ወርቃማ ንግግሮች


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።
አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot
🍂

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


‏{رَبَّنَا هَب لنَا مِن أَزوَاجِنَا وَذُرِّيَّاتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍ}


🍂


"በጭንቅ እና በመከራ ጊዜ ዱዓው ተቀባይነት እንዲያገኝ የሚፈልግ በድሎት ጊዜ ዱዓ ማድረግ ያብዛ።"

ረሱል (ﷺ)


ይህ በጋዛ በፍልስጤን ምድር ነው።

የመጀመሪያው የረመዷን ፍጥር ነው።
ንብረት ይወድማል ሀገር ይፈርሳል ደም ይፈሳል አንጥንት ይሰበራል። ነፍስ እስከ ወዲያኛው አለም ላይመለስ ይሄዳል። ይህም የዲን ፅናት ነው። ዲን ኢማን ካለን ሁሉም ነገር ምንም ነው ከባዱ ነገር ራሱ ነፍስ ከስጋው ብትለያይም ክብር ነው።


ለኢስላም ለሀገራቸው ሲሉ ሁሉንም መላ ቤተሰቡን የሸኘ እልፍ ነው። ቢሆን አሁንም በክብር አሉ በግልፅ ይዋጋሉ በግልፅ ያመልካሉ ምንም ማንንም አይፈሩም ይህ የሆነው በኢስላ ባህር ውስጥ ነው።

አላህ ፅናቱን ብርታቱን ይስጣቹ 🤲


እንኳን ለተከበረው ወር ረመዷን አደረሳችሁ።

አላህ ከሚጠቀሙበት ባሪያዎቹ ያድርገን።


ባሳኡዲ አረቢያ የረመዷን ጨረቃ በመታየቷ ነገ ቅዳሜ march 1/2025 (የካቲት 22/2017 ዓ.ል) የመጀመሪያው የ1446ኛው አመተ ሂጅራ የረመዷን ቀን ይሆናል።

ምንጭ-
Inside the Haramain

= ረመዷን ሙባረክ =


ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፦

{ وَٱلۡقَمَرَ قَدَّرۡنَـٰهُ مَنَازِلَ حَتَّىٰ عَادَ كَٱلۡعُرۡجُونِ ٱلۡقَدِیمِ }
"ጨረቃንም የመስፈሪያዎች ባለቤት ሲሆን እንደ ዘንባባ አሮጌ ቀንዘል እስኪሆን ድረስ (መሄዱን) ለካነው።" [ያሲን፡ 39]

የጨረቃ መስፈሪያዎች የተባሉት በየ ወሩ ለ 28 ቀን የሚያልፍበት ቆይታ ነው። ቀጭን ሆና ጀምራ እያደገች ትሄድና ሙሉ ጨረቃ ትሆናለች። እንደገና እያነሰች ሄዳ በምስሉ ላይ እንደሚታየው ልክ እንደ ደጋን የጎበጠ የተምር ቀንዘል ጎብጣ ትቀጥናለች። በመጨረሻ ትጠፋለች።
ወሩ 30 ቀን ሲሆን ጨረቃ ለ 2 ሌሊቶች ትደበቃለች (አትታይም)። ወሩ 29 ቀን ሲሆን ደግሞ ለ 1 ሌሊት ትደበቃለች።

ኢስላማዊው የቀን መቁጠሪያ የጨረቃን እንቅስቃሴ መሰረት ያደረገ ነው። ስለሆነም ዘካ የሚወጣው፣ የልጆች ለአቅመ መጠን መድረስ የሚወሰነው በጨረቃ አቆጣጠር መሰረት ተሰልቶ ነው። በጨረቃው አቆጣጠር አንድ አመት 354 አካባቢ ቀናት ሲኖሩት የፀሐዩ አቆጣጠር ደግሞ 365 አካባቢ ቀናት አሉት። ስለዚህ የ 11 ቀን ልዩነት አለ ማለት ነው።

