርመራ ውጤቴን ሳየው እዛው ነበር እራሴን የሳትኩ ስነቃ ዶክተሮቹ ከበው ደህና ነሽ ደህና ነሽ ይሉኛል መልሴን እራሴን ከፍ ዝቅ በማድረግ መልሼላቸው ካላጋ ላይ ወረድኩ እንባዬ ዝም ብሎ ይፈሳል አንዷ ዶክተር ሶፍት ሰታኝ እንድረጋጋ ነገረችኝ መረጋጋት ግን አቃተኝ:: ደና እንደሆንኩኝ ነግሪያቸው
ዝም ብዬ ወደቤቴ ሄድኩ እቤት ታናሽ እህቴ ብቻ ነው ያለችው ስታየኝ ደንግጣ  እሮጣ  መታ አቀፈችኝ ዝም እንድትል  አስጠንቅቂያት ወደ ክፍሌ ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ::

ክፍሌ ተጠቅልዬ ሳስብ ሳለቅስ ስገላበጥ አመሻሽ ደረሶ እናቴ ወደ ቤት መጣች እቤት ስትገባ ከሳሎን ስታጣኝ ወደ ክፍሌ መጣች ብታንኳኳ ብታንኳኳ ዝምታ ነበር መልሴ የበሩ ድብደባና ድምጿ በጣም ሲረብሸኝ ተነስቼ ከፈትኩላት ስታየኝ ደነገጠች ምነው ልጄ ምን ሆንሽብኝ እያለች ፊቴን ስታሳሸኝ እንባዬን መቋቋም አቃተኝ ፊቴን አዙሬ ወደ አልጋዬ ሄድኩ ተከትላኝ ገባችና  አልጋዬ ላይ አረፍ ካለች ቡሀላ ወደሷ ጎትታ  ጉልበቷ ላይ አስተኛችኝ በይ አሁን በርጋታ የሆንሽውን ሁሉ ንገሪኝ አለች ከናቴ ምንም ነገር አልደብቃትም ከልጅነቴ ጀምሮ እንደ ልብ ሚስጥረኛ ጓደኛ ሆና ነው ያሳደገችኝ ሌላው ቀርቶ ትምህርት ቤት እንኳን የፍቅር ደብዳቤ ሲሰጠኝ ከናቴጋ ነበር ከፍቼ ማነበው የሚጠቅመኚንና ማይጠቅመኝን ከሷ የተሻለ የሚያውቅ ሰው አለ ብዬ ስለማላስብ ነው ምንም ነገር ማልደብቃት አሁንም ሁሉንም አፍረጥርጬ ልነግራት ነበር ግን እንደማልችል ገባኝ እናቴ ይሄን ብትሰማ ምን ያህል እንደምታፍር ሳስበው ሰቀጠጠኝ እናቴ በቀላሉ እንደማትፋታኝ ስለገባኝ የሆነ ታሪክ ፈጥሬ ልነግራት እያሰብኩ እያለ ድንገት ልኡል አይምሮዬ ውስጥ ብልጭ አለ ።
እእእ ....ንገሪኛ..
ልጄ አለች በለሆሳስ ድምፅ ጠየቀችኝ ምን መሰለሽ ማም ፍቅር ያዘኝ አልኳት እየተቅለሰለስኩ ::
አላመነቺኝም 💀ፍቅር ስለያዘሽማ እንዲህ አትሆኚም ።ደሞስ ዛሬ ነው እንዴ ፍቅር የያዘሽ እእእ ይሄን ያህል ጊዜ ከማክቤልጋ ስትቆይ ፍቅር እንደያዘሽ ነበር ማቀው እኔ እናትሽ ስታይኝ ህፃን ልጅ ነው እንዴ ምመስልሽ በይ አሁኑኑ እውነቱን ተናገሪ ብትዋሽኝ አውቅብሻለሁ እሺ አፋጠጠችኝ።
  እኔም ድርቅ ብዬ እማዬ ከማክቤልጋ ተለያይተናል ከሌላ ሰው ነው ፍቅር የያዘኝ ....
     ይቀጥላል

