የሰባት ዓመት ታዳጊን በማገት በሚሊየን ገንዘብ የጠየቁ ተፈረደባቸው❗️
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ወልመራ ወረዳ ሆለታ ከተማ የሰባት ዓመት ታዳጊን በማገት በሚሊየን ገንዘብ የጠየቁ ተፈረደባቸው፡፡ በምዕራብ ሸዋ ዞን ጠቅላይ ፍርድ ቤት እያንዳንዱ የ11 ዓመት ጽኑ እስራት የተፈረደባቸው ሶስት ወጣቶች እራሳቸውን በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በማስመሰል ወንጀሉን መፈጸማቸው ነው የተገለጸው፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት የዞኑ አቃቤ ህግ ባለስልጣን በሽምቅ መንግስትን በሚፋለሙት ታጣቂዎች ስም ሰዎችን በማገት ገንዝብ የመጠየቅ ወንጀል አሁን አሁን እየተበራከተ መጥቷል፤ ብለዋል፡፡