ማስታወሻ፦
አንዳንዶች የጨረቃን መውጣት ስንከታተል "ጨረቃን ታመልካላችሁ" እያሉ ይከስሳሉ። ለነዚህ አላዋቂዎች የምንላቸው እናንተ የፀሐይን እንቅስቃሴ መሰረት ያደረገውን መቁጠሪያ የምትጠቀሙት ፀሐይን ስለምታመልኩ ነው ወይ? ለምን በራሳችሁ ላይ ትተኩሳላችሁ?
=
ኮፒ Ibnu Munewor


السلام عليكم ورحمة اللہ وبركاته

እንኳን ደስ አላችሁ

ዛዱል መዓድ ኢስላሚክ ሴንተር በ ሸይኽ አሕመድ ሸይኽ ኣደም የሚሰጡ ትምህርቶችና መረጃዎችን በሶሻል ሚዲያ እንዲሁም በቅርቡ ይፋ ባደረገው ዌብሳይት ሲያስተላልፍ መቆየቱ ይታወቃል ።
አሁን ደግሞ ሁሉንም በዛዱል መዓድ የሚሰጡ ትምህርቶችን፣ የፈትዋ መጠየቂያ፣ እንዲሁም ወቅታዊ መልዕክትና መረጃዎችን
ያካተተ ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ ልዩ አፕሊኬሽን ለዛዱል መዓድ ቤተሰቦች ይፋ ማድረጉን ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው።

አፕሊኬሽኑን ለማውረድ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ።

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.alif.zadulmead_islamic_center_app


😵🤔🙁😝😤☹️🙁☹️
🛜ታላቁ የውይይት ፕሮግራም▶️
🙁☹️😭🙁😭🙁☹️🙁
🎤
      ተ
🎁
             ጀ
▶️
                  መ
▶️
                          ረ
▶️

ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም!
ሊንኩን ለሌሎችም ሼር አድርጉት‼

 ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ ➘
t.me/twhidsun?livestream
t.me/twhidsun?livestream


✈️ታላቅ የውይይት ፕሮግራም 📣

የፊታችን ማክሰኞ በቀን 18/ 06 / 2017
🔠ከምሽቱ 3፡00 ከተለያዩ የሃገራችን ክፍል ከሚታደሙ ወንድሞች ጋር የአክፍሮት ሃይላት በተመለከተ የውይይት ፕሮግራም ይኖረናል ።

ውይይቱ የሚታደሙ
➡️ከጂንካ
➡️ከወላይታ
➡️ከጉራጌና ከሌሎች አካባቢዮችም የምናስተናግድ ይሆናል
~~
🔥 t.me/twhidsun 😤☹️🙁☹️
🔥 t.me/twhidsun 😤☹️🙁☹️


~🍂

ሙሳኮ አላህ ለርሱ ብሎ ባህሩን እንደሚከፍልለት አያውቅም። ባህሩ ጋር የደረሰውም አስቦበት አልነበረም። ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ነበር “ጌታው መቼም በዚያ አጣብቂኝ ውስጥ  እንደማይተወው”። አቤት… የቂን፤ ዐጀብ ተወኩል ፤ “ተው(አትስጉ) ጌታዬ ከኔ ጋር ነው” የሚል ተራራ ኢማን!!  ኧረ  እንዲህ አይነት የቂን ሸልመን  ያ ወዱድ!!


~

ይህ ንጋት ለአንተ ነው ይህ ቀን ለአንተ ነው ይህች ፀሃይ የምትወጣው ለአንተ ነው።
በተሰጠህ ዛሬ እንጂ በሚመጣው ቀን ለመደሰትም ለመስራትም ቀጠሮም ሆነ መኮፈስ የለብህም።

ለነገ እቅድ የያዘ እንጂ ነገን የኖረ ማንም የለምና ዛሬን ተጠቀምባት።
መልካም ቀን ከሃላል ከስብ ጋር ይሁንልን።


ጥያቄ
✍ ከሚከተሉት ውስጥ የረመዳን ወር ከሌሎቹ 11 ወራቶች ለየት የሚያደርጉት የራሱ የሆኑ መለያወች መካከል የሆነው የቱ ነው??

