[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ!
በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ!
ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ!
ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ረመዷን ብዙዎች ተውበት የሚያደርጉበት ወር ነው!
መስፈርቶቹስ?
—————
የሰው ልጅ ከስህተት የፀዳ አይደለምና እኛስ መች ነው ወደ አላህ ከልባችን ቁርጥ ያለ ተውበት አድርገን ከወንጀላችን የምንመለሰው???
በተለያዩ ወንጀሎች ውስጥ ተዘፍቀው ለሚገኙ ባሮቹ ሁሉ አዛኙና መሃሪው አምላካችን አላህ እንዲህ እያለ ይጠይቃል:-

﴿أَفَلا يَتوبونَ إِلَى اللَّهِ وَيَستَغفِرونَهُ وَاللَّهُ غَفورٌ رَحيمٌ﴾ الماءدة ٧٤

ወደ አላህ ተፀፅተው አይመለሱምን? ምህረትን አይለምኑትምን?፣ አላህ መሃሪ አዛኝ ነው።” አል-ማኢደህ 74

ዛሬ ነገ ሳንል ካለንበት ግልፅ ከወጡም ሆኑ ከድብቅ ወንጀሎች ወደ አላህ በቁርጠኝነት መስፈርቱን አሟልተን ልንመለስ ይገባል!፣ ሞት መምጫው ምስጢር ነው፣ መች በተዘናጋንበት ፈጥኖ እንደሚመጣ አናውቅም!፣ ሞት ድንገተኛ ፈጥኖ ደራሽ ነው፣ ኑዛዜያችን እንኳን አስተካክለን ሳንናዘዝ በድንገት ህይወታችን ከሰውነታችን ልትላቀቅ ይችላልና ቶሎ ወደ አላህ በቁርጠኝነት ልንመለስ ይገባል!!።

ከወንጀል ወደ አላህ ተፀፅቶ ለመመለስ (ለተውበት) ጠንካራና አይቀሬ የሆኑ 5 መስፈርቶች አሉት። ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንደሚከተለው አስቀምጠዋቸዋል:-

ለአላህ ብሎ ኒያን በማጥራት (በኢኽላስ) ወደ አላህ ተፀፅቶ መመለስ ነው።
ኢኽላስ አምልኮን ለአላህ ብሎ ጥርት አድርጎ መፈፀም ለሁሉም የአምልኮ ዘርፍ መስፈርት ነው። ከወንጀል ወደ አላህ ተፀፅቶ መመለስ ደግሞ ከአምልኮ ዘርፎች አንዱ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል:-

﴿وَما أُمِروا إِلّا لِيَعبُدُوا اللَّهَ مُخلِصينَ لَهُ الدّينَ حُنَفاءَ﴾ البينة ٥

አላህን ሀይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ሆነው እንዲገዙት እንጂ በሌላ አልታዘዙም።” አል-በይነህ 5
ሰዎች እንዲያዩለት ወይም ደግሞ አላህን አልቆና ፈርቶ ሳይሆን (የሸሪዓ ሀገር ሆኖ) በባለ ስልጣኖች ቅጣት እንዳይደርስበት ፈርቶ ተውበት ያደረገ ከሆነ ተውበቱ ተቀባይነት የለውም!።

በፈፀመው ወንጀል ላይ ተፀፃች መሆን አለበት።
አላህ ያዘዘውን ነገር ባለ መፈፀም ከነበረ ወንጀል የሰራው፣ ሀያል የሆነው የአምላኩን አላህን ትእዛዝ ባለ ማክበሩ ሊቆጭና ሊፀፀት ይገባል። አልያም አላህ የከለከለውን ነገር በመፈፀም ከሆነ የተገበረው መተው እየቻለ ፈጣሪውን አላህን በማመፁ የአላህን ሀያልነት በማስታወስ እርሱ ፊት ቆሞ እንደሚጠየቅ በማስታወስ ሊቆጭና ልቡ ሊሰበር ይገባል።

ተፀፅቶ ከተመለሰበት (ተውበት) ካደረገበት ወንጀል ሙሉ በሙሉ መላቀቅ አለበት።
የፈፀመው ወንጀል ግዴታ የተደረገበትን ነገር አለመፈፀም ከነበር ያንን ነገር ሙሉ በሙሉ መፈፀም። ለምሳሌ:- አንድ ሰው ወንጀል የሰራው ዘካ በመከልከል ከነበረ ዘካውን በአግባቡ ያለፈውንም ጭምር አስቦ መስጠት ተውበቱ ተቀባይነት እንዲኖረው ግዴታ ይሆንበታል። ወይም ስርቆትን የመሰለ ሀራም ነገር የተገበረ ከሆነ ተውበቱ ተቀባይነት እንዲኖረው የሰረቀውን ገንዘብ ለባለቤቱ መመለስ አለበት። ተውበት ባደረገበት ወቅት የሚመልሰው ገንዘብ ከሌለው ሲያገኝ መመለስ ይጠበቅበታል። ባለቤቱ ከሌለ ለወራሾቹ፣ ወራሽ ዘመድ ከሌለው ለሙስሊሞች የገንዘብ ግምጃቤት (ለበይተል ማል)፣ የሙስሊሞች ግምጃቤት (በይተል ማል) ከሌለ ሙሉ ገንዘቡን ሶደቃ ያደርግለታል። ገንዘቡን ለባለቤቱ በአካል መስጠቴ ለሌላ አደጋ ሊያጋልጠኝ ይችላል ብሎ ከፈራ፣ በሌላ በማያሰጋው መንገድ በተዘዋዋሪ አድርጎ መመለስ ግዴታ ይሆንበታል።

