⚡️⚡️#ፍትሕ_ከሰማይ_ሲወርድ⚡️⚡️
✍አሚር ሰይድ
ከማህፀናቸው ፍሬ የወጣ ልጅ፣ በክፉ ጊዜም ደራሽ ዘመድ አዝማድ የላቸውም። የሰባ ዓመት ዕድሜ ደካማ ባልቴት ናቸው። “እንዴት ሰው ያለወገን ይፈጠራል?" ይባል ይሆናል። ዘመድ አዝማዶቻቸው ሁሉ ይህችን ዓለም ተራ በተራ እየለቀቁ ቀድመዋቸው ተጉዘዋል፡፡ የጤንነታቸው ጉዳይ ማጠራጠር ከጀመረ ሰንበትበት ብላል። "እንደምን ዋሉ? " ላላቸው ሁሉ "ጉልበቴን ይቆረጥመኛል፣ ወገቤን ያመኛል፣ ዓይኔንም ያዝ እያደረገኝ ነው" ሳይሉ አያልፉም። ይህ ብቻም አይደለም" አላህ መጨረሻዬን አሳምሮ ብርሀኔን ሳያሳጣኝ፣ መላወስ ሳይሳነኝ ቀልጠፍ አድርጐ በወሰደኝ" ሲሉ ያክሉበታል፡፡
ዋነኛ መተዳደርያቸው ከመንግስት የሚያገኙት ክፍያ ነው። ኸዲጃ ይሰኛሉ። እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለዉን የጡረታ ዋስትና የሚቀበሉት በዓመት አንድ ጊዜ ነው። መንግስት የሚሰጠውን ገንዘብ እንዲያገኙ የታገለላቸዉ የቅርብ ጎረቤታቸው አንድ ወጣት ነበር። ኸዲጃ ገንዘባቸውን በተቀበሉ ጊዜ ሁሉ ካንጀታቸው ይመርቁታል።
ምግባረ ሠናዩ ወጣት አካባቢውን እስከለቀቀበት ጊዜ ድረስ ወይዘሮዋ ክፍያውን ለመቀበል ሲሄዱ አጃቸውን ይዞ ወገባቸውን ደግፎ ሲያመላልሳቸው ለዓመታት ሲያገለግላቸው ቆይቶ፣ በመጨረሻ አካባቢውን ለቀቀ። ወጣቱ መኖርያውን ከቀየረ ጥቂት ወራት በኋላ የደመወዝ ክፍያ ቀን ደረሰ። ወጣቱ የለም። ከአካባቢው ነዋሪዎች እምነት የሚጣልበትና አድርሶ ሊመልሳቸው የሚችል ሰው አላገኙም።
ኸዲጃ ከዚያ የተባረከ ወጣት ሌላ እምነት የሚጥሉበት ሰው እንደማያገኙ ተረድተዋል። ብቻቸውን ለመሄድ ቆርጠው ተነሱ።ቁና ቁና እየተነፈሱ ክፍያው ከሚፈፀምበት መስሪያ ቤት በደረሱ ጊዜ የመስሪያ ቤቱ ሴት ሰራተኞች በሚገባ ተቀብለው አስተናገዷቸው። ድካማቸውን ተወጥተው፣ ደሞዛቸውን ተቀብለው ወደ ቤታቸው ለመመሰስ ሲነሱ የመስሪያ ቤቱ ሴት ሰራተኞች እስከ ታክሲ መሳፈርያው ድረስ ሸኛቸው።
ሸኚዎቻቸው ቆመው ታከሲ በመጠበቅ ላይ ሳሉ አንድ በመካከለኛ ዕድሜ ላይ የሚገኝ ባልቴቷን በስም ጠርቶ እጃቸውን በመሳም ሰላምታ ሰጣቸው። ወደ ሸኚዎቻቸው ዞሮ የቅርብ ጐረቤታቸው መሆኑን ነገራቸው። መኪና ይዟል። ሸኚዎቹ ታክሲ እየጠበቁ እንደሆነ ሲነግሩት “እኔ እያለሁ ምን ታክሲ ያስፈልጋል። እናንተ ተመለሱ እኔ አደርሳቸዋለሁ" በማለት ሸኚዎቹን አስናብቶ ባልቴቷን ወደ መኪናው ወሰዳቸው። ጎልማሳው ኸዲጃን ከጐኑ አስቀምጦ የባጥ የቆጡን እያወራ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ከግማሽ ሰዓት በላይ ተጓዙ፡፡
