"ሐያ!አለ ሰሏህ!! ሐያ!አለል ፈላህ!!"
የአምሪኪዋ ከተማ ኒውጄርሲ የአዛን ጥሪ በግልፅ በማይክ ወደ ውጭ እንዲወጣ
አፀደቀች።በኒውጄርሲ ፓተርሰን መስጂድ አዛን እንዲፈቀድ የደነገገው የከተማዋ ካውንስል
ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ውይይት ካደረገበት በሗላ መሆኑም ታውቋል።
ፍቃዱ ሌሎች እምነቶችንም ያካተተ ሲሆን ከአዛን ጥሪ በተጨማሪም ቤተስኪያኖች ደወል
ማሰማትና ለአማኞቻቸው ጥሪ ማድረግ እንደሚችሉ ገልፆ ከአምስት ደቂቃ መብለጥ
እንደሌለበትና ሰዓቱም በነሱ አቆጣጠር 6.00 am እና10.00 pm መሆኑን እና
ከፌብሩዋሪ 25 ጀምሮም ስራ ላይ እንደሚውል ካውነስል ሻሒን ኻሊቅ ለPaterson
Times ገልፀዋል።
ፓተርሰን ከ 30 ሺህ በላይ ሙስሊሞችና ከደርዘን ያላነሱ መስጂዶች የሚገኙባት ከተማ
ስትሆን ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት የተሰደዱ ሙስሊሞች የሚኖሩባት ከተማ ነች።
በአውሮፓና በምዕራቡ ዓለም አንዳንድ ሀገሮች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የድምፅ ብክለት
በሚልና ተልካሻ ምክንያቶች አዛንና ሚናራዎች እንዲታገዱ በቀኝ አክራሪ ፅንፈኛ ነጮች
ሲስተጋባ እንደነበርና አሁንም እየተስተጋባ መሆኑ ይታወቃል።
ከአውሮፓ ማንኛውም Relegious Call ሀይማኖታዊ የሆነ የድምፅ ጥሪ አዛንን ጨምሮ
ኒዘርላንድ በ1980 በህግ የፈቀደች ሀገር ስትሆን የድምፅና የሰዓት አጠቃቀም ላይ ብቻ
ማስተካከያ እንዲደረግ አዛለች።
በስዊዘርላንድ south fittja mesjid ለመጀመሪያ ጊዜ በ2013 የአዛን ድምፅ በይፋ
በማይክ ያስተጋባ ሲሆን ሆላንድ አምስተርዳም ደግሞ በ2019 አዛን እንዲስተጋባ
ፈቅዳለች።
እነሆ!ያ በቢላል (ረ.ዐ )የተጀመረው ጥሪ ካፅናፍ አፅናፍ
እያስተጋባ ምድርን ይሞላል አዛን የማይሰማበት የዓለማችን ክፍል አይኖርም።
አቡ ሙስዓብ