ተውበት ካደረገ በኋላ፣ ተውበቱ ተቀባይነት እንዲኖረው፣ ተውበት ወዳደረገበት ወንጀል ላለመመለስ ቁርጥ ያለ አቋም መያዝ ግዴታ ይሆንበታል።

አንድ ሰው ከወንጀሉ ወደ አላህ ተፀፅቶ (ተውበት) አድርጎ የሚመለስበት ወቅት ተውበቱ ተቀባይነት የሚያገኝበት ወቅት መሆን አለበት። ይህ ማለት ሁለት ተውበት ተቀባይነት የማያገኝበት የተለያዩ ጊዜዎች አሉ፣ እናም በነዚህ ጊዜያት መሆን የለበት። እነሱም:- 1, በሰውዬው በራሱ ብቻ የተገደብ ጊዜ ነው፣ እርሱም የሞት ገርገራ ላይ ከሆነ ተውበቱ አይጠቅመውም። 2, ሁሉንም ሰው አካታች የሆነ ጊዜ ነው፣ እርሱም ፀሃይ ከገባችበት የምትወጣበት ጊዜ ነው፣ በዚህን ጊዜ የሚደረግ ተውበት ለማንም አይጠቅምም።” [ሸርህ አል-አርበዑን አንነወዊየህ ኢብኑ ዑሰይሚን 1/417]

ለእነዚህ መስፈርቶች ሸይኹ ኪታባቸው ውስጥ ማስረጃ ያስቀመጡ ሲሆን፣ እኔ ግን ከጊዜ አንፃር ለማሳጠር ብዬ ነው ማስረጃዎችን ያልጠቀስኳቸው፣ ማስረጃዎችን ማየት የፈለገ በተጠቀሰው ገፅ ከኪታቡ ማየት ይችላል።

በዚህ ጊዜ እየታየ ያለው ትልቁ ችግር ብዙ ሰዎች ረመዷን ሲገባ ብቻ ተውበት ያደርጉና ከረመዷን በኋላ ግን ወደዚያው ሲመለሱ ይስተዋላል። ይህ ከባድ የሆነ አደጋ ነው!፣ ወንጀሉንም ሙሉ በሙሉ አያስምርለትም። ታጥቦ ጭቃ ከመሆንም አላህ ይጠብቀን!!

ሸይኹ'ል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
በረመዷን ወር ብቻ ወንጀልን በመተው ላይ ቁርጥ አቋም የያዘ ሰው፣ ከረመዷን በኋላም ያለውን ጊዜ ያላካተተ ከሆነ፣ ይህ ጥቅል በሆነ መልኩ ተውበት አድራጊ አይደለም። ነገር ግን በረመዷን ውስጥ ይህን ወንጀል ከመፈፀም ተቆጥቧል፣ ይህን ያደረገው ለአላህ ብሎና የእርሱን ህግጋት (የእስልምናን እሴት) በማላቅ ከሆነ፣ ይህን ጊዜ በማክበር እርም የተደረገበትን በመተው፣ በዚህ ተግባሩ ብቻ ነው አጅር የሚያገኘው። እንጂ እርሱ ከነዚያ ሙሉ ተውበት ከሚያደርጉትና ሙሉ ተውበት በማድረጋቸው ጥቅል በሆነ መልኩ ወንጀላቸው ከሚተውላቸው (ምህረት) ከሚደረግላቸው ሰዎች አይደለም።
[መጅሙዕ አል-ፈታዋ 10/744
✍🏻ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa




‏صورة من حسين عبد الله


አልበያን መስጂድና መድረሳ (የቡታጅራ) የገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ ከቡታጀራ አልበያን መስጅና መድረሳ

በአለም ዳርቻ በቅርብም በሩቅም የምትገኙ አህለል ኸይሮች ዛሬ በጣለው መለስተኛ ዝናብ በቡታጀራ ከተማ የሚገኙ ምእመናኖች
በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል

በምስሉ እንደ ምትመለከቱት ከባድ ዝናብ ቢጥል ምንአክል ጉዳት እንደሚደርስ መገመት ይቻላል

በኣሁኑ ጊዜ ምንም እንኳን በሰለፊዮች ችግር ቢበረታም በቡታጀራ ሰለፊዮች የደረሰው በደል ተወዳዳሪ የለውም

ይሀውም ማረፊያ ቦታ በማጣት ተከራይተውም ጭድ ነስንሰው በሚሰግዱበትና በሚቀሪበት ቦታ ለሰለፊያ ጠሊታ በሆኑ ሰዎች እንግልታ በሉበት ሁኔታ በምስሉ ለምትመለከቱት ተዳርገዋል

በመሆኑም ከምንም በማስቀደም ለእኚህ ብርቅዬ ሰለፊዮች ልንደርስላቸው ይገባል

ሼር በማድረግና እጃቹ የያዘውን እንድታበርክቱ በኣሏህ ስም እንጠይቃቹሃለን


المؤمن للمؤمن كالبنيان


مثل المؤمنين في توادهم وتعاطفهم وتراحمهم كمثل الجسد الواحد إذا اشتكى منه عضو تداعى له سائر الجسد بالسهر والحمى

1000571575063
የመስጅዱ አካውንት

https://t.me/albeyanbutajiragroup?videochat=ebdbd2b7999c899de4


↪️ በፆመኞች ጨፌ ክፍል ⑤

في رياض الصائمين
[الحلقة الثانية من عجائب قدرة الباري خلق الإنسان]


📝 ከፈጣሪያችን ገራሚ ችሎታ ውስጥ የሰው ልጅን መፍጠሩ ነው!

