ጀነት እንገናኝ
〰〰〰〰
ክፍል ስምንት
〰〰〰〰
«አዎን በርግጥ ጥሩ ትዕግስትን ታገሰ ጌታዉንም አብዝቶ አመሰገነ ’ አለኝ። ይህንኑ ጥያቄ ስደጋግምበት ‘ እባክህ አሣጥር ’ አለኝ። እኔም ‘ እንግዲያዉስ ለፍለጋዉ የላክሀኝ ልጅህ አዉሬ በልቶት በደለል መሃል ወድቆ አግኝቼዋለሁ ። አላህ ምንዳህን ያብዛዉ ትዕግስትንም ያልብስህ ’ አልኩት ።
እሱም ‘ ምስጋና ከዝርያዬ መካከል በእሣት የሚቀጣዉን በሱ የሚያምፅን ሰዉ ላልፈጠረዉ ጌታ ይሁን ’ አለና በማስከተልም ‘ ኢና ሊላህ ወኢና ኢለይህ ራጂዑን ’ እንዳለ ነፍሱ ወጣች ።
«እኔም ባጋጠሙኝ ተደራራቢ ችግሮች ምክኒያት .. ኢናሊላህ ወኢና ኢለይህ ራጂዑን .. አልኩኝ። ዐይኔ እያየ ስለሞተዉ ሙስሊም ወንድሜም ሀሣብ ገባኝ ። እዚህ ትቸዉ ብሄድ አዉሬ ይበላዋል። እንዳልቆይ ደግሞ ለራሴም ምንም በእጄ የሌለኝ ደካማ መንገደኛ ነኝ ።
ለብሷት በነበረዉ ልብስ ከፈንኩት። ከራስጌዉ አጠገብ ቁጭ ብዬ በማልቀስ ላይ እንዳለሁ ድንገት የሆኑት ሰዎች መጡ።‘ ምን ሆነህ ነዉ ? ምን አጋጠመህ ’ አሉኝ ። ሁኔታዬንና የሰዉየዉን ሁኔታ ሁሉ አጫወትኳቸዉ። ከዚያም እስቲ ግለጥና ፊቱን እንየዉ አሉኝ። ሰዎቹ የሰዉየዉን ፊት ባዩ ጊዜ ወድቀዉበት በሽሚያ አንዴ ግንባሩን አንዴ ዐይኑንና እጁን እያፈራረቁ ይስሙበት ገቡ ። እንዲህ እያሉ ....
‘ ይህ እኮ አላህ ሀራም ካደረገበት ነገር እይታዉን የሰበረ ዐይን ነዉ ! ይህ እኮ ሰዎች በሚተኙበት የለሊት ሰዓት ተነስቶ ጌታዉን ማመሰገን ያዘወትር የነበረ ሰዉነት ነዉ ። ’
‘ ማን ነዉ እሱ አላህ ይዘንላችሁና ’ አልኳቸዉ ።
‘ ይህ ሰዉ አቡቁላባ አልጁረሚይ ይባላል። የታላቁ ሰሃባ የኢብን አባስ የቅርብ ጓደኛ ነዉ ። አላህንና ረሱሉን ሰለላሁ ዐለይህ ወሰለም አብዝቶ በመዉደዱ ይታወቃል ። ’ አሉኝ ።
«አጠብነዉና በእጃችን ባገኘናቸዉ ልብሦች ከፈንነዉ ። ሰግደንበትም ቀበርነዉ ። ከቀብሩ ፍፃሜ በኋላ ሰዎቹ ወደየጉዳያቸዉ ተመለሱ።እኔም ወደ ጥበቃ ሥራዬ ሄድኩኝ ። በመሸ ጊዜም ለእንቅልፍ ጋደም አልኩኝ ።በህልሜም አቡቁላባን የጀነት ልብስ ለብሶ በጀነት ጨፌዎች ዉስጥ እየተዘዋወረ ‘ ሰላሙን አለይኩም ቢማ ሰበርቱም ፈኒዕመ ዐቅበዳር የሚለዉን የቁርዓን አያት እያነበበ አገኘሁት ።
‘ ሰላሙን ዐለይኩም ቢማ ሰበርቱም ፈኒዕመ ዑቅባ ዳር
“ በናንተ ላይ ሰላም ይስፈን የመጨረሻዉ ዓለም ፍፃሜያችሁ እጅግ ያማረ ሆነ ! ” ( 13፡24 )
ተጠግቼዉ ‘ የባለፈዉ ወዳጄ አይደለህምን ? ’ አልኩት እሱም
‘ አዎን ነኝ ’ አለኝ ።
‘ ይህ ሁሉ ላንተ ነዉ ወይ ? ’ ስል ጠየቅኩት
እሱም እንዲህ ሲል መለሰልኝ --- አላህ ለእዉነተኛ ባሮቹ ያዘጋጃቸዉ ምርጥ የጀነት ደረጃዎች አሉ። እነዚያም ደረጃዎች ሊገኙ የሚችሉት እንዲሁ በቀላሉ አይደለም ። በችግር ጊዜ ትዕግስትን በመላበስ ፣ በድሎት ጊዜ አላህን አብዝቶ በማመስገን እና በስዉርም ይሁን በይፋ አላህን በመፍራት እንጂ ። ’ አለኝ ።
ኢብተስም ሊልሀያት ~
ዛሬ ብቻ ነው ቀናችን!
«የዚህችን ዓለም ዋጋ ከማንም በላይ ጠንቅቀዉ የሚያዉቁት ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይህ ወሰለም አንድ ቀን እግር በእግር እየተከተለ ሱናቸዉን የሚቃርመዉን ታላቁን ሰሃባ አብዱላህ ኢብን ዑመርን ትከሻቸዉን ያዝ በማድረግ…. ‘ በዱኒያ ላይ እንደ ባይተዋር እንግዳ ወይንም እንደ መንገደኛ ሁን ’ አሉት ። ከዚያች የረሱል ሰለላሁ ዐለይህ ወሰለም መልዕክት በኋላ ይህ ሰሃባ ላገኘዉ ሰዉ ሁሉ “ ካመሸህ ንጋትን አትጠብቅ ። ካነጋህ ደግሞ ምሽትን አትጠብቅ ” በማለት ያስጠነቅቅ ነበር ። ከበድና ጠለቅ ያለ ትርጉሙን ትተን የሰሃባዉን ንግግር ውጫዊ መልዕክት እናጢን ብንል ‘ በሰላም አንግተህ ከሆነ ስለ ማምሸትህ ዋስትና የለህም ። በጤና ካመሸህ ደግሞ ስለ ማንጋትህ እርግጠኛ አይደለህምና በቀንም ሆነ በምሽት በደቂቃና ሴኮንድ ጊዜዎች ውስጥ ለወደፊቱ ህይወትህ ለአኪራህ በብርቱ ስንቅ ለማይቀረዉ ጉዞ ተዘጋጅ ’ እንደማለት መሆኑን እንረዳለን ።
እስቲ ከልብ እናስተዉል ። ስንቶች አሉ በሙሉ ጤናና በእግር ተራምደዉ ከቤት ወጥተው በቃሬዛ የተመለሱ ! ስንቶችስ ናቸው በሰላም ከመኝታቸዉ ተጋድመዉ ዳግም ሣይነሱ በዚያው ለዘላለሙ ያሸለቡ ! ስንቶች ናቸዉ መጣን ብለዉ ሄደዉ በዚያዉ የቀሩ ! ሰው ከዚህች ዓለም የሚሰናበትባትን ቀን ሰዓት ደቂቃም ሆነ ሰከንድ አያውቅም ። የሰዉ ልጅ በማንኛውም ቅፅበት የሚመጣ ረጅም እቅዱንና ሰፊ ምኞቱን የሚያሰናክልበት ድብቅ ነገር ‘ ሞት ’ የሚባል ክስተት አለበት ።
ሰው ከአሁኑ ቁርጡን አዉቆ የዱኒያ ላይ ምኞቱን ካላሳጠረና አጀሉን ወደራሱ እጅግ በጣም አቅርቦ ካልተመለከተ በቀር ለአኪራ ከመዘጋጀት መስነፍ መዘናጋቱ የግድ ነው ። ውጤታማ የሆነ ስራ ለመስራትም ይቸግረዋል ። የአጀልን ነገር ከአላህ ቃል የተገነዘቡት ከጎረቤትም ሆነ ከቤት አካባቢያቸው በተግባር ያዩት ቀደምቶቹ ሰለፎች ሰለ ዛሬዋና ስለአሁኗ ጊዜ እንጅ ስለ ወደፊቱ ቀናት ጭንቀት አልነበራቸውም ።