🔻ክፍል ዘጠኝ ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰7️⃣

ምክንያቱም እኔ የብር ችግር የለብኝም ይሄንን ጥያቄ ለ1 የኔ ቢጢ ብታቀርቢለት መልሱ ገንዘቡን ይልሻል እኔን ስጠይቂኝ ደሞ ሰውዬውን አልኩሽ ሰው የሌለውን ነገር ነው የሚመኘው እኔ ገንዘብ አለኝ ፍቅር ግን የለኝም ባሁን ሰአት ከገንዘቡ ይልቅ አንድ የልቤን ማማክረው እውነተኛ ሰው ባገኝ ነው ምመርጠው እኔ ሚስት ማግባት ብፈልግ ገንዘቧን አይቼ አይደለም
ማገባት ለምን መሰለሽ በቤት ላይ ቤት በመኪና ላይ መኪና በገንዘብ ላይ ገንዘብ እንጂ ፍቅርን አትሰጠኝም አንዲት ሴትን ሳፈቅራታ ክፍተቴን እንድትሞላልኝ እፈልጋለሁ የኔ ክፍተት ገንዘብ አይደለም የኔ ክፍተት እውነተኛ ፍቅር ነው ገንዘብ ሳላጣ ጤነኛ ሆኖ በሚኖረው ሰው እቀናለሁ :ሁሌ እየሳቀ በሚኖረው እቀናለሁ :የልቡን ሁሉ ዝርግፍ እያደረገ ለልብ ጓደኛው ሲያማክር ሳይ እቀናለሁ: ምክንያቱም አሁን የጠቀስኩልሽ ነገሮች ሁሉ የለኝም እነዚህ ነገሮች ያሏቸው ሰዎች ግን ለነሱ እንደተራ ነገር ናቸው እነሱ በእጃቸው የሌለውን እሩቅ አሻግረው ሲያዩ የተሰጣቸው ነገር ሳያመሰግኑበት  ሳይጠቀሙበት ያልፍበታል ተመለሰልሽ ብሎ ጉንጬን ነካ ነካ እስኪያደርገኝ ድረስ አፌን ከፍቼ ነበር ምሰማው
አንዳንድ ጥያቅዎችን ተፈጥረውብኛል ግን ዝም አልኩኝ ።
ልኡሌ አነጋገሩ ውስጤ ነበር የገባው እውነት ፈልጎ ያጣውን ክፍተቱን እኔ  ብሞላለት ብዬ ተመኘሁ ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ እሱን ለማስደሰት ለራሴ ቃል ገባሁ  ።
ሳየው ሁሉ ነገሩ ነው የሚያሳሳኝ ከንፈሩ አይኑ ብቻ አላቅም ወደሱ የሚጎትተኝ ብዙ ነገር አለ በጭራሽ መቋቋም የማልችለው ።

አንዳንዴ በጣም ያመኛል ምግብ እራሱ አይረጋልኝም በልቼው ወዲያው ይወጣል ያጥወለውለኛል ብቻ ሀኪም ቤት ለመሄድ እነሳና ምን እንዳስቀረኝ ሳላቅ እቀራለሁ። ዛሬ ግን በጣም ሲብስብኝ ሄድኩ ምርመራ አድርጌ ጨርሼ ልወጣ ስል  ማክቤል ደወለ ግራ እየተጋባሁ አነሳሁት ሄሎ የኔ ውድ አለኝ አቤት አልኩ በመኮሳተር ድምፅ🎈😡😡 ፈልጌሽ ነበር ከቻልሽ አስቸኳይ ነው እባክሽ አለ። እኔም ምን ሊለኝ ነው ብዬ እያሰብኩ  እዛው ከግሮሰሪያችሁ   ፊት ለፊት ያለው ሆስፒታል ነኝ አልኩት ትንሽ እንኳን አልደነገጠም አስቸኳይ ነው ትመለሻለሸ ቶሎ ነይ አለኝ  እኔም ውጤት ለመስማት ተራዬን እየጠበኩ ስለነበር ዝም ብዬ ወጥቼ ሄድኩ ።
ውጤቱን እስክሰማም ጨንቆኛል ግን ለምን ወጥቼ እንደሄድኩ እንጃልኝ።
ልክ  አስፋልቱን ተሻግሬ  በር ላይ ስደርስ ማክቤል በር ላይ ቆሞ በፈገግታ ተቀበለኝ የኔ ፊት ግን ጭራሽ አልተፈታም።
አቤት ምንድነው አልኩት ከፊት ለፊቱ ቆሜ: አትኮሳተሪ እንጂ ጉዳዩን ደግሞ ግቢና እነግርሻለሁ በናትሽ አልገባም እንዳትይኝ ብቻ መቼም እዚህጋ ቆመን እናውራ አትይኝማ አለ የመማፀን ፊት እያሳየኝ እሺ ብዬ አልፌው ገባሁ ከፊቴ ቀደመና የሆነ ወንበር ስቦልኝ ተቀመጥኩ ምን ልታዘዝ አለችኝ አስተናጋጇ ነበረች አይ ምንም አልፈልግም በቃኝ ስል.. ማኪያቶ አምጭላት አለ ማክቤል ::
እሺ ምን ፈልገህ ነው ንገረኝ አሁን እቸኩላለሁ አልኩት።
ተረጋጊ እንጂ እስቲ የሆነ ነገር ቅመሺ አለኝ እየሳቀ ነበር
ወዲያው አስተናጋጇ ማኪያቶውን ይዛ መጣች እንደዛ የምወደው ማኪያቶ ገና ሲሸተኝ አቅለሸለሸኝ ፉት ለማለት ወደ አፌ  እንኳን ማስጠጋት አቃተኝ አጎንብሼ ልውጣ አልውጣ እያለ የሚታገለኝ ነገር እየከበደኝ  አፌን በሶፍት አፍኜ ስጠባበቅ ትንሽ መለስ ሲልልኝ
በቃ ንገረኝ ልሄድ ነው ብዬ ቀና ስል በጣም የምታምር የደም ግባት ያላት ልጅ የማክቤልን ትከሻ ተደግፋ ቆማለች ተዋወቁ ፍቅረኛዬ ነች አለ
በማፌዝ አስተያየት እያየኝ ልጅቷ ፈገግ ብላ እጇን ዘረጋችልኝና መርሀዊት እባላለሁ አለች ስትስቅ ድፕሏ ጎላ ብሎ ይታያል ውበቷንም በእጥፍ ይጨምርላታል ውስጤ ቅጥል እያለ ሰላም እባላለሁ ብዬ ጨበጥኳት እጇን ለቀኳትና በጣም እንደምታምር ነግሪያት ተነስቼ ወጣሁ ማክቤል መጣሁ ብሏት ተከተለኝ በህይወቴ እንደሱ ወራዳ ሰው አይቼ አላቅም በጣም ጠላሁት ከኋላዬ መጥቶ እየሳቀ ቆንጆ ናት እንዴት አየሻት ሲለኝ ድምፁ ሊያስታውከኝ ምንም አልቀረውም ነበር ዝም ብዬ ወደፊቴ ሄድኩ እሱ እየተከተለኝ ይለፈልፋል እንዴት ነው ፍቅረኛሽ ሸመጠጠሽ እንዴ አብራችሁm አትታዩም  ወይስ ተከራይተሽው ነበር ብቻ ምላሱን ብቆርጠው በምን እድሌ መጨረሻ ላይ ትግስቴ ሲሟጠጥ በርጋታ ወደሱ ዞርኩና ፍቅረኛህ በጣም ቆንጆ ናት በጣም ደስ ትላለች ግን ደሞ ታሳዝናለች እንዳተ አይነት ሰው ላይ ስለጣላት ለማንኛውም ያዝልቅላቺሁ እኔን ግን ተወኝ እኔኮ በቃ እርግፍ አድርጌ ትቼሀለሁ እኔ የራሴን ህይወት ጀምሬሀለሁ አንተን ከሰው እኩል እንኳን መቁጠር ካቆምኩ ሳምንታቶች አልፈዋል ሰርግህን እንዳትረሳኝ ከቀደምኩህ አረሳህም ብዬው በቆመበት ጥዬው ሄድኩ ልክ ልኩን ስለነገርኩት አልተከተለኝም ብቸኝነት ሲሰማኝ የምሄድበት የሆነ ቦታ አለ እዛ ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ የምርመራ ውጤቱም አለ ለካ .....
ይቀጥላል