🎙🎙 ዶክተር ሸይኽ ሑሰይን ሙሐመድ አስ’ሲልጢይ አላህ ይጠብቃቸው

👂በደምብ ይደመጥ


القناة الرسمية التابعة والمعتمدة للشيخ حسين السلطي حفظه الله
https://t.me/HussinAssilty


🟢መልእክት ለቁርኣን ቃሪኦች

*[ يا قارئ القرآن لاتكن من الذين يتعجلون بالقرآن ولا يتأجلونه]*

أخرج أبو داود في سننه عن جابر -رضي الله عنه- قال: خرج علينا رسول الله -صلى الله عليه وسلم- ونحن نقرأ القرآن، وفينا العربي والأعجمي، فقال: ((اقرءوا فكل حسن، وسيجيء أقوام يقيمونه كما يقام القدح يتعجلونه ولا يتأجلون)) 
صححه الشيخ الألباني في
الصحيحة(٢٥٩ )
والشيخ مقبل في الصحيح المسند(٢٣٦)

قال صاحب عون المعبود رحمه الله

*[ يقيمونه ]* أي يصلحون ألفاظه وكلماته ويتكلفون في مراعاة مخارجه وصفاته.

*[ كما يقام القدح]* أي يبالغون في عمل القراءة كمال المبالغة لأجل الرياء والسمعة والمباهاة والشهرة.

*[ يتعجلونه ]* أي ثوابه في الدنيا.

*[ ولا يتأجلونه ]* بطلب الأجر في العقبى بل يؤثرون العاجلة على اﻵجله ، ويتأكلون ولا يتوكلون. انتهى

*قال العلامة المحدث مقبل الوادعي* رحمه الله
وفيه علم من أعلام النبوة فقد كثر المتأكلون بالقرآن.


https://t.me/Menhaj_Alwadih

القناة الرسمية التابعة والمعتمدة للشيخ حسين السلطي حفظه الله
https://t.me/HussinAssilty


መንሀጅን በተመለከተ ጠንከር ያሉ ምክር አዘል ንግግሮች!

* قال ﺍﻟﻌﻼﻣﺔ ﺍﻟﻤﺤﺪِّﺙ ﻣﻘﺒﻞ ﺍﻟﻮﺍﺩﻋﻲ - ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ تعالى -

”ﻓﺎﻟﺪﻋﻮﺓ ﻋﻨﺪﻧﺎ ﺃﻋﺰ ﻣﻦ ﺃﻧﻔﺴﻨﺎ ﻭﻣﻦ ﺃﻫﻠﻴﻨﺎ  ﻭﺃﻣﻮﺍﻟﻨﺎ ﻭﻣﺴﺘﻌﺪﻭﻥ ﺃﻥ ﻧﺄﻛﻞ ﻭﻟﻮ ﺍﻟﺘﺮﺍﺏ ﻭﻻ ﻧﺨﻮﻥ ﺩﻳﻨﻨﺎ ﻭﺑﻠﺪﻧﺎ ﻭﻻ ﻧﺘﻠﻮﻥ ﺍﻟﺘﻠﻮﻥ ﻟﻴﺲ ﻣﻦ ﺷﻴﻤﺔ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﺴﻨﺔ“اﻫـ .

* የየመኑ ሊቅ ሙቅቢል አል-ዋዲዒይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦

«ዳዕወቱ-ሰለፊያ እኛ ዘንድ ከነፍሳችን፣ ከቤተሰቦቻችን እና ከንብረቶቻችን በላይ ናት። (ብናጣ) አፈር ለመብላት ዝግጁ ነን። ዲናችንን አንከዳም። ሀገራችንን አንከዳም። አንቀያየርም። መቀየያር ከሱና ሰዎች መገለጪያ አይደለም።»

ﺍﻟﺒﺎﻋﺚ ﻋﻠﻰ ﺷﺮﺡ ﺍﻟﺤﻮﺍﺩﺙ ص ٥٧.

* وقال العلامة ابن العطار - رحمه الله:

”لا بد من البيان وعدم الكتمان وإظهار الحق وتبيين الكذب من الصدق والله تعالى يعلم المفسد من المصلح والملبس من الموضح“ اﻫـ .

* ኢብኑል ዐጣር የተባሉት እውቁ ሊቅ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦

«(ሀቅን) ግልፅ ማድረግ፤ አለ-መደበቅ ግዴታ ነው። ሀቅን ፍንትው ማድረግ እና ውሸቱን ከእውነቱ ለይቶ ግልፅ ማድረግ (ግዴታ ነው)። አላህ ደግሞ አበላሹን ከአስተካካዩ እንዲሁም የሚያለባብሰውን ከሚገልፀው ለይቶ ያውቃል።»

رسالة السماع له ص - ٤٨.


* وقال العلاّمة أحمد النجمي - رحمه الله:

”أما الذين سكتوا عن بيان الحق للناس فإنهم ﻻ يعذرون بسكوتهم ولو قالوا نحن لسنا معهم فإنهم ﻻيعذرون“ اﻫـ .

* እውቀተ-ብዙዉ አህመድ ቢን የህያ አን-ነጅሚይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦

«እንዚያ ሀቅን ለሰዎች ግልፅ ከማድረግ ይልቅ ዝም ያሉትማ ዝምተኛ ናቸው በማለት አይመካኝላቸውም። እኛ (ከባጢል) ሰዎች አይደለንም! ቢሉ እንኳ አይመካኝላቸውም።»

تحذير السلفي من منهج التميع الخلفي ص - ٣١١.

