💚#በረሱል_ፍቅር_ሰጥሜ_መስጂዳቸውን_ጎጆዬ
............. #ላደርግ_ለአላህ_ቃል_ገባሁ.............
✍አሚር ሰይድ
ቁመቱ አጭር መልኩም የቀይ ዳማ ነው። ጀለቢያ መልበስ ያዘወትራል። ከዘምዘም ዉሀ በመዳፉ እየጨለፈ ይጎነጫል። ካገኘ ፍርፋሬ ይመገባል። ካጣም ሆዱን አጣጥፎ የጌታውን ቁርአን እያነበበ ፆሙን ያድራል። መሬት ፍራሹ፣ ብርድ ልብሱም ሠማይ ነው። የነቢ መስጂድ ውስጥ ጎጆውን ቀልሶ ለአስርት ዓመታት ኖሯል። ሰውነቱ የኮሰሰ ቀጫጫ ትውልደ አልባኒያዊ ነው።
ከነቢ ቀብር ፊት ለፊት ከሐረም አን-ነበዊ መታጠቢያ ቤት የወጣውን ይህን ወጣት አራት የሰዑዲ ፖለሶች ዘለው ተከመሩበት። በሆዱ አስተኝተው እጆቹን ቀፍድደው የፊጥኝ አሰሩት “ሽፍታም ሌባም አይደለሁም” እያለ መጮኽን መማፀን ጀመረ።
በዕድሜ የገፉ አንድ ሽማግሌ ክስተቱን ተመልክተው ቢጠጉ ገፅታው አልጠፋቸውምና “ይህን ወጣት አውቀዋለሁ” አሉ
“የረሱል መስጂድ ውስጥ እየሰገደ ሲያለቅስ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ አላህን ሲማፀን አውቀዋለሁ አዎ ራሱ ነው" አሉ መሬት ላይ የሚንፈራገጠውን ወጣት ትኩር ብለው እየተመለከቱ።
ጣል ጣል ብለው የሚታዩ የፂም ፀጉሮች ባለቤት ነው። ቀለል ያለ ሰው ፊቱ ላይ የሚንፀባረቀው ነጭ ኑር ከሩቅ ያብለጨልጫል። ሸይኹ ቀጠሉ "ምን አጥፍቶ ነው ያሰራችሁት?" ብለው ጠየቁ።
.... “አንተ ሽማግሌ!" አሉ ፖሊሶቹ" ጣልቃ አትግባ ይህ አንተን አይመለከትም" አላቸው።
“ሲሰርቅ አይታችሁታል?! ገዳይስ ነው ነፍስ ሲያጠፋስ ደርሳችሁበታል?! ወይስ ምን ወንጀል ሰርቷል?!" ሸይኹ ዳግም ግራ በመጋባት መንፈስ ጠየቁ፡፡
......“ይህ ወጣት" አሉ ፖሊሶቹ ንግግራቸውን ሲጀምሩ “ይህ ወጣት... ኑሮውን እዚህ መስጂድ ውስጥ ማድረግ ከጀመረ አስርት ተከታታይ ዓመታት ተቆጥረዋል። የመኖርያ ፈቃድ ኢቃማም ሆነ ፓስፖርት የለውም። በነቢ መስጂድ ስለተቀመጠ አባረን ልንዘው አልቻልንም ነበር። ስናሳድደው ሲያመልጠን ይሄው አስር ዓመታት ተቆጠሩ። ዛሬ ግን በእጃችን ገባ። ወደ ኤርፖርት ወስደን ወደ ሀገሩ አልባኒያ ልንመልሰው እንዳያመልጠን አድርገን አሰርነው" አሉ።
ወጣቱ የፖሊሶቹን ንግግር ሲሰማ ስቅስቅ ብሎ አያለቀሰ😢😢 “አልሰረቅኩም ነፍስም አላጠፋሁም በረሱል ፍቅር ሰጥሜ መስጂዳቸውን ጎጆዬ ላደርግ ለአላህ ቃል ገባሁ። ሽፍታም አይደለሁም። የአላህ መልዕክተኛን ስለምወድ እዚህ ቀረሁ። ከረሱል ﷺ መስጂድ ከሳቸው ጉርብትና ተነጥዬ እንዴት መኖር ይቻለኛል?? አለ ትካሻውን አያወዛወዘ
"ተቀባይነት የሌለው ምክንያት ነዉ ። እዛዉ ወደ ሀገርህ ትመለሳታለህ አሉ ፊታቸው በንዴት የቀላው ፖሊሶች
ወጣቱ ፊቱን ወደ መስጂድ አን-ነበዊ አቅጣጭቶ : -
“አላህዬ ስምምነታችን አንዲህ ነበር? " አለ አንገቱን ወደ ሰማይ አቅንቶ “ከአላህ መልክተኛ ጎን አኑረህ አንድትገለኝ አልነበር የጠየቅኩህ?! እናትና አባቴን ትቼ ሱቄን ዘግቼ የመጣሁትስ ለዚሁ አይደል?! ፍቅራቸው ንግዱን አስትቶ እዚህ አመጣኝ። መስጂዳቸውን መኖርያዬ ላደርግ ጉርብትናቸውን ትቼ ሀገሬ ላልገባ በአንተ ቃል ገባሁ። አሁን አነዚህ ሰዎች እየከለከሉኝ መሆኑን ተመልከት....ያ አላህ ጣልቃ ገብተህ ለምን በጠየቅኩህ ዱዓ ምላሽ አትሰጥም?! ያረቢ የረሱልን ጉርብትና እለምንሀለው😔" ሲል በምሬት እያነባ ጌታውን ጠየቀ።