🔻ክፍል ስምንት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
  💔 💔💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰6️⃣

ስለዚህ በሆነ ነገር ልፈትነው አሰብኩ ልክ እንደተገናኘን በመጣደፍ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህማ አልኩት መቼም አንዴ ሲፈጥረኝ እርጋታ ብሎ ነገር አልፈጠረብኝም እሺ ሞልቃቂት አለ እየሳቀ ሲስቅ አንዳች ሰውነትን ስንጥቅ የሚያደርግ ምትሀት ነገርማ አለው )
በቃ ተወው ስንወጣ መኪና ውስጥ እነግርሃለሁ ብቻችንን ስንሆን አልኩት እሺ እንደተመቸሽ አለኝ ደሞኮ ሲያወራ ቃላቶቹ አንቺ ቅደሚ አንቺ የሚባባሉ ነው የሚመስለው አቤት እርጋታቸው ።
ልክ መኪና ውስጥ ስንገባ ወደፊት ንዳው አልኩት የት እንደሚሄድ ባያቅም ይነዳዋል ብቻ ዞር ስል ትንሽዬ ቦታ አየሁ አቁመው አቁመው ሳይታወቀኝ አንባረኩበት እሺ ተረጋጊ እንጂ ሰላም አለ ።
እሺ ወደ ታች ታጠፍ አልኩት ታጠፈ  ትንሽ ተጉዘን ከመኪናው ወረድን ለሁለታቺንም በደንብ እየተያየን ለማውራት የሚመቸንን ቦታ ከመረጥን ቡሀላ ቁጭ አልን እሱ ትንሽ ከፍ ያለ ድንጋይ ላይ እግሩን ከፍቶ ተቀመጠ እኔ በእግሮቹ መሀል  ገብቼ ቁጭ ልል አልኩና ድፍረት ይሆንብኛል ብዬ ከጎኑ ወደሱ ዞሬ ቁጭ አልኩኝ
እሺ አጂሪት ቀጥይ አለ። ለመስማት እንደጓጓ  የሆነ ነገር ሹክ ብሎኛል ።
ምን መሰለህ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህ ነበር አልኩ ምን ብዬ እንደምጀምር ግራ እየገባኝ እኮ ነው ። ጠይቂኛ ብቻ አፈቅርሀለሁ እንዳትይኝ እንጂ አለ አነጋገሩ የቀልድ አይመስልም ማለት አልኩት አንዳንድ ጥያቄዎች መልስ የላቸውም ቀጥይ አለ።
እሺ ብዬ የራሴን ጥያቄ ልግባው 😂😂😂😂😂😂 በቃ ለምሳሌ መንገድ ላይ እየሄድክ አንድ የኔ ቢጤና አንድ ሚሊየን ብር ብታገኝ ቀድሞ ልብህ የትኛውን ይከጅላል አልኩት ::
መልሱን እስክሰማ   ተጨነኩ
እእእ በቃ ለዚህ ነው እዚህ ድረስ ያመጣሺኝ ብሎ አፍንጫዬን ጎተተኝና
ወደ መልሱ ስገባ እኔ የኔ ብጤውን እመርጣለሁ ምክንያቱም ይቀጥላል .....................