* وقال شيخ الإسلام بن تيمية رحمه الله:

"وصاحب الهوى يعميه الهوى ويصمه فلا يستحضر الله ورسوله في ذلك ولا يطلبه ولا يرضى برضا الله ورسوله ولا يغضب لغضب الله ورسوله بل يرضى إذا حصل ما يرضاه بهواه ويغضب إذا حصل ما يغضب له بهواه"

* የኢስላም ባለውለታው ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላል፦

«ስሜትን የሚከተል ሰው ስሜቱ አሳውሮ ያደነቁረዋል። ስሜቱን ሲከተል አላህ እና መልእክተኛው በልቡ አይሰየሙም (አይፈራም)። መፍራትም አይፈልግም። የአላህ እና የመልእከተኛው ውዴታም አያስደስተውም። የአላህ እና የመልእክተኛው መቆጣት አያስቆጣውም። እንደውም እሱ የሚወደው ነገር ሲገኝ ለስሜቱ ሲል ይደሰታል። እሱን የሚያስቆጣው ነገር ሲገኝ ለስሜቱ ሲል ይናደዳል።»

منهاج السنة له ٢٥٦/٥.

* قال الحافظ ابن القَيِّم - رحمه الله:

 ”ﻭﻣﻌﻠﻮﻡ ﺃﻧﻪ ﺇﺫﺍ ﺍﺯﺩﻭﺝ ﺍﻟﺘﻜﻠﻢ ﺑﺎﻟﺒﺎﻃﻞ ﻭﺍﻟﺴﻜﻮﺕ ﻋﻦ ﺑﻴﺎﻥ ﺍﻟﺤﻖ ﺗﻮﻟﺪ ﺑﻴﻨﻬﻤﺎ ﺟﻬﻞ ﺍﻟﺤﻖ ﻭﺇﺿﻼﻝ ﺍﻟﺨﻠﻖ“ اﻫـ .

* የሳቸው ኮከብ ተማሪ የሆኑት ኢብኑል ቀዪም (ረሒመሁላህ) ደግሞ እንዲህ ይላሉ፦

«እንደሚታወቀው ባጢልን ከማስተማር እና ሀቅን ግልፅ ከማድረግ ዝም ማለት የተቆራኙ ግዜ በመካከላቸው የሀቅ አለ-መታወቅ እና ፍጥረትን ማጥመም ይፈጠራል።»

الصواعق المرسلة ص - ٥٢.

* وقال العلاّمة ابن عثيمين - رحمه الله:

”ﺇﻥ ﻛﻨﺖ ﻭﺣﻴﺪﺍ ﻓﻲ ﺑﻠﺪﻙ ﺗﺪﻋﻮﺍ إلى ﺍﻟﺴﻨﺔ ﻭﺍﺗﺒﺎﻉ ﺍﻟﺴﻠﻒ ﻭﻛﺜﺮ ﺍﻷﻋﺪﺍﺀ ﺍﻟﺬﻳﻦ ﻳﺪﻋﻮﻥ ﺇﻟﻰ ﻣﺬﻫﺒﻬﻢ ﺍﻟﺒﺎﻃﻞ ﻓﺎﻟﻮﺍﺟﺐ ﺃﻻ ﺗﻨﻬﺰﻡ لأﻧﻚ ﺇﺫﺍ ﺍﻧﻬﺰﻣﺖ ﻓﻘﺪ ﻫﺰﻣﺖ ﺍﻟﺤﻖ ﺑﻞ ﺍﺛﺒﺖ ﻭﻣﺎ ﺃﺭﻋﺐ أﻋﺪﺍﺀﻙ ﺇﺫﺍ ﺭﺃﻭﻙ ﺛﺎﺑﺘﺎ“ اﻫـ .

* የዘመኑ ሊቅ የነበሩት ኢብኑ ዑሰይሚን (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦

«ሀገርህ ውስጥ ቀደምቶችን ወደ-መከተል እና ወደ-ሰለፍያ የምትጣራ ብቸኛ (ዳዒ) ከሆንክ እና ወደ-ጥመታቸው የሚጣሩ ጠላቶችህ ከበዙ ባንተ ላይ ግዴታው አለ-መሸነፍ ነው። ምክንያቱም አንተ እጅ ከሰጠህ (ባንተ ሲመራ የነበረው) ሀቅ ይወድቃል። እንግዲያውስ ፅና። ጠላቶችህ ፀንተህ ሲያዩህ ለነሱ ምንኛ አስፈሪ ነው?! (ፍርሀት ይወድቅባቸዋል።)»

ﺷﺮﺡ ﺍﻟﻜﺎﻓﻴﺔ ﺍﻟﺸﺎﻓﻴﺔ ٢٠١/١.

t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


ሐሜትና ወሬ አመላላሽነት መልካም ስራን ባዶ ያደርጋል
———
ሰዒድ ኢብን ጁበይር (ረሂመሁላህ) እንዲህ አለ:-
“በእለተ ትንሳዔ ለአንድ ባሪያ የስራው መዝገብ ይመጣና ይከፈትለታል፣ መዝገቡ ላይም የሶላትም ሆነ የፆም ውጤት አይመለከትበትም፣ ወደሰራው መልካም ስራም ቢመለከት የለም፣ ይህን ጊዜ "ጌታዬ ሆይ ይህ እኮ የሌላ ሰው መዝገብ ነው፣ የኔ የስራ መዝገብ አይደለም፣ ምክንያቱም ለኔ መልካም ስራዎች ነበሩኝ እዚህ መዝገብ ላይ ደግሞ የሉም።" ይላል፣ ለእርሱም ምላሹ እንዲህ ይባላል:- ጌታህ አይስትም አይረሳም፣ ስራህ እንዳለ ሰዎችን በማማትህ ጨርሶ ሄዷል። ይባላል፣
አደራ!! ወንድም እህቶቼ ሐሜትንና ወሬ አመላላሽነትን ተጠንቀቁ!! ሁለቱም ዲንን ይጎዳሉ!! የመልካም ሰሪንም ስራ ያበላሻሉ!!። አላህ ይጠብቀንና በሙስሊሞችም መካከል ጥላቻን ያስወርሳሉ።”
[በህር አድ-ዱሙዕ ሊብን አል-ጀውዚ 133]

