Muhammed Mekonn dan repost
🔷 ተውሒድና ሱና ሐራ ላይ
🔎 ውድና የተከበራችሁ ወንድምና እህቶች ሐራ ማለት በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ከወልዲያ 24 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኝ ከተማ ናት። እቺ ከተማ በሰሜኑ ክፍል ከእስልምና የሚያወጣ ሽርክ በሚከናወንባቸው ቦታዎች የተከበበች ነች። ከእነዚህ ውስጥ ዳናና ከረም በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። እንደሚታወቀው በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ያሉ የቀብር አምልኮ ቦታዎች ሰዎች ከየቦታው ሲተሙና በቀብር ዙሪያ ሲርመሰመሱ ማየት የተለመደ ነው። ወደ ዳናና ከረምም ይኸው ነበር እየሆነ የነበረው። ብዙ ሰዎች (ሙስሊሞች) ችግራቸውንን፣ መከራቸውን፣ ማጣታቸውን፣ መሀን መሆናቸውን (ዘር ማጣታቸውን)፣ ድህነታቸውን፣ ከጠላት የሚደርስባቸውን ግፍና በደላቸውን ለመንገርና መፍትሄ ፍለጋ እየመጡ ፍፁም በሆነ መተናነስና ራስን ዝቅ በማድረግ ችግራቸውን ዘርዝረው መፍትሄ ካገኘን ይህን እናደርጋለን በሚል የተለያየ ስለት አድርገው መፍትሄ አገኘን እያሉ ከአላህ ውጪ ላለ አካል እየተንበረከኩ፣ እየሰገዱ፣ እየዳሁ እየሄዱ ስለታቸውን የሚያደርሱባቸው ቦታዎች ናቸው።
➲ ያሻውን ሰሪ ብቻውን ቀሪ የሆነው አላህ ይህን ታሪክ ቀይሮ የተውሒድና የሱና ባልተቤቶች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተውሒድና ሱናን ፍለጋ ወደ ሐራ እንዲተሙና በመስጂድ አስሰፋ ዙሪያ እንዲርመሰመሱ አድርጓል። ወደ ዳናና ከረም መውሊድ ሲሄዱ የነበሩ ግመልና በጎች ወደ ተውሒድ ጥሪ ማእከል ወደ ሰፋ መስጂድ እንዲነዱ አድርጓል!!! ሐራ ከየቦታወ በተመሙ የተውሒድ ሰራዊቶች ትንፋሽ አጥሯት ተጨናንቃለች። ከሰፋ መስጂድ በሚወጣው የተውሒድና ሱና መአዛ አካባቢዋ ታውዶ ይገኛል ። የሰፋ መስጂድ ስፋት በተራ ጊዜ መጥቶ ላየው ማን ሊሰግድበት ነው በዚህ መልኩ ተዘርጥጦ የተሰራው ያስኛል። አንድ ጥግ ቁጭ ያለ ሰው ሌላኛው ጥግ ላይ ያለው ማን እንደሆነ መለየት አይችልም። ከመሆኑም ጋር አሁን ግን እግር ማስቀመጫ በማይገኝበት ሁኔታ በተውሒድና ሱና ናፋቂ ሰለፍዮች ተጨናንቋል። የመስጂዱ ጊቢ ስፋት አንድ ቀበሌ ነው እንዴ ያሰኛል። በከተማዋ መሀል ዋና መንገድ ላይ ነው የሚገኘው።
✅ የሐራ መስጂድ አሁን ያለበት ሁኔታ ይህን ሲመስል ከተወሰኑ አመታት በፊት ድቤ የሚደለቅበት፣ ወንድና ሴት ተቀላቅሎ የሚጨፍርበት፣ በጋጃ አድሩስ አየተጨሰ ጫት የሚቃምበት፣ መውሊድ የሚከበርበት መስጂድ ነበር። ይህን ያደርጉ የነበሩት የዳና ሙሪዶች ነበሩ። መስጂዱን ያሰራው አንድ ወደ ሱና የቀረበ ሰው እንደበርና ሰርቶ ሲጨርስ ወሀብይ ነህ ተብሎ ወደ አካባቢው እንዳይደርስ እንደ ተደረገ ነው የሰማነው። የሚያሳዝነው አሁን በህይወት የሌለና ይህን የአላህ ተአምር አለማየቱ ነው። አላህ ይዘንለት አላህ የጀነት ያድርገው ። መስጂዱ ከዛ የሽርክና የቢዳዓ ማእበል ወጥቶ ወደ ተውሒድ እንዲቀየር ሰበብ የሆኑት ከአላህ ቶፊቅ በኋላ ሸይኻችን ሸይኽ ሙሐመድ ሐያት ናቸው። የአካባቢው ወጣት ከሳቸው ጎን ቆመው መሳሪያ ተማዞ ነው ወደ ተውሒድ መስጂድነት የተቀየረው። አላህ እሳቸውንም እኛንም በተውሒድና ሱና ላይ ፀንተን ኖረን በዛ ላይ ሞተን በዛ ላይ የምንቀሰቀስ ያድርገን።
♻️ ይህ ካለው ሁኔታ አንፃር በጣም ጥቂት ማሳያ ነው። አላህ ይህን ሳያሳየኝ ስላልገደለኝ ለሱ የሚገባ ምስጋና ይገባው እላለሁ።
የጌታውን ምህረት ከጃይ ደካማ ባሪያው ወንድማችሁ ባህሩ ተካ።
https://t.me/bahruteka
ለትውስታ