......ከመቅፅበት በቆመበት ቦታ ተዝለፍልፎ መሬት ተደፋ። ፖሊሶቹ “ተነስ አንተ አታላይ” እያሉ በያዙት ዱላ አንድ ሁለቴ አቀመሱት። ወጣቱ ግን ምላሽ አልሰጠም መሬት አንደወደቀ ነው። ውሀ ደፉበት ሲነቃ ግን አልተቻለውም። አምቡላንስ በአስቸኳይ አስጠርተው ይዘውት ወደ ሆስፒታል አቀኑ።
ፖሊሱ ክስተቱን ሲያወጋ እንዲህ ይላል፡-
“ለሞት የሚያበቃ ዱላ አልሰነዘርንበትም። ሆስፒታል አንዳደረስነው ሀኪሞቹ የልብ ምቱን አዳምጠው ሩሑ ከጀሰዱ የመላቀቁን ዜና አረዱን። አዎ ከሰባት ሰማያት በላይ ያለው ጌታ አላህ ምሳሹን ሰጠ። በረሱል ሀገር በሳቸው መስጂድ አቅራቢያ ሩሁን እንዲያወጣ መለከል መውትን አዘዘ"
ፖሲሶቹ በትዕይንቱ ዕንባ እየተናነቃቸው በሀዘን ተብረከረኩ። በድርጊታቸው ተፀፅተው በዕንባ ተዋጡ።
"ለአላህ መልእክተኛ ﷺ ይህን ያህል ፍቅር እንዳለው ብናውቅ ኖሮ ይህን ባላደረግን” እያሉ በድንጋጤ ተዋጡ።
አምቡላንሱ ጀናዛውን ይዞ ወደ በቂዕ መቃብር ጉዞውን ጀመረ። ታላላቅ ሰሐቦች ወደተቀበሩበት ሥፍራ ከነፈ።
ሸይኹ “ክስተቱን ከጀምሩ እስከ ፍፃሜው እየተከታተልኩ ነበር" ይላሉ። ታጥቦ ተከፈነ ሰላተል ጀናዛ ከተሰገደበት በኋላ ወደ ቀብሩ ልናስገባው ስንሄድ ፖሊሶቹ በትከሻቸው ተሸክመውት ነበር። ጠጋ አልኩና አኔም ጀናዛውን ልሸከም አቀበለኝ አልኩት ለአንደኛው ፓሊስ። እሱም ዓይኖቹ አያነቡ "ወንጀላችን ይብቃን ምናልባት አላሁ ተዓላ ይቅር ይለን ዘንድ ጀናዛውን እኛ አንጂ ማንም እንዲሸከመው አንፈቅድም" አለኝ
ጌታህን አብዝተህ ስታወሳ መጨረሻህ የምራልና አላህዬን ይዘህ ፅና!!
ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ
⚡️⚡️ነብዩን መዉደድ ማለት ሙዚቃ የሚመስል ነሺዳን በሌላ አገላለፅ የአሁን ነሺዳ እሩብ ጉደይ ለሙዚቃ የሆነን በማዳመጥ ...አብሮ ነሺዳን በማለት በየመድረኩ ነቢይ በማለት አይደለም፡፡ የነቢይ ዉዴታ ሲኖርህ መድረክ ለመድረክ በየሚዲያዉ ነቢይ ስላልን ወደናል ማለት ራስን ማታለያ ነዉ፡፡ ራስን ማታለል ይቻላል አላህን ግን ማታለል አይቻልም፡፡ ነቢዩ ስም ልናነሳ ስንል እስክታዉ ዝላዩ ዉዝዋዜዉ ሳይሆን እንባችን ይቀድመን ነበር ወገን👌
በፊት የነበሩት ትዉልዶች ነቢይ ሙሀመድ ﷺ እንዴት እንደሚወዷቸዉ በኡሁድ ጦርነት ጊዜ ነቢይ ሙሀመድ ﷺ ይወዱ የነበሩ ሱሀቦች እና አሁን እኛ ባለንበት ሀቢቡና ﷺ እንዴት እንደምንወድ ራሳችንን እንፈትሽ ለምን....ነገ የምንቀሰቀሰዉ የስራችን ሚዛን የሚለካዉ ከእነሱ ጋር ስለሆነ...እኛ የነቢይ መሀመድ ﷺ ኡመት ነንና
በቀንም በሌትም በጧትም በማታም ሶሉ አለነቢይ ሙሀመድ ﷺ💚
አንድ ሺህ ነሺዳ ከማዳመጥ አንድ ሶለዋት አለረሱል ብናወርድ ነዉ ለኛ ነገ ሙተን ቀብር ገብተን ለአኼራ ጥያቄ የሚጠቅመን ..
ህይወት ትላንት ወይ ነገ አይደለችም ህይወት አሁን ናት ለቀብር የሚጠቅምህን ስራ፡፡አሁን ሲያልፍ ትላንት ይሆናል የወደፊት አሁን ደግሞ ነገ ይሆናል
....ግን ነገን ማየት ላንችል እንችላለን ጀናዛ ልንባል እንችላለንና በአገኘነዉ አጋጣሚ ጊዜን በነሺዳ(እሩብ ጉዳይ ሙዚቃ) ከማዳመጥ ይልቅ ሶለዋት አንዘንጋ
ሶሉ አለነቢይ ሙሀመድ ﷺ ﷺ ﷺ💚💚💚
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group