(ትክክለኛው መልስ ሰታገኙ
ጠቃሚ ቻናሎች ታገኛላችሁ  +add📈
👇👇


"አላህ አዳዲስ ጅማሮዎችን ሲሰጥህ… የበፊት ስህተቶችን አትድገም።"
[ነጂብ መህፉዝ ]

ምናልባት ትናንትህ  በብዙ ስህተቶች ተሞልቷል። ትናንት ላይ ያባከንካቸው በርካታ እድሎች ይኖራሉ። ግን አስተውል ዛሬ አዲስ ጀንበር ወጥታለች… ጨለማውን የገረሰሰች ጀንበር… ስለዚህ አዲስ ጅማሮን አላህ ሲሰጥህ የትናንቱን ብኩንነትና ስህተት አትድገም።


~🍂

በጊዚያዊ ስሜቶች ለሚያስተናግዱህ ሰዎች ክፍት ሁን ብዬ አልመክርህም። ሲፈልጉህ እላፊ ተጠግተው የነፍስ ዓለም የሚያደርጉህና ስትፈልጋቸው ደግሞ ሽታቸው የሚርቅህ ዓይነት ሰዎች ማለቴ ነው። እና እዚህ ዓይነት ብቻህን የምትፋለምበት ግንኙነት ውስጥ ሰላምም ህይወትም የለም። መራራቅ የማያደበዝዘው፣ መከራና ደስታን የሚጋራና መከታ የሚሆን ግንኙነት ውስጥ ራስህን ኢንቨስት አድርግ። ጓደኞችህንም  በመመርጥ ላይ እያልኩህ ነው።


አዋጅ ሰዎች ሆይ ንቁ!!
ኢማናችሁን ጀድዱ። አካላችሁን በስፖርት መንፈሳችሁን በዒባዳ አንፁ። ማንነታችሁን በዚክር ገንቡ። መጪው ጊዜ ከባድ የዕልቂት ዓመት ነው። በኢማን ብርሃን ጨለማውን የሚሰነጥቁ ሰዎች ብቻ ነጃ የሚወጡበት ዘመን!! አላህ ለጦርነት የፈጠራቸው ሙጃሂዶች እንጂ የማይድኑበት ወቅት

አዋጅ ሰዎች ሆይ ንቁ!!
ምድርና ሰማያት የተመሰረቱባትን ቃል አጥብቃችሁ ያዙ። ፍጥረታት ወደዚህ ምድር የመጡባት፣ ይቅጣጩበት ዘንድ ቂብላ የተተከለባት፣ የጂሃድ ሰይፎች የተመዘዙባት፣ የአላህ መብት በባሪያው ላይ ሁሉ የተደነገገባት ቃል!! ላኢላሀ ኢለላህ!! በእርሷ መንገድ ኑሩ በእርሷ መንገድ እንደፀናችሁም ሙቱ። ራሳችሁን ለመጪው ጊዜ አዘጋጁ።


የአክሱም ሙስሊሞች ጭቆና በአክሱማዊቷ የቁርአን መምህርት (ኡስታዛ)

📍ሐምሌ 1984 አክሱም ላይ ምን ተፈጥሮ ነበር?