ልብ በሉ! የሀሜትና ነገር አዋሳጅነት አደጋ እንዲህ የከፋ ከመሆኑም ጋር አላህ (ይጠብቀንና) ብዙዎች የተዘፈቁበት ልክ ሀላል (የተፈቀደ) እስኪመስል በሁሉም ወቅት የሚያዘውትሩት አደገኛ መልካም ስራን አውዳሚ ተግባር ነውና በእጅጉ ልንጠነቀቀውና ልንርቀው ይገባል!!
✍🏻ኢብን ሽፋ
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ  ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ)  የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


የረመዷን ምክር 01

(የፆም ህግጋቶች የተዳሰሱበት እና በፆማችን ላይ እያጋጠሙ ያሉ እክሎች የተዳሰሱበት)

#እጅግ_በጣም_ወሳኝ_ነጥብ_የተዳሰሰበት_አጠር_ያለ_ሙሓዶራ

በሸይኽ ሐሰን ገላው ሃፊዞሁሏህ

#መጠን_3.54 mb

#1446_ሒ.

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة


ፆመን ውለን ስናበቃ ያለ አጅር ባዶዋችን እንዳንገባ እንጠንቀቅ!!
———
በዚህን ጊዜ አላህ ያዘነለት ሰው ሲቀር የብዙ ሰዎችን ተግባርና ምላስ ስናይ ፆም ማለት:- በቃ ከምግብና ከሚጠጡ ነገሮች መታቀብ ብቻ ይመስላቸዋል። ይህ ከባድ የሆነ አደጋ ነው!። አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል አለ:-

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : " مَنْ لَمْ يَدَعْ قَوْلَ الزُّورِ وَالْعَمَلَ بِهِ وَالْجَهْلَ، فَلَيْسَ لِلَّهِ حَاجَةٌ أَنْ يَدَعَ طَعَامَهُ وَشَرَابَهُ ".
صحيح البخاري وغيره

(ፆመኛ ሆኖ) በውሸት መናገርን ያልተወ፣ በውዳቂ ነገር መስራትን ያልተወ ሰው፣ በአላዋቂነትና በሞኛሞኝነት በሰዎችም ሆነ በራሱ ላይ ድንበር ማለፍን (ቂላቂል መሆንን) ካልተወ ምግብና የሚጠጣ ነገር በመተው ለአላህ ግድ የለውም።”  [ቡኻሪና ሌሎችም ዘግበውታል።]

ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
«ፆመኛ ማለት አካሎቹ ከሀጢአት የጸዱ፤ ምላሱን ከአሉባልታ፣ ከውሸት እና ከአጸያፊ ንግግር የጠበቀ፤ ሆዱን ከምግብ ፣ ከመጠጥ እና ብልቱን (በቀን ክፍለ ጊዜ) ከግብረ ስጋ ግንኙነት የጠበቀ ነው።

ፆመኛ ከተናገረ፣ ፆሙን በማይጎዳ መልኩ ይናገራል፣ ስራ ከሰራ ፆሙን በማያበላሽበት መልኩ ይሰራል። ፆመኛ ጠቃሚና ቁምነገር ያለው ንግግር እና ስራ ሲሰራ ምሳሌው ልክ ከሽቶ ተሸካሚ ሰው ጋር ተቀምጦ መልካም ሽታ እንደሚያገኝ ሰው ነው!!። ከፆመኛ ጋር የተቀመጠም ሰው መልካም ነገርን እንጂ ሌላ አያገኝም። ከተለያዩ መጥፎ ነገሮች እንደ ቅጥፈት፣ ውሸት፣ ጥመት እና በደል ከመሰሉ ነገሮች ሁሉ ሰላም ይሆናል። ይህ ነው ትክክለኛና ህጋዊ ፆም ማለት። ከምግብና መጠጥ ብቻ መታቀብ ፆም አይባልም።

ፆም ማለት አካላትን ከሀጢአት፣ ሆድን ከምግብና ከሚጠጣ ነገር በመታቀብ መፆም ነው። ምግብና የሚጠጣ ነገር ፆምን እንደሚያበላሽ ሁሉ ሀጢአትም የፆምን ምንዳ ያበላሻል፣ ውጤቱንም ያበላሻል። በዚህም ምክንያት ልክ ፆም እንዳልፆመ ተደርጎ ይታሰባል።» [አልዋቢሉ አስ-ሶይብ 31-32]
✍🏻 ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa




ዳር አስ-ሱንና Dar As-sunnah Channel dan repost
↪️ በፆመኞች ጨፌ ክፍል ③

في رياض الصائمين
[الحلقة الثانية من عجائب قدرة الباري خلق الإنسان]


📝 ከፈጣሪያችን ገራሚ ችሎታ ውስጥ የሰው ልጅን መፍጠሩ ነው!

🎙🎙 ዶክተር ሸይኽ ሑሰይን ሙሐመድ አስ’ሲልጢይ አላህ ይጠብቃቸው

👂በደምብ ይደመጥ


القناة الرسمية التابعة والمعتمدة للشيخ حسين السلطي حفظه الله
https://t.me/HussinAssilty


ዳር አስ-ሱንና Dar As-sunnah Channel dan repost
↪️ በፆመኞች ጨፌ ክፍል ②

في رياض الصائمين
[الحلقة الثانية من عجائب قدرة الباري خلق الإنسان]


📝 ከፈጣሪያችን ገራሚ ችሎታ ውስጥ የሰው ልጅን መፍጠሩ ነው!