ኸዲጃ መንገዱ ያለቅጥ ረዘመባቸውና አንዳች ነገር አእምሯቸውን ከነከነው። ጥቂት አሰቡና “ምናልባትም እግረ መንገዱን መድረስ የፈለገበት ይኖር የሆናል" ሲሉ ስጋት ያደረበት ልባቸውን መልሰው አረጋጉት። ነገሩ ግን እንደዚያ አልነበረም። ሰውየው አቅጣጫውን በመቀየር ወደ ግራ ታጥፎ ከዋናው መንገድ በመውጣት ጉዞውን ሽቅብ ወደ ተራራው አደረገ። የኸዲጃ ልብ በፍርሃት ይናጥ ገባ። መላ አካላቸው ተንዘፈዘፈ ...መጮህ ቃጣቸውና መልሰው ተውት። የሞት ሞታቸውን “ልጄ ወዴት ነው የምትወስደኝ?" ሲሉ ጠየቁት ቁርጥ ቁርጥ ባለ አነጋገር። “እዚህ ቅርብ ነው። የአትክልት ቦታዬን ማየት አለብኝ። እርስዎም ፍራፍሬዎችን ይዘው ቤትዎ ይመለሳሉ" አላቸው። ያሰበው ነገር የተነቃበት ይመስል በተሳሰረ አንደበት።
ኰሮኰንቹን ሲጨርስ መኪናውን አቆመ። ዝምታ ለደቂቃዎች ሰፈነ። ትርጉም ያለው ዝምታ ነበር፡ የባልቴቷን የሰጋት፣ የጐልማሳው ደግሞ ዘዴን የመሻት። ደቂቃዎች ተቆጠሩ። ጐልማሳው ጥጥና ጨርቃ ጨርቅ ነገር ከኪሱ አወጣ። በፍርሀት ተውጠው አቀርቅረው የተቀመጡትን ደካማ አሮጊት አንገት አነቀ። እንዳይገድላቸው ተማፀኑት። ገንዘባቸውን ወስዶ ሕይወታቸውን ብቻ እንዲያተርፍላቸው ለመኑት። ስለ ነገሩ ለማንም ትንፍሽ እንደማይሉም ገለፁለት። .....በአምሮተ ንዋይ የታወረው ጐልማሳ ግን ሊራራላቸው አልቻለም። ይልቁንም ጭካኔውን አባሰው። አፋቸው ውስጥ ጥጥ ከጐሰጐሰ በኋላ ገዘባቸውን ከጉያቸው አወጣ። አጆቻቸውን ከተቀመጡበት ወንበር ጋር የፊጥኝ አሰራቸው። ከመኪናው ወርዶ ከኋላኛው የመኪናው ኪስ አካፋና ዶማ አወጣ።
ደካማዋን ባልቴት ገድሎ ከቀበረ በኋላ በገንዘባቸው ዓለም ዘጠኝ ሊሰኝ በመወሰን ቁፋሮውን ተያያዘው። መጠኑ ብዙ በሆነው ብር የሚያገኘው ደስታ እየታየው በጥድፊያ ይቆፍር ጀመር። ቢሆንም ግን ጉድጓዱን ቆፍሮ ሳይጨርስ ድንገተኛ ፍትህ ከአላህ ዘንድ ወረደ። ርዝማኔው ከአንድ ሜትር በላይ የሆነ ኮብራ እባብ አቀርቅሮ በሚቆፍረው በዚያ አረመኔ ሰው ጀርባ ላይ ተከመረ። አራት የተለያየ ቦታ ከነደፈው በኋላ አንገቱ ላይ ተጠመጠመ። ወጣቱ ደካማዋን አሮጊት ለቀብርባት በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ተዘረረ።
ይህ ሠማያዊ ፍትሕ ከመውረዱ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት ሰውየው ጉድጓዱን በመቆፈር ላይ ሳለ የተጨነቁት ባልቴት ደጋግመው አላህን ይለምኑታል “በእርግጥም ያንተ ፍጡር ነኝ። በንፁህ ልቤም ተገዝቼሀለሁና ከዚህ ድንገተኛ መአት አድነኝ። የማሳድጋትን የቲም ልጅ ለወግ ማዕረግ ሳላበቃ አትግደለኝ" ይሉ ነበር ደጋግመው።