🔻ክፍል ሰባት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔 💔💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰5️⃣

ልብሴን ለባበሼ ስወጣ ልኡልጋ ደወልኩ አነሳውና እዛው እየጠበቀኝ እንደሆነ ነገረኝ ሄድኩ ውስጥ ስንገባ ማክቤል የለም ለነገሩ አይኑን ማየት እራሱ ነበር ያስጠላኝ ልክ ስንገባ የሆነ ምግብ ሸተተኝ እና በጣም አማረኝ ለልኡል ልነግረው ነበር ግን ይታዘበኛል ብዬ ተውኩት ።
አስታናጋጇ ትንሽ ቆይታ ስገባ የሸተተኝን ምግብ ባጠገቤ ይዛ አለፈች መቋቋም እስኪያቅተኝ ድረስ አማረኝ ስትመለስ አስተናጋጇን በእጄ ጠርቻት አሁን ባጠገቤ ይዘሽ የሄድሺውን ምግብ ይዘሽልኝ ነይ አልኳት ልኡልንም ምን እንደሚፈልግ ጠይቃው ሄደች
ምግባችንን ጨራርሰን እየተጎነጨን ዝም ብለን እያወራን ነው ልኡል በጣም ተጨዋች ነው ።
አጉል እንደሀብታም አያካብድም በጣም እየገረመኝ ነው ጨራርሰን ልንወጣ ስንል ማክቤል ከፊት ለፊት መጣ አየተሳሳቅን ባጠገቡ አለፈን በግልምጫ አንስቶ አፈረጠኝ ቦታም አልሰጠሁትም የወደድኩትን ያህል ነው ያስጠላኝ ብቻ በቃ ከልኡሌጋ በጣም እየተቀራረብን ነው አንዳንዴ ሳስበው በጣም ነው ሚገርመኝ ፈጣሪ እንዴት ሁሉን ነገር አሟልቶ ለ1 ሰው ይሰጣል ብዬ አሰብኩ ከመልክ መልክ በሀብት ላይ ሀብት በፀባይ ላይ ፀባይ አላቅም ብቻ ይሄ ጎሎታል ማይባል እንደስሙ ልኡል የሆነ ሰው ነው አንዳንዶቹ ሀብት  ካላቸው በጎነት ይጎላቸዋል በሀብታቸው ምንም ነገር ማድረግ የሚችሉ የሚመስላቸው ተራ ሰዎች በዚች አገር ላይ እልፍ ሰዎች አሉ አንዳንዶቹ ደሞ መልክ ካላቸው ፀባይ ይነሳቸዋል ብቻ ልኡሌ ከማቃቸው ሰዎች በብዙ ነገር ተለየብኝ አሁን አሁንማ ሳላገኘው ማደር እራሱ በጣም ጭንቅ ክፍት ይለኝ ጀምሯል አረ እንደውም በጣም ነው የሚያነጫንጨኝ ማክቤልን ከልዑልጋ ማወዳደር እየከበደኝ መጣ።
ማክቤልን ማስታወስም ማየትም ስለማልፈልግ የነሱ ግሮሰሪ እግራችን ደርሶ አያቅም ::
ከልኡልጋ በደንብ ማውራት ከጀመርን አንድ ወር አልፎናል ይመስለኛል የሆነ ስሜት እየተሰማኝ ነው ነገር ግን እሱጋ ስደርስ አላስነቃም አንዳንዴ ልኡሌ እየተደበረብኝ  ይመስለኛል ምክንያቱም ማክቤል ያለኝን ሳስታውስ እውነት እንደሱ ሀብታም ስላልሆነኩ ባይወደኝስ ብዬ አስባለሁ:

🔻ክፍል ስድስት ከ2️⃣5️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


ታሪኩን እየወደዳችሁት ነው?