🎙🎙 ዶክተር ሸይኽ ሑሰይን ሙሐመድ አስ’ሲልጢይ አላህ ይጠብቃቸው

👂በደምብ ይደመጥ


القناة الرسمية التابعة والمعتمدة للشيخ حسين السلطي حفظه الله
https://t.me/HussinAssilty


ዳር አስ-ሱንና Dar As-sunnah Channel dan repost
↪️ በፆመኞች ጨፌ ክፍል ①

في رياض الصائمين
[الحلقة الثانية من عجائب قدرة الباري خلق الإنسان]


📝 ከፈጣሪያችን ገራሚ ችሎታ ውስጥ የሰው ልጅን መፍጠሩ ነው!

🎙🎙 ዶክተር ሸይኽ ሑሰይን ሙሐመድ አስ’ሲልጢይ አላህ ይጠብቃቸው

👂በደምብ ይደመጥ


القناة الرسمية التابعة والمعتمدة للشيخ حسين السلطي حفظه الله
https://t.me/HussinAssilty


አሏህ ከባሮቹ የተብቃቃ ነው

አሏህ ለባሮቹ በጎ ሰሪ  ፤ ከባሮቹ የማይፈልግ ፣ በራሱ የተብቃቃ ነው፤
ቸር  ፣ አሸናፊ ፣ አዛኝ የሆነ ጌታ ነው።

ከባሪያው የማይከጅል ከመሆኑ ጋር ፣ ለባሪያው በጎ ይሰራ ፣ ለባሪያው መልካምን ይሻል ፣  ከባሪያው ላይ ጉዳትን ያስወግዳል። ይህን የሚፈጽመው   ከእርሱ በሆነ እዝነትና በጎ አድራጊነት እንጅ ከባሪያው  ጥቅምን ሽቶ ፣ (የሚመጣ) ጉዳት ኖሮ ጉዳትን ከእርሱ ላይ እንዲከላከሉለት ፈልጎ አይደለም።

አሏህ ፍጡራንን የፈጠረው እርሱ አነስተኛ ሆኑ ቁጥሩን ለማብዛት አይደለም ወይም የሚዋረድ ሆኖ በእነርሱ ልቅና ለማግኘት አይደለም ወይም እርሱን ለመመገብ ፣ እርሱን ለመጥቀም አይደለም ወይም ከእርሱ ላይ ጉዳትን እንዲከላከሉለት አይደለም።

አሏህ የሚከተለውን ተናግሯል :-
وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
مَا أُرِيدُ مِنْهُم مِّن رِّزْقٍ وَمَا أُرِيدُ أَن يُطْعِمُونِ
إِنَّ اللَّهَ هُوَ الرَّزَّاقُ ذُو الْقُوَّةِ الْمَتِينُ
"ጅንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ ከነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም፡፡ ሊመግቡኝም አልሻም፡፡ አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ኀይል ባለቤት ነው፡፡"
(ዛሪያት 56-58)

አሏህ የሚከተለውን ተናግሯል :
وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي لَمْ يَتَّخِذْ وَلَدًا وَلَمْ يَكُن لَّهُ شَرِيكٌ فِي الْمُلْكِ وَلَمْ يَكُن لَّهُ وَلِيٌّ مِّنَ الذُّلِّ ۖ وَكَبِّرْهُ تَكْبِيرًا
«'ምስጋና ለአላህ ለዚያ ልጅን ላልያዘው፣ ለእርሱም በንግሥናው ተጋሪ ለሌለው፣ ለእርሱም ከውርደት ረዳት ለሌለው ይገባው' በልም፡፡ ማክበርንም አክብረው፡፡»
(ኢስራእ :111)

አሏህ ወዳጆቹን የሚወደው ከእርሱ በሆነ በጎነትና  እዝነት ነው።

አሏህ የሚከተለውን ተናግሯል:-
وَاللَّهُ الْغَنِيُّ وَأَنتُمُ الْفُقَرَاءُ ۚ 
"አላህም ሐብታም ነው፡፡ እናንተም ድሆች ናችሁ፡፡"
(ሙሀመድ :38)

ፍጡራን እርስ በርስ የሚደጋገፉት ድሃ በመሆናቸው ነው። አፋጣኝ ወይም ዘግይቶ የሚገኝ ጥቅም ሽተው ነው። ጥቅምን  ታሳቢ ባያደርጉ ኖሮ አንዱ ለሌለው በጎ ባልሰራ ነበር።

በሀቂቃ ካየነው የሰው ልጅ ለሌሎች በጎ የሚሰራው ከእነርሱ ጥቅም ለማግኘት መዳረሻ መንገድን ለማመቻቸት ነው።
የሰው ልጅ  በጎ የሚሰራው በዚህ አለም የመልካም ዋጋውን ፈጥኖ ለማግኘት  ወይም ለበጎ ስራው  ለውጥ ፈልጎ ወይም ከሌላው ምስጋና እና ውዳሴን ጠብቆ ነው
ወይም በአኼራ ከአላህ ዘንድ ምንዳ ለማግኘት ፈልጎ ነው።  በዚህ ምክንያት እርሱ ለነፍሱ በጎ ይሰራል።

ይሁን እንጅ ደካማ ሳይሆን በሚጠቅመው (አሏህ በፈቀደው) ነገር ላይ መጓጓቱ እርሱን የተሟላ ያደርገዋል እንጅ የሚያስወቅሰው አይደለም።

