Bahiru Teka dan repost
👉 የነሲሓዎች የአደባባይ ዝቅጠት ለአደባባይ ክስረት
ነሲሓዎች የነበሩበት መንገድ ለዱንያዊ ክብረት እንደማይሆን ሲያውቁ ሸይኻቸው ኢልያስ አሕመድ ህዝቡን አስተኝቶላቸው ከኢኽዋን ጋር ተቀላቅለው መስራት እንዳለባቸው ከወሰኑ በኋላ በ30 የእንቅልፍ ክኒን ወጣቱን አስተኛላቸው ። ቀጥለው የተኛው ህዝብ ሳይነቃ ቶሎ ወደ ሚፈልጉበት ለመድረስ ሩጫ ጀመሩ ። ሩጫቸው ታርጌት ያደረገው የእንጀራ አባቶቻቸው ኢኽዋኖችን ማስደሰት ላይ ነበር ። በዚህም ሸይኻቸው ዶ/ር ጀይላንን ከማወደስ ጀምሮ የተለያዩ ደረጃዎችን በፍጥነት እየተንደረደረ ነጎደ ።
አደባባይ እየወጣ ከነ ካሚል ሸምሱ ፣ አቡ በከር አሕመድ ፣ ያሲን ኑሩ ፣ ሙሓመድ ሓሚዲን ፣ ሓሚድ ሙሳና ሌሎችም ዋና ዋና መሪዮች ጋር በተለያዩ ፕሮግራሞች አብሮነታቸውን አሳየ ። እሱ መርጂዓቸው ስለሆነ እንጂ እነ አዩብ ደርባቸውም በፊናቸው በተለያዩ መድረኮች አብሮነታቸውን አረጋግጠዋል ። ይህ ሁሉ ሲሆን በ30 የእንቅፍ ክኒን እንዲተኙ የተደረጉ ሙሪዶች አልነቁም ነበር ። ይልቁንም እኛ ስለማናውቅ ነው እንጂ እነርሱ ያለ መስላሓ አይሰሩም የሚል የጋራ ድምፅ ያሰሙ ነበር ።
ኢልያስ አሕመድ 30 የእንቅልፍ ክኒን ሲሰጥ አብዛኛው ወጣት ኢኽዋኖችን ያለእውቀታችን በናንተ ላይ ተናግረን ነበር አሁን ተመልሰናል አውፍ በሉን ብሎ ነበር ። ያኔ የ30 ክኒኖቹ ሚስጢር የገባቸው ሰዎች ውስጣቸው እያረረ ኢኽዋኖች በድል አድራጊነት ስሜት ይጎርሩ ነበር ። መሻኢኾችና የተወሰኑ ወንድሞች ያደረጉት የነሲሓዎችን አካሄድ የማጋለጥ ትግል ብዙ ፍሬ ያፈራ የነበረ ቢሆንም የአሁኑ አይነት ድል ይገኛል ብሎ ያሰበ አልነበረም ።
በሚገርም መልኩ ብዙ ወንድምና እህቶች የነሲሓዎች ሸይኽ ሶሞኑን የሱፍያና ኢኽዋንያ ሚንሀጅ እስፕሪስ ጭማቂ ከሚያንቃርረው ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን ጋር የነበረውን ፕሮግራም ካዩ በኋላ አውፍ በሉን ነገሩ በዚህ መልኩ አልመሰለንም ነበር እያሉ ነው ።
ለእነዚህ ወንድምና እህቶች እንዲሁም ለሌሎችም የምንለው መጀመሪያ ምስጋና ሐቅን ላሳወቃችሁ አምላካችን አላህ ይገባው ። ቀጥሎ እኛን በግል በሰድብም ይሁን ስም በማጥፋት ላደረሳችሁት በደል በቅድሜያ እኔ በግሌ አውፍ ብያለሁ መሻኢኾችም ይሁን ሌሎች ወንድሞች ከዚህ የተለየ እይታ ይኖራቸዋል አልልም ። ምክንያቱም ሁላችንም ነብዩን ነውና የምንከተለው ። የአላህ መልእክተኛ አላህ መካን እንዲከፍቱ ድል ሲሰጣቸው እነዚያ መተተኛ ፣ ጠንቋይ ፣ ገጣሚ ፣ እብድ ሲሏቸው የነበሩ የመካ ሹማምንቶች ተሰብስበው ፍርዳቸውን ለመቀበል ሲጠብቋቸው ሂዱ እናንተ ነፃ ናችሁ ነበር ያሉዋቸው ። ነብዩላሂ ዩሱፍም ጉድጓድ ውስጥ የወረወሩዋቸውን ወንድሞቻቸው አላህ ድል ሰጥቶ የበላይ አድርጓቸው አንገታቸውን ደፍተው ይቅርታ ሲጠይቋቸው ሂዱ አላህ ምህረቱን ይስጣቸሁ ነበር ያሉዋቸው ። የሚፈለገው ሐቅን አውቆ ወደ አላህ መመለሱ ነውና የሰዎች ክብር የተነካው በአላህ መንገድ ላይ እስከሆነ ድረስ ከፍታ እንጂ ዝቅታ ስላልሆነ ቦታ አይሰጠውም ። ይልቁንም ይህን ወንጀል ከመስራታችሁ በፊት ከነበራችሁ ደረጃ ይጨምርላችኋል ። ምክንያቱም አላህ ዘንድ አንድ ሰው ወንጀል ሳይሰራ በፊት ከነበረው ደረጃ ወንጀል ሰርቶ ተውበት አድርጎ ሲመለስ ያለው ስለሚበልጥ ።
አሁንም ኢልያስም ሆነ ሌሎች በየቀኑ እየዘቀጡ ማየታችን ለኛ ህመም እንጂ ደስታን አይፈጥርም ። የወንድምና እህቶች መመለስ የሚፈጥረው ደስታ የነሲሓዎች ዝቅጠት ያደበዝዘዋል ። ሙሉ ደስታ የሚሰጠው ሙኻሊፎች ባጠቃላይ ተውበት አድርገው ወደ አላህ መመለሳቸው ነው ። አሁንም ለነሲሓዎች የምንለው በየቀኑ በአደባባይ የምታሳዩት ዝቅጠት ወደ አደባባይ ክስረት እየተቀየረባችሁ ነውና ቆም ብላችሁ አስቡና ተመለሱ ነው ።
https://t.me/bahruteka