አገር አቋራጭ እንቅስቃሴዎችን መገደብ
~~~~~~~~~~~~~
እንደ ሃገር እስካሁን ‘ኦፊሻሊ’ በተነገረን መሰረት ወረርሺኙ የገባው አዲስ አበባ ብቻ ነው። የሃገሪቱ አብዛኞቹ የጤና ተቋማት፣ የህክምና ‘ፋሲሊቲ’፣ አንፃራዊ የህዝብ ንቃት፣ የተሻለ ርብርብ ያለውም ከክፍለ ሃገሩ ይልቅ በአዲስ አበባ ነው። ስለዚህ ባለንበት ሁኔታ ወረርሺኙ ወደ ክፍለ ሃገር ቢዛመት ከአዲስ አበባ ይልቅ ውጤቱ ይበልጥ አስከፊ የመሆን አዝማሚያ አለው። እኛ ደግሞ ሃይማኖታችን ለሌሎችም ተምሳሌት የሚሆን መመሪያ አለው። እንደሚታወቀው ወረርሺኝን አስመልክቶ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
«إِذَا سَمِعْتُمْ بِالطَّاعُونِ بِأَرْضٍ فَلاَ تَدْخُلُوهَا، وَإِذَا وَقَعَ بِأَرْضٍ وَأَنْتُمْ بِهَا فَلاَ تَخْرُجُوا مِنْهَا»
“በአንድ ሃገር ወረርሺኝ መግባቱን ከሰማችሁ ወደሷ አትግቡ። ባላችሁባት ሃገር ከተከሰተ ከሷ አትውጡ።” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ይህንን ነብያዊ ትእዛዝ በጥብቅ ልንተገብረው የሚገባን ወሳኝ ጊዜ ላይ ነን። ስለዚህ:–
① የሸገር ነዋሪዎች ሆይ! ወደ ክፍለ ሃገር የምታደርጉትን ጉዞ አቁሙ።
② የክፍለ ሃገር ነዋሪዎች ሆይ! ወደ ሸገር የምታደርጉትን ጉዞ አቁሙ።
•
በአስገዳጅ ምክንያት የምንጓዝ ከኖርንም ተገቢውን ጥንቃቄ ከማድረግ አንዘናጋ። ለእያንዳንዱ ነገር የመንግሥት እወጃዎችን ልንጠብቅ አይገባም። እስካሁን እየታዘብን ባለው በጉዳዩ ላይ ከፊት ሳይሆን ከኋላ ነው። እነዚህ የህዝብን ጩኸት እያዘገሙ በርቀት የሚከተሉ የተንቀራፈፉ አካሄዶቹ መዘዛቸው የከፋ ነው። የመንግስት ከፍተኛ ባለ ስልጣናት ማታ በሚዲያ ስለ መራራቅና መሰል ጥንቃቄዎች ደስኩረው ቀን በስብሰባ ተጠምደው እየዋሉ ነው። ሌላው ቀርቶ ዛሬ ከጃክ ማክ የተላከን እርዳታ ለመረከብ በነበረ ክንውን ላይ የነበራቸው ሁኔታ አሳፋሪ ነው።
ዋናው ትኩረቴ ግን ለእያንዳንዱ ነገር የመንግስትን ውሳኔ ሳንጠብቅ እራሳችን ልንወስዳቸው የምንችላቸውን ጥንቃቄዎች እንወጣ ለማለት ነው። በተለይም ደግሞ እንቅስቃሴዎቻችንን በተቻለ መጠን እንገድባቸው።
ኢብኑ ሙነወር
https://t.me/IbnuMunewor