አሏህ የሚከተለውን ተናግሯል :-

إِنْ أَحْسَنتُمْ أَحْسَنتُمْ لِأَنفُسِكُمْ ۖ
"መልካም ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ፡፡"
(ኢስራእ :7)

አሏህ የሚከተለውን ተናግሯል

وَمَا تُنفِقُوا مِنْ خَيْرٍ يُوَفَّ إِلَيْكُمْ وَأَنتُمْ لَا تُظْلَمُونَ
"ከገንዘብም የምትለግሱት ሁሉ (ምንዳው) ወደናንተ ይሞላል፡፡ እናንተም አትበደሉም፡፡"
(በቀራ :272)

አሏህ በሀዲሰል ቁድስ የሚከተለውን ተናግሯል:-
(يا عبادي! إنكم لن تبلغوا نفعي فتنفعوني ، ولن تبلغوا ضري فتضروني ، يا عبادي! إنما هي أعمالكن أحصيها لكم ، ثم أوفيكم إياها ، فمن وجد خيرا فليحمد الله ، ومن وجد غير ذلك فلا يلومن إلا نفسه)
أخرجه مسلم (٢٥٧٧)
(ባሮቸ ሆይ! እናንተ እኔን መጥቀም (ብትፈልጉ) መጥቀም አትችሉም ፤ መጉዳት (ብትፈልጉ) መጉዳት አትችሉም ፤ ባሮቸ ሆይ ! እርሷ ስራችሁ ነች፣ ለእናንተም እዘግባታለሁ ፤ ከዚያም እርሷን እመነዳችኋለሁ። መልካምን ያገኘ አላህን ያመስግን ፤ ከእርሱ ውጭ ያገኘ ፣ ነፍሱን እንጅ ሌላን እንዳይወቅስ)

"ጢቡል ቁሉብ : 227-228)

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة


የተራዊህ ሶላት እና ሴቶች
———
ጥያቄ:- ለሴት ልጅ የተራዊህ ሶላት ተደንግጓልን?

መልስ:- የሴት ልጅ ሶላት ግዴታ የሆነውም ሆነ ሱንናውም፣ ተራዊህም ሌሎችንም ሶላቶች በላጩ ከመስጂድ ይልቅ በቤቷ መስገዷ ነው። [የሳዑዲ የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ 7/201]

#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa


“ቁል ሁወ አላሁ አሀድ  قـُلْ هُـوَ اللَّهُ أَحـَد ” ብልጫ
———
ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አልበድር አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ይላሉ:-

“ቁል ሁወ አላሁ አሀድ: قـُلْ هُـوَ اللَّهُ أَحـَد
የቁርኣንን አንድ ሶስተኛውን ትስተካከላለች። አላሁ አክበር! ብልጫዋን ምንኛ አከበዳት?! የ30 ጁዝ ቁርኣን ፊደሎች ብዛት 361180 ፊደል ነው፣ 323015 ፊደል ነውም ተብሏል፣ 340740 ፊደል ነውም ተብሏል፣
ኢብን ከሢር በተፍሲራቸው መቅደም ላይ እንደጠቀሱት።

በኢብኑ መስዑድ ሀዲስ እንደተጠቀሰው ከቁርኣን አንድ ፊደልን የቀራ 10 ምንዳ አለው ከተባለ፣ ቁርኣንን ሁሉን ጨርሶ ከቀራ ስንት ምንዳ ነው የሚያገኘው? «ቁል ሁወ አላሁ አሀድ»ን ሶስት ጊዜ መቅራት ሁሉንም ትስተካከለዋለች፣ ወላሂ ምንዳዋ ምንኛ የከበደ ነው! ይህ ብልጫዋ/ ትሩፋቷ ነው! ምክንያቱም እሷን ሶስት ጊዜ መቅራት ሰላሰውን ጁዝ ከመቅራት የሚያብቃቃ ነው፣ እንዲያውም ከቀደምቶች 30ጁዝ ሙለውን ከተቀራ እሷን ከአንድ ጊዜ በላይ መቀራቷን ጠልተዋል።
ምንጭ:-http://al-badr.net/muqolat/4487 ግርድፍ ትርጉም ኢብን ሽፋ።

ኢብን ሽፋ:- ይህ የረመዷን ወር ነውና ከምን ጊዜውም በላይ ለቁርኣን ጊዜ ሰጥተን በተደጋጋሚ እያስተነተንን ለመጨረስ ልንዘጋጅ ይገባል!። በተለይ ሴቶች! ምግብ ለመስራት ከምታደርጉት ዝግጅት በፊት ለቁርኣን ጊዜያችሁን ከወዲሁ ሳያመልጣችሁ ማመቻቸትና ማስተካከል ይገባችኋል!! ብዙ ጊዜ ሴቶች ረመዷን ሲመጣ ምግብ በመስራትና በመሳሰሉ ነገሮች ራሳቸውን ማጨናነቃቸው የተለመደ ነገር ሆኗል፣ ቀደምቶች የረመዷንን ወር ምግብ በመስራት አልነበረም ቢዚ ሆነው የሚያሳልፉት፣ ወንዶችም በጫትና በነሺዳ እንዲሁም ድራማ መሰል ነገሮች ላይ አልነበረም ራሳቸውን ቢዚ የሚያደርጉ የነበረው፣ ቁርኣን ለማንበብ ያልታደሉና ጭራሹኑ ምንም መቅራት የማይችሉ ሰዎችም ቁርኣንን ትኩረት ሰጥተው ተረጋግቶ በማዳመጥ በዚክርና ስለ ዐቂዳቸው ሊያውቁባቸው የሚችሉ የሱንና ሰዎች የፃፏቸው መፅሃፍቶችን በማንበብ ቢዚ ሊሆኑ ይገባል፣ ስለዚህ ከወዲሁ ቆም ብሎ ማስተዋልና በቁርኣንና በሌሎችም የዒባዳ አይነቶች ጠንክረን ልናሳልፍ ይገባል!!
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