#ባርያውን_የማይረሳው ጌታ የእኒህን ደካማ ሴት ጥሪ ሰምቶ ፈጣን ምላሹን ሰጠ። ሕይወታቸውንም ታደገ።
ሰዓታት አንድ ሁለት ተብለው ተቆጠሩ። ህፃናት እረኞች የከብት መንጋ አየነዱ በአካባቢው ሲያልፋ የቆመ መኪና ተመልከተው ተጠጉ። በአእምሯቸው የሚከብድ ነገር አይተዋልና ለወላጆቻቸዉ ሊነግሩ ፈጠኑ። የህፃናቱ ወላጆች የሰሙትን ለፓሊስ አሳውቀው ወደ ሥፍራው ተጓዙ።
....አፋቸው በጥጥና በጨርቅ የታፈነውና እጆቻቸውም የፊጥኝ የታሰሩት አሮጊት ፖሊስ ደርሶ ከአፈናውና ከእስራቱ ነጻ አወጣቸው “አልሐምዱሊላህ" ሲሉ ተሰማ። ጉድጓድ ውሰጥ የተዘረረውን ሰው ሁኔታ ለማጣራት ፖሊሶች ፊታቸውን ወደዚያ አዞሩ። ወደ ሰውየው በማምራት ላይ ሳሉም በሰውየው አንገት ላይ የተጠመጠመው እባብ ቀስ በቀስ ተፈትቶ ወደ ጥሻ ውስጥ ተፈተለከ። የሰውየው ነገር አብቅቷል። የደም ዝውውሩ አቁሟል። አስከሬኑ ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ሲላክ ደካማዋ አሮጊት ወደ ቤታቸው ተወሰዱ። አጀብ የአላህ ስራ!
#ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ
አብሽሩ አይዞን ....ጥሎ የማይጥል በችግር በጭንቅ በሀሳብ ከሰዉ መፍትሄ የጠፋ ጊዜ የሚሰማ ለእኛ መፍትሄ ቅርብ የሆነ ጌታ አለን አልሀምዱሊላህ፡፡ አልቅሰን ሰደቃ ኸይር ስራ አብዝተን ወይም ተዉበተን አድርገን እንቅረበዉ እንጠይቀዉ አላህን ጠይቆ ያፈረ ባዶ እጁን የተመለሰ የለምና
🔰🔰ብቻ ብቻ ጠይቀነዉ ዘግይቶ ይሆናል እንጂ የጠየቅነዉ አይቀርም.አላህ የኛን ዉስጥ ስለሚያቅ የጠየቅነዉን ቢሰጠን ለኛ የማይጠቅም ከአላህ የሚያጣላ ሊሆን ስለሚችል አስቀርቶት በአጅር በምንዳ ወይ በሌላ ለኛ በሚጠቅም
ነገር ቀይሮት ይሆናል ለምሳሌ በጤና እና ድንገተኛ አደጋ የሚመጣን በላዕ ችግር አስቀርቶልን ይሆናል፡፡ የአላህን በር አንኳክቶ ቦዳዉን ላይመልስ ቃልገብቷል፡፡ እስኪ ለሰዉ ነግረነዉ ያልተፈፀመ ከሰሚዉ ጆሮ ያላለፈዉን ጉዳይ ያአሏህ ያዘል ጀላሊ ወልኢክራም ብለን እንገረዉ ..መልስ አለ
አይዞን የምን ተስፋ መቁረጥ ጠበቅ አድርገን የአላህን ደጅ ከመፅናት እንዳናቆም .የጠየቅነዉ ሁሉ አላህ የጠየቃችሁት ከኔ የማያጣላችሁ ብሰጣችሁ እኔን ወንጅላችሁ ጀነቴን ታጣላችሁ ብሎ አስቦልን ይሆናል ያልሰጠን እንጂ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ዱአ ስናደርግ የተደረገዉ ዱአ የሚደርስ ወይም ወንጀል እንደሚያብስ ወይም ለአኼራ እንደሚቀመጥ ነግረዉናል፡፡
አይዞን