አዎ ❤️
አይ😔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 4️⃣

አዎ ላወራሽ ፈልጌ ነበር አለ ከተመቸኝ እሺ አልኩት በቃ ቻው ደህና ደሪ ስልኩ ጆሮዬ ላይ ተዘጋ ከትንሽ ደቂቃዎች ቡሀላ ወደ ልኡል ጋ ደወልኩ አያነሳም ልረብሸው ስላልፈለኩ ዝም አለኩ እንቅልፌ ሸለብ ከማድረጉ ስልኬ ጮኸ ልኡል ነበር አነሳሁትና በሰላም ገባህ አልኩት አዎ እየነዳሁ ስለነበር ነው ያላነሳሁት ይቅርታ አለኝ የተወሰነ ካወራን ቡሀላ ቻው ተባብለን ተኛሁ ጠዋት ከእንቅልፌ የተነሳሁት 3 ሰአት ላይ ነበር ቁርሴን በላልቼ ስጨርስ ወደ ጓደኛዬጋ ልወጣ ልብሴን ስለባብስ ስልኬ ጮኸ ማክቤል ነው አነሳሁት ሄሎ አለኝ አቤት አልኩት ዛሬ እንገናኛለን ተባብለን አልነበር ከተመቸሽ አሁን ላግኝሽ በራቺሁ ጋ ነኝ አለ ጠብቀኝ ብዬው ከ10 ደቂቃ ቡሀላ ወጣሁ ተኮሳትሮ ነበር የጠበቀኝ ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ምንድነው ልታናግረኝ የፈለከው አልኩት በውስጤ ይቅርታ ሊጠይቀኝ እንደሆነ እርግጠኛ ነበርኩ እኔም ትንሽ ከለመነኝ ቡሀላ እሺ እንደምለው ወስኜ ነበር እሱ ግን የትናትናው ልጅ ፍቅረኛሽ ነው አለ ተኮሳትሮ ለምን ጠየከኝ አልኩት አይ እኔ እንድትጎጂ አልፈልግም ላስጠንቅቅሽ ብዬ ነው ማለት አልኩት ውስጤ ግራ ግብት ብሎታል እሱኮ በጣም ሀብታም ነው በጣም ታዋቂ መኪና አስመጪና ላኪ ድርጅት አላቸው ከወንድሞቹጋ በዛ ላይ የራሱ የሆነ ምን የመሰለ ሆቴል አለው ስታስቢው ዝቅ ብሎ ካንቺጋ የሚሆን ይመስልሻል እኔ እንኳንኮ የራሴ የምለው ምንም ነገር ሳይኖረኝ ባባቴ ጎሮሰሪ  ተኩራርቼ ነው አንቺን ደሀ ነሽ ብዬ የተውኩሽ ?።እስኪ እራስሽን ተመልከቺ አንቺም ሆንሽ ቤተሰቦቺሽ ከዚህ ከቆመ የጭቃ ቤት በቀር የራሴ የምትሉት ምን አላቺሁ እና ተጠቀቂ ብሎኝ  በቆምኩበት ጥሎኝ ሄደ ብቻ አላቅም በስለት እንደተወጋሁ ነገር ሰውነቴን ሁላ ደነዘዘኝ የማቀው ማክቤል አልመስልሽ አለኝ ለአይኔ አስጠላኝ በጣም ቀፈፈኝ እስከዛሬ ፍቅረኛዬ መሆኑን ሳስብ ሰቀጠጠኝ ፈዝዤ በቆምኩበት የሆዴን ህመም መቆጣጠር አቅቶኝ መሬት ላይ ወደኩ ከየት መጣ ሳልለው የሆነ ሰውዬ መቶ አነሳኝ እራሴን ለማረጋጋት ከሞከርኩ ቡሀላ ወደ ቤት ገብቼ ተኛሁ ያለኝን በሙሉ ማሰብ ጀመርኩ ግማሹ ልቤ እውነቱን ነው አንቺ ተመርቀሽ እንኳን ስራ የለሽ የራሴ የምትይው የግል ቤት የለሽ ይለኛል ግማሹ ልቤ ግን ለፍቅር ገንዘብ መስፈርት እንደማይሆን እየነገረኝ ነው ብቻ ጭንቅላቴ ሊፈነዳ ደርሷል ሳወጣ ሳወርድ ከራሴጋ ስጣላ ስታረቅ ብቻ ክፍሌ ሆኜ በሀሳብ ሀገሪቷን ሳስስ ከሀሳቤ ልኡሌ ነበር ደውሎ የቀሰቀሰኝ እንደከፋኝ እንዲያቅ ስላልፈለኩ እንደመሳቅ ብዬ ሄሎ አቶ ልኡል ምን ነበር ስለው አይ ዛሬስ ፍቅረኛሽን አታስቀኚውም ወይ ልልሽ ነበር አለኝ ::በዛ እረጋ ባለ ድምፁ አይይ ታውቆብሀል በቀጥታ ላግኝሽ ነው ሚባለው አልኩት እየተፍለቀለኩ እሺ የት እንገናኝ እዛው የባለፈው ቤት ነዋ አልኩት እየተፍለቀለኩ ወዲያው ተነስቼ ከሌላ ጊዜው በተሻለ የሚያሳምረኝን ልብስ መምረጥ ጀመርኩ
``
።