ቁርኣንን ለማስተንተን የሚረዱ አስር ነጥቦች
—————
① በእራስ ላይ የተረጋጋና የመተናነስን ተፅእኖ እያሳደሩ ማንበብ። እንዲሁም የአንባቢው ግብ ሱራውን መጨረስ ብቻ መሆን የለበትም።

② አንባቢው የተናጋሪውን የአላህን (ጥራት ይገባ ውና) ልቅና በሚያነብበት ጊዜ በልቡ ሊያስገኝ ነው። ለአላህ ቃል ነቃ ሊል! ልቡም ሊረጥብና ሊፈራ! እንዲሁም የአላህን ረህመት ሊከጅል በዚህም ሊደሰት ይገበዋል።

③ ከሸይጧን በአላህ ይጠበቅ! ከሸይጧንም የመጠበቁን እገዛ በልቡ አላህን ሊያስቀምጥ ነው። ምክንያቱም ሸይጧን አንባቢውን የአላህን ቃል አንብቦ እንዳይጠቀምበት ለማድረግ ይሸቀዳደማል።

④ ቁርኣን የሚቀራው ሰው ድምፁን ዝቅ አድርጎ አሳምሮ ልክ ትርጉሙን እንደሚፈልግና እንደሚያጠና መፍጠንንም እንደሚፈራ ሆኖ የአንቀፁን ሀሳብ ባልቋጨበት ቦታ ከማቆምና አለያም ሀሳቡ ምን እንደሆነ ሳያጤናው ማለፍ የለበትም!።

⑤ ቁርኣንን ለማስተንተን ከሚረዳው ነገር ትልቁና አንዱ ከሰማይ ወደ ምድር እንዴት እንደወረደና ነቢዩ እንዴት እንደያዙት፣ ከዚያም ሶሃቦች ከነቢዩ የመጀመሪያ በሰሙት ጊዜ በነፍሳቸው ላይ ምን አይነት ተፅእኖ እንዳሳደረባቸውና እንዴት ተቀብለው እንደተገበሩት ማወቅ ነው!!።

⑥ ሌላው ወሳኝ ነጥብ በየትኛውም ሁኔታ ስንኖር ለሕይወታችን ቁርኣንን መድኃኒት ማድረግ ነው!!። እናታችን ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ስለ ነቢዩ ስነ-ምግባር ስትጠየቅ "ስነ-ምግባራቸው ቁርኣን ነበር" ብላ ነው የመለሰችው።

⑦ አንባቢው በነቢያቶችና በደጋጎች ላይ የአላህን ውዳሴ ካነበበ አላህ እያናገረው መሆኑን ያውቃል። ነቢያቶችንና ደጋጎችን መከተሉ ተፈላጊ መሆኑንም ያውቃል። አላህ ወንጀለኞችንና በደለኞችን የሚወቅስበትን ቦታ ካነበበ አላህ እያናገረው መሆኑን ያውቃል፣ የሚፈለገውም ከነሱ ባህሪ መጠንቀቁና መራቁ እንደሆነ ሊያውቅ ይገባል።

⑧ አንቀፆችን በተደጋጋሚ እንደ አዲስ ማስተንተንና አንዴ ብቻ በማስተንተን አለመገደብ፣ አንዲትን አንቀፅ አንዴ ካስተነተናት በኋላ በዛው ከልቡ ልትቋረጥ አይገባውም!። ሊደጋግማትና ወደርሷም መለስ እያለ ሊያየስተውላት ይገባል!! ትርጉሟም በልቡ እስኪታተም ከአንቀጿ ሊቋረጥ አይገባውም!!።

⑨ ወደራሱ ሊመለከትና ራሱንም ሊፈትሽ ይገበዋል። እውነት ከልቤ አስተንትኜዋለሁ?! ወይስ አላስተነተንኩትም? ብሎ እራሱን ሊጠይቅ ይገበዋል። በውስጣዊና በውጪያዊ ስራው ቁርኣን በሕይወቱ በ(ኢባዳው) በአምልኮው ተፅእኖ መፍጠር አለመፍጠሩን እራሱን ሊፈትሽ ይገበዋል።

10, ከቤተሰባችን ከልጆቻችን በምንቀማመጥበት ጊዜና በምንመካከርበት፣ ሙሃደራ በምናደርግበት፣ እንዲሁም መድረክ ላይ ቆመን ንግግር በምናደርግበት ጊዜ ንግግራችን ሁሉ ሊሆን የሚገባው ቁርኣንን ስለ ማስተንተንና በቁርኣን ስለመተግበር ሊሆን ይገባል!!

እርግጥ ነው! አላህ ግንዛቤውንና ማስታወሱን አግርቶልናል። ከፍጥረተ  ዓለሙ ሁሉ በላይ ከፍ ያለው፣ የላቀው! አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

﴿وَلَقَد يَسَّرنَا القُرآنَ لِلذِّكرِ فَهَل مِن مُدَّكِرٍ﴾ القمر ١٧

ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፣ ተገንዛቢ አለን?። " አል-ቀመር 17

አላህ በአግባቡ በትክክለኛው መንገድ ለመገንዘብና ለማስተንተን በህጎቹም በትክክል ለመተግበር፣ ስነ-ምግባራችን ቁርኣን  እስኪሆንና በአኼራም "ዱኒያ ላይ ታነበው እንደነበረው አንብብ" እስክንባል ይወፍቀን!! አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.