📍ይህ ፅሑፍ "አክሱማዊቷ የቁርአን መምህርት" በሚል ነሐሴ 1985 ከታተመው ቢላል መፅሔት የተወሰደ ነው።

"በትግራይ ክልል፤ አክሱም ከተማ ውስጥ የከፍተኛ 2 ቀበሌ 05 ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሸምሲያ ሸህ ሷሊህ ለዲናችን መጠናከር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በቅርብ የመከታተል እድል አጋጠመኝና አርአያነታቸውን ላወሳችሁ ወደድኩ።

ወ/ሮ ሸምሲያ ሸህ ሷሊሕ ከሰላሳ አምስት በላይ ህፃናትን ቁርአን በማስቀራት ታላቅ ተግባር የፈፀሙ የሙስሊሞች መኩሪያ ናቸው። እኚህ ደርባባ ወ/ሮ ሲናገሩ ረጋ ያሉና ገፅታው የበራ ነው። ቁርአን ማስቀራት የመጀመራቸው ጉዳይ ከአባታቸው ጋር የተያያዘ ነው። አባታቸው ሸህ ሷሊህ ቁርአን ያስቀሩ ነበር። እርሳቸው ሲሞቱ የቁርአን ትምህርቱ ተቋረጠ። በዚህን ጊዜ በአካባቢው የሚገኙ ሙስሊሞች ወ/ሮ ሸምሲያን "ለምን አንቺ አታቀሪም? እርሳቸው ሳሉም ብዙውን ጊዜ የምታቀሪና ቁርአኑን በሉህ (አነስተኛ ጣውላ) የምከትቢው አንቺው አልነበርሽምን?" ብለው ወተወቷቸው። ወ/ሮ ሸምሲያም "እናንተ ከተቀበላችሁኝ ደስታዬ ነው" በማለት ልጆቹን ሰብስበው ማቅራት ጀመሩ። ቁርአንን ለማስቀራት የሚከለክል ምክንያት /ዑዝር/ ሲገጥማቸው አንጋፋ ተማሪዎቸቸው በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን እንዲያቀሩ ውክልና እንደሚሰጡ አውግተውኛል-በጣፋጭ አንደበት።

ወ/ሮ ሸምሲያ ቁርአን ማስቀራት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ [1980ዎቹ] ድረስ አያሌ ተፈታታኝ ችግሮች ገጥሟቸዋል። ከእነዚህም ውስጥ ጎላ ብለው የተፈታተኗቸውን እንዲህ ሲሉ አወጉኝ። "እንደምታውቀው እኛ የአክሱም ሙስሊሞች የግላችን ቤት አልነበረንም። ሀብታምም ይሁን ድሃ የአክሱም ሙስሊም የሚኖረው በኪራይ ቤት ነበር። ቤት ለመስራት አይፈቀድልንምና! ይህ በኋይለስላሴ ጊዜ የነበረ ጭቆና ሲሆን ደርግ መጣና ሙስሊም አክሱም ውስጥ ቤት እንዳይሰራ የሚከለክለውን እገዳ አንስቶ መሬት ሰጠን። ታዲያ በክራይ ቤት እኖር በነበረበት ጊዜ ልጆችን ሰብስቤ ቁርአን ሳቀራ አከራዮቼ "ቤታችንን የልጆች መሰብሰቢያ አድርገሽ ልታፈርሺብን ነው..." በማለት በማቅራቴን እንዳቆም ይጠይቁኝ ነበር። እኔ ግን ጥያቄያቸውን አልቀበል ብዬ ማቅራቴን እቀጥላለሁ። እነርሱም ከቤታቸው ያስወጡኛል። እንደገና ሌላ ቤት ተከራይቼ ማቅራቴን እቀጥላለሁ። ትንሽ ቆይተው እነዚህም ይቃወሙኛል። እንዲህ እያልኩኝ የግሌን ቤት እስካገኝ ድረስ ከሀያ ቤቶች ተባርሬያለሁ።