🔻ክፍል አምስት ከ2️⃣5️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 3️⃣


ቀኑ እየመሸ ሄደ ከ10 ሰአት ጀምሮ ስልኬን ሳነሳ ስጥል ቆየሁ ልክ 11.50 ሲል ደወለልኝ ውጪ ሰፈር መጥቻለሁ🙄
ክው አልኩ እንዴ ልብስ ሳልቀይር ሳልዘጋጅ ከራሴጋ እያወራሁ በፍጥነት ከሌላ ጊዜው በላይ ቆንጆ ሚያደርገኝን ልብስ መርጬ ለበስኩ : ፀጉሬ ከመጀመሪያውም ተሰርቼው ስለነበር ያን ያህል አላስቸገረኝም ።
ይቅርታ አስጠበኩህ አደል??
የሴት ነገር የታወቀ ነው በሰላም ነው የፈለግሽኝ ??? ቀጥታ ወደ ጉዳዩ ገባ
ቀለል ያለ ሰው እኔም ቀለል አድርጌ እዚህ ነው እንዴ ምናወራው ባይሆን እኔ ከፍላለሁ ሻይ ቡና እንበል እንጂ !!
ሳቀብኝ ምናልባት ከቸኮልሽ ብዬ ነው እንጂ እሺ ምታቂው ቤት አለ እዚህ አካባቢ ወይስ በኔ ምርጫ ልውሰድሽ ???
አይ እኔ ማቀው ቤት አለ አዛ ልውሰድህ አልኩት ። ቀጥታ እነ ማክቤልጋ ወሰድኩት ገባን ቁጭ አልን እሺ ለምን እንደፈለግሽኝ ንገሪኝ ከማዘዛችን በፊት አለኝ ።
በቃ አጠር ቀልጠፍ አድርጌ እንባ እየተናነቀኝ የ6 አመት ፍቅረኛዬ ምን እንደተፈጠረ እንኳን ሳይነግረኝ ከመሬት ተነስቶ እንለያይ አለኝ 
ሳላስበው እንባዬ ካይኔ ዝርግፍ ብሎ ፈሰሰ።
አይዞሽ ብሎ ሶፍት ሰጠኝ ቀና ስል ማክቤል እያየኝ ነበር እሱ ፊት እንደዚህ መሆኔ በራሴ እየተናደድኩ ለመሳቅ ሞከርኩ እንዴ ምነው አለኝ ፍቅረኛዬኮ ፊት ለፊት እያየኝ ነው እንዴ እዚህ ምን ይሰራል እዚህ እንደሆነ አውቀሽ ነበር እንዴ ብሎ ተከታታይ ጥያቄ ጠየቀኝ።
አዎ ይሄ ቤት ያባቱ ነው እሱ ደሞ ከዚህ አይጠፋም ይቅርታ ግን ላናድደው ፈልጌ ነው እሱ ከማያቀው ሰውጋ ሆኜ ለሱ ደሞ ካንተ የተሻለ ሰው አላገኘሁም ማለቴ ላስቀናው ከፈለኩ ከሱ የተሻለ ቆንጆ ሰው መሆን አለበት ብዬ ሳስብ አንተ መጣህልኝ !!ቁጥብ ፈገግታውን ለገሰኝ ሲስቅ የሆነ ብቻ የሚያስደነግጥ ነገር አለው እኔ ምልሽ  ካንቺ ምን አጥቶ ነው የተጣላሽ ????? መጀመሪያ ከኔ ምን ጎድሎት ነው የተጣላኝ ብለሽ እራስሽን ጠይቁ አለኝ።
ማወቅ ምፈልገው እሱን ነው አልኩት እና ምግብ እንዘዝ አለኝ አስተናጋጁን ጠራነው እሱ የራሱን ምርጫ ሲያዝ እኔ የቀድሞ ፍቅረኛዬ አብዝቶ ሚወደውን ምግብ አዘዝኩ እየተመገብን እያለ ላጉርስህ ማለቴ ካልደበረህ??? አልኩት ምነው እያየሽ ነው እንዴ አለኝ አዎ አይኑን ከኛ ላይ መንቀል አልቻለም አልኩት እሺ አለኝ በዙም ደስ እንዳላለው ያስታውቃል ግን የኔ አይና አውጣነት አጎረስኩት በልተን እንደጨረስን በቃ እንሂድ አለኝ እሺ ብዬ ተነሳሁና እጁን ያዝኩት የሆነ የገባው ነገር ነው ወደ እራሱ አስጠግቶ አቀፈኝ ልክ ከበሩ እንደወጣን ልሸኝሽ አለኝ ካላስቸገርኩህ አልኩት ደርሰን ልወርድ ስል ለካ እስካሁን ስሙን አላቀውም እውይ እረስቼው ስምህንኮ አልነገርከኝም አልኩት የዛኔ ከት ብሎ ሳቀብኝ እንዴት ስሜን እንኳን ሳታቂ የጋበዝኩሽን ምግብ ትበያለሽ ደሞ ጭራሽ መኪናዬ ውስጥም ገብተሻልኮ አለኝ ከደበረህ ይቀራላ አትንገረኝ ተወው ብዬ ፊቴን ዘፈዘፍኩት ባክሽ አታኩርፊ  ልኡል እባላለሁ አለኝ ስምን መለአክ ያወጣዋል ማለትኮ እንዳንተ ነው  በቃ ቻው አልኩት እሺ ብሎ ሄደ መኪናው ካይኔ ሲሰወር ወደ ቤቴ ገባሁ ልክ ሰገባ ማዘር ምነው ቶሎ መጣሽ ብላ ሙድ ያዘችብኝ ሰአቱን ሳየው2 ሰአት አልፏል ትንሽ ካወራን ቡሃላ ወደ ክፍሌ ገብቼ ጋደም ከማለቴ ስልኬ ጮኸ ሳየው ማክቤል ነው ።ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ አላነሳውም ትንሽ ይበሳጭ ብዬ ዝም አልኩት ድጋሜ ደወለ አሁንም ዝም   በ4ኛው  አነሳሁት ሄሎ አልኩ በመኮሳተር ድምፅ ምነው ስልክ አታናሺም አለ ::
መጀመሪያ ሰላምታ አይቀድምም ስልክ ያላነሳሁት ደሞ ከፍቅረኛዬጋ ነበርኩ ምነው በሰላም ነው የደወልከው??
ይቀጥላል

