አንዲት የቆቅ ልጅ የስንዴ እሸት ትርክክ ብሎ በስሎ በሚገኝበት እርሻ አጠገብ ወጥመድ ተጠምዶ አይታ እናቷን እናቴ ሆይ እሸት አምሮኝ ነበር ከዚህ ማሳ ገብቼ እንዳልበላ ወጥመድ ተጠምዷል ምን ይሻለኛል አለቻት ።
እናቷም ተይ ልጄ ይቅርብሽ ትያዣለሽ አይሆንም ብላ መከረቻት
ልጅቷ ግን ግዴለሽም እማዮ የለም አይዘኝም ትንሽ ተክ ተክ አድርጌ ልውጣ አለቻትና ገብታ ስትበላ እናቷ እንደፈራችው እግሯን ጥርቅም አድርጎ ያዛት
መቼም መከራ ሲመጣ ለእናት አደል የሚዋየው የእናቷን ምክር አልሰማ ያለቺው እረናቴ ተያዝኩልሽኮ አለቻት ምነው ልጄ አስቀድሜ ነግሪሽ አለነበርምን አሁን ምን ላርግልሽ እችላለሁ ብላ መለሰችላት
እማዮ እባክሽን ፍችልኝ ?
በምን እጄ ልጄ
ታድያ እንዴት ልሁን ምን ይበጀኝ እማዮ ?
በዚህ ግዜ እናት ለልጇዋ ምርጥ መካሪይ ስለሆነች እንዲህ አለቻት ዝም ብለሽ የሞትሽ መስለሽ ተኚ ከዛ ባለወጥመዱ ሲመጣ ሞታለች ብሎ ፈቶ ይለቅሻል አለቻት ።
ያ ባለወጥመድ ሰው ፣ ሰብሉን ጉብኝቶ መጣና ቢመለከት ዝልፍልፍ ብላ ተኝታ ዐይኗን አጨልማ አገኛት ።
እሱም የሞተች መሰለውና እዮ ጉዴ ወጥመዴ ቆቅ ይዞልኝ ነበር ነገር ግን በክታለች እያለ አዘነ ።
ጓደኛው ከበላዩ ሰብል ይጠብቅ ነበርና ወንድም ብሎ ተጥርቶት ወጥመዴ ቆቅ ይዞልኝ ነበር ነገር ግን በክታ አገኘሃት አለና ነገረው ባልንጀራውም እስቲ ወደ ላይ አጉናት አለው እሱም እያት አለና ።
ወደ ሰማይ ወርወር ቢያደረረጋት ቱር ብላ ከጫካዋ ጥልቅ አለች ይባላል ።
ወላጆቻችን በአስተሳሰብ በሁሉም ነገር ከኛ የበለጡ ናቸውና ከወላጅ ምክርና ተግሳጽ አንውጣ ።