ይህን ካወጉኝ በኋላ የትዝታ ቅኝታቸውን ወደቅርቡ ዘመን መለሱት። እናም እንዲህ አሉኝ። "እንደምታስታውሰው ሐምሌ 1984 በአክሱም ሙስሊሞች ላይ የ"ክተት" አይነት ዘመቻ ተጠንስሶ ነበር። በዚያን ጊዜ እኔ ከሌሎች ሙስሊም ጎረቤቶቼ በበለጠ ተሳድጃለሁኝ። የዚህም ምክንያት ቁርአን የማቀራ ስለሆንኩኝ ነው። አልሐምዱሊላሂ ጎረቤቶቼ ጋር ተደብቄም ቢሆን ነፍሴን አትርፌአለሁ። ሆኖም ግን እኛን ለማጥቃት የተነሱት ሰዎች እቤቴ ድረስ ገብተው የማቀራበትን ቁርአን ቀደድው ሉሑን ሰባብረው ቤቴ ላይ ያለ እቃ አንድ እንኳ ሳይቀር ሰባብረውብኛል።

በውይይታችን መሀል "እስላም የሴቶችን የመማር እድል ይነፍጋል" የሚለው የአላዋቂዎች አሉባልታ ድንገት ትውስ አለኝና ነገሩን አጠገቤ ካሉት እንስት መምህር ጋር አስተያይቼው በውስጤ ሳቅሁኝ። እናም "ሴት አስተማሪ /ቁርአን አቅሪ/ በመሆንዎ የደረሰብዎት ችግር አለን" ብዬ ለወ/ሮ ሸምሲያ ጠየቅኋቸው።

"በእውነቱ ሴት አቅሪ በመሆኔ አንድም የደረሰብኝ ችግር የለም፤ እንዲያውም ብዙዎች ይደሰቱብኛል። ባለቤቴም ለዲኔ በማደርገው እንቅስቃሴ ፍፁም ደስተኛ ከመሆናቸውም ባሻገር አጥብቀው ያበረታቱኛል። እንዳውም አንዳንድ ጊዜ ህመም ቢጤ ጫን ሲለኝና ድካም ሲበረታብኝ ህፃናቱ እንዳይጉላሉና እንዳልጨነቅ ብለው እርሳቸው ያስቀራሉ።" አሉኝ።

ወ/ሮ ሸምሲያ ቁርአን በማቅራት ላሳለፏቸው ረዥም አመታት በእጅጉ እንደሚያስደስታቸው አውግተውኛል። "አየህ" አሉኝ በጣፋጭ አንደበታቸው "ሌሊቱን ታምሜ አድሬ ጠዋት ተማሪዎቼ ሲመጡ በሽታዬ ይለቀኛል። መቼም እነሱን በማቅራቴ የሚሰማኝን ደስታ እኔን አንድ አላህ ብቻ ነን የምናውቀው። "

እኒህ የተባረኩ ወ/ሮ በአሁኑ ጊዜ [1985] ከሁለት መቶ ህፃናት በላይ በግቢያቸው ውስጥ ያቀራሉ። ልጆቹን ሰብስበው የሚያቀሩት በግቢያቸው ውስጥ በሚገኝ ጥላ ቦታ ላይ ነው። ይህ ቦታ ጠንከር ያለ ፀሐይ እንዳያጠቃቸው የሚከላከልላቸው ቢሆንም ቅሉ ዝናብ በሚዘንብበት ጊዜ ለማቅራት አመቺ አይደለም። ወ/ሮ ሸምሲያ እንደነገሩኝ ከሆነ አላህ በጭድ የተሸፈነ ጣሪያ ቢጤ ያለው ቤት እንኳ የመስራት አቅም ቢሰጣቸው በእጅጉ ይደሰቱ ነበር። ትልቁ ችግርና ጭንቀታቸውም ከፀሐይና ከዝናብ የሚከላከል ጎጆ ቢጤ መቀለሱና ህፃናቱም ተመቻችተው የሚቀመጡበት ወንበር አለማግኝታቸው ነው። ወ/ሮ ሸምሲያ ለዲናችን ከሚያበረክቱት ታላቅ አስተዋጽኦ አኳያ ያለባቸውን ችግር ከጎናቸው ሆኖ መቅረፉ የአህለል ኸይሮችን ትኩረት የሚሻ ይመስለኛል። የሚመለከተውም ክፍል ችላ ሊላቸው አይገባም ባይ ነኝ። "