🔻ክፍል አራት ከ2️⃣5️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል2️⃣

ምሽቱን ሙሉ አይኔ ደም እስኪመስል ሳለቅስ አመሸሁ አንድም ቀን ካፉ ክፉ ቃል አውጥቶ አስቀይሞኝ አያቅም ይሄ ነው የምለው መጥፎ ፀባይ የለበት በድንገት እንደዚህ ያደረገው ነገር ግራ ገባኝ አልቅሼምም አልወጣ አለኝ::

  ማታ መሽቶ እናቴ ወደቤት መጣች ከእህቴጋ ሲያወሩ እየሰማኋቸው ነው እህትሽ ምን ሆና ነው በጊዜ ወደመኝታ ቤት ያመራችው ??
እኔጃ እማዬ ከመጣሁ ጀምሮ አላናገረችኝም እስቲ አንቺ አናግሪያት አለቻት።
እኔም ምንም እንዳልተፈጠረ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ እናቴ አይታኝ ተያት በቃ እንቅልፍ ወስዷታል ብለው ከክፍሌ ወጡ።
   ሌሊቱን ሙሉ አንዴ ስነሳ አንዴ ስቀመጥ አንዳንዴም እንደ ህንድ አክተር ልግደለው እንዴ እላለሁ አንዳንዴ ደሞ በድንገት ቢሊየነር ሆኜ በየቲቪው ብታይኮ እራሱ እየለመነ ይቅርታ ይጠይቀኛል ብቻ ሌሊቱ እንዲሁ ነጋልኝ በሀሳብ ስብሰለሰል ።
  
   በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ላይ ስነሳ ቤት ማንም የለም ከነጋ ቡሀላ ስለሆነ እንቅልፍ የወሰደኝ አርፍጄ ነው የተየሳውት ቀጥታ ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ ወደ ቤተክርስቲያን ሄድኩኝ ድፍት ብዬ አለቀስኩ የሆነ ሸክም ከላዬ ላይ እንደቀለለ ነገር ተሰማኝ ወደ ቤቴ ተመልሼ ምሳ ሰአት ሳይደርስ ቤቱን ፏፏ አድርጌ እናቴን ጠበኳት ተጨዋውተን ወደ ስራዋ ተመልሳ ሄደች ።
እኔም ለባብሼ ወደነማክቤል ሬስቶራንት ሄድኩኝና አስጠራሁት ገና ሲያየኝ ፊቱን ቅይይር አደረገው ።