ለዚህም ለዛሬዋ ዕድሜያቸው እጅጉን ይሳሳሉ ። ደቂቃን ቆጥበው ሰከንድን መንዝረው የዛሬ ሰው ሙሉ ቀኑን ቢሰራ ከሚሰራው ሥራ በላይ ምንዳ ያለው ነገር ይሰራሉ ። ህይወትን ካልተሻሻሉባት ዕድሜን በየቀኑ ወደ አላህ ካልቀረቡባት በነሱ ዘንድ ትርጉም አልባ ናት ። አንሳሳት - ቀናችን በእጃችን የገባው የዛሬው ቀን እንጅ ከእጃችን የወጣው የትናንትናዉ አይደለም ። ነገም ቢሆን የኛ ስለመሆኑ የምናዉቀዉ ምንም ነገር የለም ። ከእጃችን አልደረሰም ጣዕም የለው ሽታ የለው ። ማሰብ መጨነቃችን ለዛሬው ቀን ብቻ ይሁን።
« በዛሬ ውስጥ ተወልዶ ዛሬን ብቻ ኖሮ ዛሬውኑ እንደሚሞት ሰዉ ኑሮን እንኑር ። ዛሬውኑ መልካም የተባለን ስራ ሁሉ እንሥራ ። ለዱኒያችን እንሯሯጥበት ፡፣ ለአኪራችን እንሰንቅበት ፣ አላማችንን እናሳካበት ፣ ዲናችንን እንወቅበት ፡ ኢማናችንን እናበልፅግበት ። ዛሬን ብቻ በዱኒያ ላይ የመጨረሻዋን ሶላት እንደሚሰግድ ሰው ሶላትህን አሳምረህ ስገድ ። ከዛሬ በቀር የመፆምን ዕድል እንደማያገኝ ሰው ለፆምህ ተጠንቀቅለት ። ዛሬ ብሦቱን አውጥቶ የለመነህን ችግረኛ የነገ ቀን ያንተ ስለመሆኑ ሳታዉቅ ነገ ተመለስ ብለህ አታባርረዉ ። ለቀጠርከው የተውባ ቀን ስለመድረስህ እርግጠኛ አይደለህምና ዛሬውኑ ሙሉ በሙሉ ከወንጀል ተነቀል ።
ዛሬውኑ መልካም የተባሉ ነገሮችን ሁሉ ስራ .. ኒያህን አሳምር ፣ መስጊድ ግባ ፣ ቁርዓን ቅራ ፣ አላህን ፍራ ፡ ዛሬውኑ ወጥን ዛሬውን ጀምር ለነገ አትቅጠር ። ነገ ብለው ለነገ ያልደረሱ ብዙ አሉ ፡ ነገ ማለትን የሚያበዙ ዘወትር ነገ እንዳሉ ይኖራሉ ፡ ዛሬ አልፎ በነገ ቢተካም ነገም ነገ ማለታቸው አይቀርምና ‘ ሰዉ ’ ሳይሆኑ ይህቺን ዓለም ይሰናበታሉ ። ዛሬውኑ እውነተኛ ማመንን በአላህ እመን ፡ ቀደርን ከልብ ተቀበል ፣ የአላህን ክፍፍል ውደድ ስራውን ሁሉ አመስግን ። ዛሬውኑ መጥፎ ፀባይህን አሻሽል ፣ ከወንጀል ተጠንቀቅ ፣ ለአኪራህ ሰንቅ ፣ አጀልህን ጠብቅ ።
የምኖረው ዛሬን ብቻ ይሆን ይሆናል ብለህ አስብና መልካም ወደ ተባሉት ነገሮች ሁሉ ፍጠን ። ከታዘዝክበት ተገኝ ፣ ከተከለከልክበት ተከልከል ፣ግዴታህ የተደረገብህን ተወጣ ፣ ከሱናውም ጨማምር ጀመዓን አዘውትር ፣ ወንድም እህቶችን አክብር ። ዛሬን እንደ......
ይ .........!
https