_
በነገራችን ላይ ኡስታዛ አላህ ረጅም እድሜ ሰጥቷቸው አሁኑም በአክሱም ከተማ በህይወት አሉ። ከአንድ አመት በፊት Nur Quran Bank Islamic Association / ኑር የቁርኣን ባንክ ኢስላማዊ ማህበር ወደ አክሱም ተጉዘው በነበሩ ጊዜ በኔ ጥቆማ ቤታቸው ድረስ ሄደው እንደዘየሯቸው እና በነብዩ ሙሐመድ ሰላዋት ሲያወርዱ ቀርጿቻዋል።




~

ይህ የምድራችን ትልቁ ፍጥረት የሆነው ሰማያዊ ዓሳ ነባሪ ነው። ቁመቱ 30 ሜትር ይደርሳል። ክብደቱ 180ሺህ ኪሎግራም ይመዝናል። ይህም በአማካኝ 33 ዝሆኖች ያህል ማለት ነው። ልቡ ብቻ ቁመቱ 1.5 ሜትር ሲሆን ክብደቱ 180ኪሎግራም ነው። የሰው ልጅ የልቡን ያህል እንኳን ክብደት የለውም። እንዲሁም በአንዱ የልቡ የደም ቧንቧ ውስጥ ገብቶ በሌላኛው መውጣት ይችላል።

ይህ ግዙፍ የአላህ ፍጥረት ታዲያ ጌታውን ከመታዘዝ አይኮራም። ሰው ግን ከሁሉም በላይ ነኝ ብሎ ይንጠባረራል።

አላህም እንዲህ አለ፦

«በምድርም ላይ የተንበጣረረክ ሆነህ አትሂድ። አንተ ፈፅሞ ምድርን አትሰረጉድምና። በርዝመትም ፈፅሞ ጋራዎችን አትደርስምና።»
(ኢስራዕ 37)


ካነበብኩት dan repost
🍃 ዱ ኒ ያ 🍂


👑          ⭐️             ⚡️
ٰ    • ○ ° 🌹🌹🌹• ○ °• ○ °• ○ °
 • ○    🌹🌹🌹🌹    • ○ °  👈አበባውን
• ○ °🌹🌹🌹🌹🌹           በመንካት• ○ °
  • 🌹🌹🌹🌹🌹🌹    ብቻ ምርጥ
○ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹    የሱና 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡  ° :.
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹         ያገኛሉ📡
 • 🌹🌹🌹🌹🌹      ° :.   * • ○       
• ○  🌿🌹🌹🌿      
  • ○ °   🌿🌿            👈
     •        🌿   • ○ °        🌿🌿
 • ○ °        🌿     • ○ ° 🌿🌿🌿
   • ○ °         🌿       🌿🌿🌿🌿
    • ○ °          🌿  🌿🌿🌿🌿🌿
        • ○ °       🌿   🌿🌿🌿🌿
      • ○ °         🌿  🌿🌿🌿
          • ○ °     🌿  🌿° :. * • ○
         °• ○ °      🌿° :.   * • ○
                    🌿° . °☆  . * ● ¸
.    ★  🌿° :.   * • ○ °
        ° .     🌿. * ● ¸
                  🌿       በቀላሉ ይቀላቀላሉ ።
☆  . * ● ¸ .
★ ° . *   ° . °☆  . * ● ¸
.    ★  ° :.   * • ○

🅰️🅰️🅰️⭐️✅🔗🔡🔡🔡
ለተጨማሪ ሀሳብ አስተያየት  ጥቆማ
@twhidfirst1 ⭐️🔗🔡🔡🔡



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.