ምንድነው??
ማክቤል መለያየታችን ይሁን እሺ  ቢያንስ ግን ይሄ ነው ጥፋትሽ በለኝና ልወቀው እኔም ጭንቅላቴ እረፍት ያግኝ አልኩት።
        በቃ መለያየት ፈለኩ ተለያየን ሌላ ምክንያት መደርደር አያስፈልገኝም እየመጣሽ እንዳትበጠብጪኝ ክብርሽን ጠብቂ ።   
ይሄን ተናግሮ በቆምኩበት ጥሎኝ ሄደ
እንባ እየተናነቀኝ ፊቴን አዙሬ ወደ ቤቴ ሄድኩኝኝኝ ምሽቱን በሙሉ ከራሴጋ ሳልሆን መምሸቱም መንጋቱም ስለማይቀር መሽቶ ነጋ ዛሬም በጠዋት ተነስቼ ወደቤተክርስቲያን ሄድኩኝ ።
ቅዱስ ሚካኤል አባቴ ለኔ ካላልከው በቃ ከልቤም ከህይወቴም አውጣልኝና አንተ የተሻለውን እንደምታዘጋጅልኝ ስለማምን አንተን እጠብቅሀለሁ የራሴን ሰው እስክሰጠኝ አሱን ግን አባቴ ከነትዝታዎቹ ከሀሳቤም ከኔ ህይወት አውጣልኝ ብዬ ፀለይኩ።።
ወደ ቤቴ ተመልሼ እንደተለመደው እናቴን ምሳዬን ሰርቼ ቤቴን አፀዳድቼ ጠበኳት ከሷጋ ተሳስቀን የልብ የልባችንን አውርተን ወደስራዋ ሄደች ።
  ልክ እናቴ ሄዳ ለብቻዬ ቁጭ ስል ቀጥታ ሀሳቤ ውስጥ ይመጣል ። አልጋዬ ውስጥ ገብቼ ቁጭ አልኩ እንዴት ነው እሱን መበቀል ምችለው ????????
ከብዙ ሀሳብ ቡሀላ ጭንቅላቴ ውስጥ 1 ሰው መጣ ነዛሬ ሳምንት ሆዴን በጣም እያመመኝ ተቸግሬ ነበር ።
ለመታየት ወደ ሆስፒታል አመራሁ ልክ ከtaxi ወርጄ የሆስፒታሉ በር ላይ ስደርስ ከአንድ ልጅ ይሁን ሰውዬ ብቻ አላትሞ መሬት ላይ ዘረረኝ ። በጣም ደንግጦ ወይኔ ይቅርታ በሀሳብ ተውጬ ነው ተጎዳሽ የኔ እናት እእ በፈጣሪ ስም ደና ነሽ  ብቻ ምን ልበላችሁ ተርበተበተ ከወደኩበት አነሳኝ ለጊዜው ትንሽ ቢያዞረኝም ያን ያህል ህመም አልተሰማኝም ነበር። ወዴት ነሽ እ ምን ልርዳሽ አለኝ ወደ ሀኪም ቤት ልገባ የነበርኩት ልጅ ወደ ቤቴ ነኝ አልኩት ።
እሺ ነይ እኔ ልሸኝሽ  አለኝ እንኳን ለመንዳት ለማየት ወደምታታሳሳው መኪናው ውስጥ አስገባኝ ።
ይቅርታ አላየሁሽም ነበር እሺ ካመመሽ ወይ የሆነ የጉዳት ስሜት ከተሰማሽ ደውይልኝ ብሎ ቁጥሩን ሰጠኝ ወደ ቤቴ ሸኝቶኝ ተመለሰ ። ይኸው 1 ሳምንት ሙሉ ትዝ አላለኝም ነበር ዛሬ ግን ማክቤልን ለማስቀናት ለአንድም ይሁን ሁለት ቀን ይተባበረኝ ይሆናል ብዬ አሰብኩ።
 
በሰአቱ ስሙን አልነገረኝም ነበር ስልኬ ላይ የገፈተረኝ ልጅ ብዬ ነው save ያደረኩት ያ በደንብ ለማስታወስ ያህል ማለት ነው😂😂   

   ስልኬን አነሳሁ ደወልኩ አያነሳም 😣
  ወዲያው ስልኬን ከጄ ላይ ሳላስቀምጠው መልሶ ደወለ ።
     ሄሎ!!!
ሄሎ ጤና ይስጥልኝ ሰላም ነህ (ምን እንዳርበተበተኝ ፈጣሪ ይወቀው)።
   አብሮ ይስጥልን ሰላም ነኝ ማን ልበል?
(ወይኔ ድምፁ ደስ ሲል ከዛ ከርከሮ ማክቤል ተብዬ አንፃርማ ይሄ)....
እእእእ ይቅርታ ሰላም ነኝ እእ ባለፈው ሆስፒታል በር ላይ ገፍትረህ የጣልከኝ ልጅ።
   እእእ አወኩሽ ምነው አመመሽ እንዴ እእ???
አረ አደለም ሰላም መሆኔን ልንገርህ ብዬ ምናልባት ተጨንቀህ ከነበር አልኩት ቀልድ ማውራቴ ነው በኔ ቤት እሱ ግን በስሬስ
እውነት ለመናገር አስቤሽ ነበር ግን በሰአቱ ስልክሽን አልወሰድኩም እና ቢያማት ትደውል ነበር ብዬ ዝም አልኩ።
   አለኝ።
አረ አላመመኝም ደና ነኝ ግን ከይቅርታጋ 1 ነገር ላስቸግርህ ነበር ማለቴ ከተመቸህ ዛሬ ላገኝህ ነበር 1 ጉዳይ ላወራህ ነበር ። (አይና አውጣነቴን ከየት እንዳመጣሁት አላቅም) 
እእ ምነው በሰላም ነው የፈለግሽኝ???
አዎ በሰላም ነው ግን ካልተመቸህ ችግር የለውም ተወው በቃ ።  አልኩት
አረ እንደዛ አላልኩም ወደማታ አካባቢ ስራ ከጨረስኩ አገኝሻለሁ ሰፈርሽ ባለፈው ያደረስኩሽ ቦታ ነው አደል???

   አዎ አዎ እዛ ነው ደውልልኝ ቀደም ብለህ ማለቴ ከተመቸህ አልኩት ።
 እሺ እደውልልሻለሁ መልካም ቀን።
ስልኩ ተዘጋ
       

🔻ክፍል ሶስት ከ2️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

5 619

obunachilar
Kanal statistikasi
Kanalda mashhur

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹          💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​ ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀ...
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹          💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​ ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀ...
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹          💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​ ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀ...
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹          💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​ ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀ...
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹          💗የፍቅር ማእበል💗    ‍ ​ ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀ...